Connect with us

የጌታቸው ረዳን ቃለ መጠይቅ ሰማሁት፤ ሰውዬው አሁንም በትግራይ ህዝብ እንደጨከነ ነው!

የጌታቸው ረዳን ቃለ መጠይቅ ሰማሁት፤ ሰውዬው አሁንም በትግራይ ህዝብ እንደጨከነ ነው!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የጌታቸው ረዳን ቃለ መጠይቅ ሰማሁት፤ ሰውዬው አሁንም በትግራይ ህዝብ እንደጨከነ ነው!

የጌታቸው ረዳን ቃለ መጠይቅ ሰማሁት፤ ሰውዬው አሁንም በትግራይ ህዝብ እንደጨከነ ነው!

(እሱባለው ካሳ)

ጦርነት ምኑም ደስ የሚል ነገር ባይሆንም ገና ከጠዋቱ ባህላዊ ጨዋታዬ ነው እያሉ ስሜት ቀስቃሽ ድለቃ ሲለቁ የነበሩት ጨዋታው ላይ የሉም፡፡ ትህነግ አሁንም ከሰላም ይልቅ አመጽ፣ የማደርገውን አውቃለሁ ባይነትና ዛቻ ላይ ናት፡፡

ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ትርጉም በሌለው አመጽ የተሰማራው ሃይል ቢያንስ ከደረሰው ኪሰራ እና ህዝቡ ላይ ካሳደረው ጫና አንጻር በጥሞና ሊያስብ ሲገባው አሁንም እንጫረስ ዜማውን እያዜመ ነው፡፡

ጌታቸው ረዳ ትህነግ በዋና ዋና ሰዎቿ ሞት የደረሰባት ኪሳራ ማሳያ ናቸው፡፡ ከጌታቸው ረዳ ጋር ሲነጻጸር ቢያንስ እነኛ የበርሃ ታጋዮች ህዝባቸውን ይወዱታል፡፡ 

የምናድነው ፕሮጀክት የለም፤ የምንመኘው ወንበር የለም ግን ውጊያ እንቀጥላለን ማለት ትርጉሙ ሰላም አንፈልግም ማለት ነው፡፡

የጌታቸው ረዳ ንግግሮች ጦርነቱን በማቀጣጠል ህዝቡን በማስቆጣት በኩል እንኳን ዛሬ ያኔም ባለውለታ ነበሩ፤ አጋንንቶች ያሉት የኦሮሞ ወጣቶች ትህነግ ትብቃኝ ሲሉ ለቁጣቸው ጥሩ ምክንያት ሆነው ሰርተዋል፡፡ አማራ እና ኦሮሞን እሳትና ጭድ ሲሉ ውጤቱ ምን እንደወለደ አይተዋል፡፡

በየቀኑ የትግራይ ህዝብ የሚጎዳበትን ንግግር ሀሳብና ዛቻ በማፍለቅና ሰላም ጠል መርሆችን በማራመድ ትውልድን እልህ ውስጥ የሚከቱት ሰውዬ ሀሳባቸው ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ 

በቃለ መጠይቃቸው ከፈለግን እንጦጦ እንደርሳለን ሲሉ ስሰማቸው አሁንም ከዚህ ሁሉ ኪሳራ በኋላ ህዝቤ ያሉትን አካል የሚጎዳ በቀል ውስጥ ምን እንደከተታቸው ግራ ይገባኛል፡፡ 

አልፎ አልፎ ጣል የሚያደርጉት ሰላም ይበልጣል ባይነትን ደጋግመው እንወጋታለን፣ እናሳያታለን፤ ሌላ ስራ የለንም በሚሏት ኢትዮጵያ የቅዠት ምኞታቸው ያፈርሱታል፡፡ በእርግጥ ለአቶ ጌታቸው ትልቋ ኢትዮጵያ የሚባለው እንደሚያስቃቸው ነግውናል፡፡  

አሁንም ኪሰራን እንደ ድል የሚመለከተው አማጺ በህዝቡ ህይወት ዘመንና ሞራል ላይ እድሉን ስለመሞከር የሚያስብ መሆኑ ግን የጌታቸው ረዳ ሀሳቦች ማሳያ ናቸው፡፡ ለትግራይ ህዝብ ዋስትና የትግራይን ህዝብ ጨርሰንም ቢሆን እድላችንን እንሞክራለን ሲሉ ያለ መጨራረስ የትግራይ ህዝብ ደህንነት የሚጠበቅበትን መንገድ ማየት አልችልም እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡

ችግሩ ግን የኔ ያሉት ህዝብ ምን ያህል ቢከፉበት ነው እንዲህ ያለ ሀሳብ ማሰብ የፈለጉት፤ ምን ቢያደርጋቸው ሰላም መኖሩን ጠሉት፤ ለምን ይሆን አቅማቸውን በአንድ ትውልድ ህይወት መሞከርስ የፈለጉት? ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

በአሁኑ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋርም የውጊያ እቅድ እንዳላቸው ጠቆም አድርገዋል፡፡ ስለ ሂሳብ ማወራረድ ደጋግመው የሚናገሩት እልህ እንጂ ፍሬ የለውም፡፡ ያም ሆኖ ትውልድ ገብሬም ቢሆን ያሰብኩት አሳካለሁ አይነት ምኞት እገብረዋለሁ ያሉትን ትውልድ ምን ድረስ ቢጠሉት ነው?

መቀሌን በቅጡ ሳይመሩ ወልዲያን ይዘናል ፕሮፖጋንዳው ቢያስቅም የሚበጀውን ሰላም ለጦርነት የሄዱበት ርቀት ድረስ ሄደው አለመከጀላቸው ግን ህዝቡ ምን አስቀይሟቸው ጨከኑበት ያስብላል፡፡

በምክክር የሆነ በማይመስል መልኩ የእሳቸው ሀሳቦች አፈንጋጭ፣ ግለሰብ ተኮር፣ ሀገር በታኝ፣ የኔ ያሉትን ወገን ጎጂ፣ በትምክህት የተሞላ መሆኑ አሁንም ያሳሰበኝ፤ የእኔ ላሉት ህዝብ የሚያመጡትን ጦስ ሳስብ ነው፡፡ ቀስ ብሎ ማሰብ ከሁሉም ይበልጣል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top