Connect with us

“ክተት!!”

"ክተት!!"
አሚኮ

ነፃ ሃሳብ

“ክተት!!”

“ክተት!!”

“በአማራ ክልል ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሳሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ [ከዛሬ] ጀምሮ ይክተት” ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። አሸባሪው ትህነግ በተለያዩ ግንባሮች ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ የማጥቃት ሙከራ እያደረገ ነው ብለዋል። ሕዝቡ ከጎናችን እንዲሆን ባስተላለፍነው መልዕክት በአሁኑ ወቅት በሁሉም ረገድ ከጎናችን ሆኗል ነው ያሉት። ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋና ይገባዋልም ብለዋል።

የክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ለክልሉ መንግሥትና ለጸጥታው ኃይል ያደረጉት ድጋፍ የክልሉን መንግሥት አኩርቷል ነው ያሉት። የአማራ ክልል ባለሀብቶችና የንግዱ ማኅበረሰብ እያደረጉት ላለው ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ከተሠለፈብን ጠላት አኳያ ብዙ ኃይል የምናሰልፍበትና ሎጅስቲክስ የሚያስፈልግ ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ የክልሉ ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ያሰዩት ምላሽ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል። ክልሎች እያደረጉት ያለው ድጋፍ ታሪካዊ ነውም ብለዋል።

የክልሉ ተመላሽ የሠራዊት አባላትና የጦር መኮንንኖች ሠራዊቱን ተቀላቅለው እየተፋለሙት እንደሚገኙም ገልጸዋል። አሸባሪው ትህነግ በውጊያው ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ እያሰለፈ ነው፣ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን እያስጨረሰ ነው፣ ጦርነት የማያውቁ ሕፃናት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ጉዳት እየደረሰባቸው ነውም ብለዋል፡፡

የትህነግ ዓላማ የአማራን ሕዝብ ለማጥቃትና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያለመ ስለመሆኑም ተናግረዋል። ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ነው ብለዋል። በራያና በጠለምት ግንባሮች የጁንታው ጀሌዎች እንደ ቅጠል እየረገፍ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት እየታገለ የመጣ ጀግና ሕዝብ ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ አማራ ማን እንደሆነ ያውቁታል፣ ይህን ሕዝብ ለማንበርከክ የትኩረት አቅጣጫ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነውም ብለዋል።

አሸባሪውን ቡድን የአፋርና የአማራ ሕዝብ እየተፋለመው ነውም ብለዋል። በሕዝቡ፣ በልዩ ኃይሉና በመከላከያ ሠራዊት ትህነግን የመምታት ሥራ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል። ይህ ኃይል እስካልጠፋ አናርፍም ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ። የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ ጦርነቱ የአማራን ሕዝብ ሕልውና የምንታደግበት ነውም ብለዋል።

የሕልውና ጦርነቱን በአሸናፊነት ለመጨረስ የአማራ ሕዝብ አስተዋጽኦ የጎላ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ርእሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከዛሬ ሐምሌ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ማዕከል እንዲከት የክተት ጥሪ ተላልፏል።

ሁሉም የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ለፀረ ትህነግ ዘመቻ መዘጋጀት አለበት ብለዋል። የክተት ጥሪው አማራንና ኢትዮጵያን የመታደግ ጥሪ ነውም ብለዋል። ሀገር የማፈረስ ዓላማ ያለውን ኃይል በተባበረ ክንድ መደምሰስ አለብን ነው ያሉት። 

አሁን በገጠምንበት አውደ ውጊያ ከፍተኛ ከሲሳራ እየገጠመው ነው፣ ወደ ትግራይ ተመልሶ መሄድ አይፈልግም፣ ምክንያቱም ለትግራይ እናቶች የሚሰጠው መልስ የለውም፣ ስለዚህ ህልሙን ማጨናገፍ አለብን ብለዋል፣ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነውን ከሀዲ ቡድን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሁሉም መነሳት አለበት ነው ያሉት።

በአሉባልታ ሊያፈርሱን ስለሚፈልጉ ከአሉባልታ መጠበቅ ይገባል፣ በአንድነት ማሸነፍ አለብንም ብለዋል። በሁሉም ግንባር የጠላትን ኃይል ዋጋውን እየሰጠነው ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ሕዝቡ ከጎናችን መሆኑን መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

ኅብረተሰቡ መረጃ እንደሚያስፈልገው እናውቃለን ነገር ግን ሁሉም የጦርነት መረጃ ስለማይነገር በትዕግሥት መጠበቅ ይገባል፣ አስፈላጊ መረጃ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ይሰጣልም ብለዋል። መረጃ ከትክክለኛው አካል መውሰድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሁሉም ሕዝብ በትህነግ ፕሮፖጋንዳ ሳይደናገጥ የቡድኑን እኩይ ድርጊት መታገል እንዳለበትም ገልጸዋል። ሠርጎ ገብነት ላይ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅም አሳስበዋል፣ የትግራይ ሕዝብ ወንድማችን ነው፣ ትግሬ የሆነ ሁሉ ጠላታችን አይደለም፣ በትህነግ ፕሮፖጋንዳ ተሳስቶ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ እየተዋጋ ነው፣ አሁንም መላው የትግራይን ሕዝብ አይወክልም ነው የምንለው፣ ነገር ግን የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ወደጦርነት ከማሰለፍ መታቀብ አለባቸው፣ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ ነው፣ ወያኔን በቃህ ማለት አለበት፣ በክልላችን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሰላም እንዲኖሩ እንፈቅዳለን፣ ለጠላት የሚያብሩ ካሉ ግን ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት።

የአማራን መሬት ለወያኔ እሾህ እናደርገዋለን፣ በየትኛውም አቅጣጫ ሊንቀሳቀስ እይችልም፣ ሁሉም በየደረጃው መደራጄት አለበት፣ ወደ ግንባርም መሄድ አለበት ነው ያሉት። ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የጀመሩትን አኩሪ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። ወቅቱ ለአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ወቅት ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ታሪክ የምንሰራበት ነው፣ ባንዳን መቅበር ደግሞ የአማራ ሕዝብ እንደሚያውቅበት ገልጸዋል።

(አሚኮ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top