Connect with us

ባለ ኮኮብ ሆቴል ከሺህ ዓመቷ ኢትዮጵያ ህልውና አይበልጥም፤

ባለ ኮኮብ ሆቴል ከሺህ ዓመቷ ኢትዮጵያ ህልውና አይበልጥም፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አንጥፈው ለሚጨፍሩት ኢትዮጵያ ሀገራቸው አይደለችምና!
social media

ነፃ ሃሳብ

ባለ ኮኮብ ሆቴል ከሺህ ዓመቷ ኢትዮጵያ ህልውና አይበልጥም፤

ባለ ኮኮብ ሆቴል ከሺህ ዓመቷ ኢትዮጵያ ህልውና አይበልጥም፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አንጥፈው ለሚጨፍሩት ኢትዮጵያ ሀገራቸው አይደለችምና!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

አዲስ አበባ የተዘጋው ባለ ኮኮብ ሆቴል ቁጥር እንዲህ ደረሰ የሚል ዜና ስላቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገር ናት፤ እየወጓት እየጠሏት ጡትሽን ካልጠባሁ እና ነግጄ ካላተረፍኩ ማለት ቀልድ ነው፡፡ አሜሪካም ቢሆን ከኦሳማ ቢላ ደን የተዛመደ ባለ ሆቴል ባንዲራዋን አንጥፎ እየጨፈረ የታሊባን ድሏን ቢያራክሰው ስቃ አታልፈውም፡፡

አዲስ አበባ የሆነውን አየን፤ ከኢትዮጵያ የሚጋጠምን ጠላት የሚደግፍ ባለ ሃብት ቢያንስ ምኞቱና ቅዠቱን ይዞ ይኑር በሚል ቢተው የሆነው ነገር ጸሐይ የሞቀው ነው፡፡ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ለመቀለድ እየሞከሩ ኢትዮጵያን ሀገሬ ማለት አይቻልም፡፡

ትግራይ ታሸንፋለች የሚል የቅዠታሞች ዜማ እያቀነቀኑ የጥቂት ቀማኛ እና ሽፍታዎችን ምኞት ለማሳካት እየባተሉ መልሶ በሀገራችን መስራት አልቻልንም ድራማ የለም፡፡

እንደው ለመሆኑ ወያኔ እና ጌታቸው አሰፋስ ቢሆኑ የግንቦት ሰባት እና የኦነግን ድል በአዲስ አበባ እናብስር አስረሽ ምቺው የሚገባ ባለሃብት ቢመለከቱ ቤተ መንግሥት ጠርተው ይሸልሙት ነበር?

ጌታቸው አሰፋ እኮ በሆድህ ተቃዋሚ ደግፈሃል ብሎ ነው ስንቱን በየሜዳው ሲያረግፍ የኖረው፡፡ ያ ሞልቶ የፈሰሰው የግፍ ጽዋ እንዲህ አርአያም ደርሶ ዋሻ ለዋሻ ያርመሰመሳቸው እኮ እንኳን የሆነ ያልሆነ ሆነ ብለው ሀገር አሳድደው ነው፡፡

ሁሉንም ያየን ሰዎች ዛሬ በህይወት አየን፤ ኢሳት ቴሌቨዥን አትመልከቱ ተብሎ እኮ አዋጅ ታውጆብናል፡፡ ዜና መስማትን የሚከለክል መንግስት መከላከያ ተሸነፈ ብሎ የሚጨፍር ሀገር የለሽ ውራጃምን አደብ ቢያስገዛ ምን ይገርማል?

እንኳን አራት እና ስምንት ባለ ኮኮብ ሆቴል ድፍን የሀገሩ ሆቴል መኖር የሚችለው ኢትዮጵያ ስትኖር ነው፡፡ ያኔ እኛ ብንሆን ኖሮ ምን እናደርግ ነበር የሚለውን ማሰብ ቅንነት ነበር ያን ማሰብ አለመቻል ከመርከብ ሌብነት ዱቄት ዘራፊነት የከተተው ጁንታ ሆቴል ተዘጋ ባለሃብቱ ተጎዳ የሚል ድራማ ውስጥ ቢገባ ቀልድ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ከሀገር ነቀርሳ ጋር እየተዋጉ ነው፡፡ ይሄንን ትግራይ ከኢትዮጵያ ገጠመች ብላችሁ የምትተረጉሙ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሀብታችሁን ለመጠበቅ ከምትንፈራገጡ ትግራይ ያሉ የወንድሞቻችሁን ነፍስ ለመታደግ መፍትሔ ብትሆኑ መልካም ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከብረው ኢትዮጵያን የመውጋቱ ፋሽን በሚቀድመው ትግል አብቅቷል፡፡ ተረት ቀመሱ የተራራ አንቀጥቅጥ ታሪካችሁ የነውራችሁን መንገድ ነግሮናል፡፡ ያ ድጋሚ በእናት ሀገር ኢትዮጵያ ምድር አይሆንም፡፡

ኢትዮጵያውያን ትግራይ ጠላታችን ናት አላሉም፤ እናንተ ኢትዮጵያ ጠላታችን ናት ብላችሁ እንበር ተጋዳላይ ለማለት ቢያንስ ኢትዮጵያ ላይ ሆናችሁ አትችሉም፡፡ የነገውም እውነት ይሄው ነው፡፡ ንጹህና ሀገር ወዳዱ የትግራይ ሰው እንኳን ለዕለት ጉርሱ ዛሬም በሹመት አለ፡፡ ዛሬም ሀገር የሚመሩ ትግራዋይ አሉ፡፡ ዘራፊውን አቅፋለሁ ያለ ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ 

በዚህ ሁሉ የወንበዴ ድራማ ውስጥ አዲስ አበባ ተቀምጦ ግንባር ለሃገሩ በሚዋደቅ ወታደር ማላገጥ እንደማይቻል ግን የንግድ ቤቱ መዘጋት ምልክት ነው፡፡ ልክ ያልሆነ ነገር መቀጠል ልክ ያልሆነ ውጤት ያመጣልና፤

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top