”የሶማሊያን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም .. ”
(እስክንድር ከበደ – ድሬቲዩብ)
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ግዛትን ይገባኛል በማለት በኦጋዴን ጦርነት ከፍታ ፤ በፈረንጆቹ መጋቢት ወር 1978 ዓ.ም ሽንፈት አጋጠማት፡፡ ይህ ሽንፈት የፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬን በሱማሊያውን ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት ያሳጣቸው ሲሆን፤ በዛው አመት ሚያዚያ 10 በዚያድ ባሬ የጦር ጀነራሎች ዘንድ ተቃውሞ በመፍጠሩ የመፈንቅለ መንግስት ሞከሩ፡፡
አብዛኛዎቹ የመፈንቅለ መንግስት የሙከራ ጀነራሎች የተከበቡ ሲሆን፤የተወሰኑት ተገድለው ጥቂት የሚሆኑት አመለጡ፡፡
እ..ኤ.አ በ1980ዎቹ የሶማሊያ እርስ በእርስ ጦርነት የተቀሰቀሰው ከዚያድ ባሬ ጦር ባፈነገጠ አንጃ መሆኑ ይነገራል፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1988 እስከ 1990 ዓ.ም የሶማሊያ ጦር ኃሎች ከተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ውጊያዎች ያካሂድ ነበር፡፡ በሰሜንምስራቅ ከየሶማሊያ ዴሞክራሲያዊ መድህን ግንባር ጋር መዋጋት የጀመረ ሲሆን ፤፣በሰሜን ምእራብ ከሶማሊያ ብሔራዊ ንቅናቄና በደቡብ ደግሞ የሶማሊያ ህብረት ኮንግረሰ ጋር የመንግስት ጦር መፋለሙን ቀጠለ፡፡
ጎሳ ዘመም የሆኑት ተቃዋሚ ታጣቂ ቡድኖች የፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬን መንግስትን እ.ኤ.አ በ1991 ዓ.ም ከስልጣን አስወገዱ፡፡ የተለያዩ ታጣቂ አንጃዎች በተፈጠረው የስልጣን ክፍተት እና በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ሁከት ለመቆጣጠር በሚል እርስ በእርስ ፉክክር ያዙ፡፡
በሶማሊያ በውጊያው ሳቢያ እ.ኤ.አ በ1990 እስከ 1992 ዓ.ም መደበኛ ህግን ማስከበር አልተቻለም፡፡
እ.ኤ.አ በመስከረም 1991 በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጦርነት ተቀስቅሶ በቀጣዩ ወራት በሀገሪቱ ተስፋፋ፡፡ በእርስ በእርስ ጦርነቱ ባዛው አመት መጨረሻ 20 ሺህ ሰዎች ለሞትና ጉዳት ዳረገ፡፡ጦርነቱ የሶማሊያን ግብርና አውድሞ ፤ በሀገሪቱ የተወሰነ ክፍል ክፍተኛ ረሃብ እንዲከሰት ሆነ፡፡
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህይወት አድን የምግብ አቅርቦት ለረሃብተኛው ህዝብ ቢልክም ፤ የጦር አበጋዞችና የጎሳ መሪዎች በመጥለፍ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች በመሸጥ ከሌሎች ሀገራት የጦር መሳሪያዎች ይሸምቱበት ገቡ፡፡ 80 በመቶ የሚገመተው የእርዳታ እህል ይዘርፋል፡፡ ይህ የተፋላሚ ወገኖች የእርዳታ እህል ዘረፋ በሶማሊያ ያለውን ረሃብ ስላባባሰው 300 ሺህ ሰዎች በረሀብ እንዲሞቱ እና እ.ኤ.አ በ1991 እስከ 1992 ዓ››ም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች በቸነፈር ተሰቃዩ፡፡
እ.ኤ.አ በሐምሌ ወር 1992 ዓ.ም ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ ማቆም ስምምነት ካደረጉ በኋላ የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ስርጭቱን የሚታዘብ 50 ወታደራዊ አባላት ያሉት ልኡክ ወደ ሶማሊያ አሰማራ፡፡
እ.ኤ.አ በነሐሴ ወር 1992 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሚያደርገው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ኦፕሬሽን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤች.ደብሊዩ ቡሽ የአሜሪካ ጦር ድጋፍ እንደሚያደርግ ይፋ አደረጉ፡፡ አስር ሲ-130 የጭነት አውሮፕላኖች እና 400 ሰዎች ኬኒያ ሞባሳ ወደብ በመግባት እህልና መድሃኒት ከሞባሳ ወደ በሶማሊያ ገጠራማ ስፍራዎች በአየር ማጓጓዝ ጀመሩ፡፡ አውሮፕላኖቹ 48 ሚሊየን ቶን የእርዳታ ምግብና መድሀኒት ለተራበው 3 ሚሊየን የሱማሊያ ህዝብ ለማድረስ ጥረት ተጀመረ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የጽጥታው ምክር ቤት እ.ኤ.አ ታህሳስ 3 ቀን 1992 የተባበሩት መንግስታት አሜሪካ መራሽ የሰላም አስከባሪ እንዲሰማራ የውሳኔ ቁጥር 794 ያስተላልፋል፡፡
ተ.መ.ድ ጸጥታው ምክር ቤት እ.ኤ.አ በ1993 የሱማሊያ ማአከላዊ መንግስት መውደቁን ተከትሎ፤ የአሜሪካ መራሹ ሰላም አስከባሪ ጦር በሱማሊያ የሰላም ማስከበርና ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንዲያካሂድ ስልጣን ሰጠ፡፡
ከሁለት አመት በኋላ የሰላም አሰከባሪ ጦር ቁጥር እንዲቀንስ ሲደረግ፤ የጦር አበጋዙ መሀመድ ፋራ አይዲድ በሰላም አስከባሪው ላይ ጦርነት እንዲከፈት አወጀ፡፡
እ.ኤ.አ በ1993 አመተ ምህረት በሱማሊያ እርስ በእርስ ጦርነት ማአከላዊ መንግስቱ መፍረሱን ተከትሎ ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ሰላም አሰከባሪው ጦር ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስድ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
ከሰላም አሰከባሪ ጦር አባላት አብዛኛዎቹ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ከፊል ሞቃዲሾን የተቆጣጠሩት ሚኒሻዎች የጦር አበጋዙ መሀመድ ፋራህ አይዲድ ሞቃዲሾ የቀሩትን ጥቂት የሰላም አሰከባሪ ኃይል ላይ ጦርነት አወጁ፡፡
ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ ሶስት ልዩ ኦፕሬሽን ኃይሎች እራሱን ፕሬዚዳንት ብሎ የሚጠራውን የሞቃዲሾውን የጦር አበጋዝ አይዲድን ለመያዝ ከፍተኛ ግብግብ የገጠሙበትን ”የሞቃዲሾው ውጊያ ” ይሰኛል፡፡
የአይዲድ ሚኒሻዎች ከአሜሪካ ልዩ ኮማንዶዎች ጋር ያደረጉትን አሰቃቂ ውጊያ ፡፡ በጦርነቱ 1ሺህ ሱማሊያውያንና 19 አሜሪካ ልዩ ኃይል አባላት የሞቱበት ሲሆን፤ የአይዲድ ሚኒሻዎች Black Hawk የተሰኘችውን ሂሊኮፕተርን በመጣል ብሎም የሞተ የአሜሪካ ወታደርን ሲጎትቱ የሚያሳይ አሰቃቂ የጦርነት ፊልምን ሆሊውድ ሰርቶ ተመልክተናል፡፡
የሱማሊያ የጦር አበጋዞች የተዋጉት ወይም ያጠቁት የራሳቸውን ወታደር ሳይሆን የውጭ ወታደሮች ናቸው፡፡አሜሪካ በዛ ውጊያ የሞቱትን እና የቆሰሉ ወታደሮቿ በመኪና ያሸሸች ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ወታደሮች በእግራቸው ሮጠው አመለጡ፡፡ አሜሪካ በዚህ አዋራጅ ጦርነት ላለመቀጠል በወቅቱ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ትእዛዝ እንዲወጡ የሆኑበት ሁኔታ ይታወሳል፡፡ ይህ ጦርነት የተካሄደው በአንዲት ደሃ የአፍሪካ ሀገርና በኃያሊቷ አሜሪካ