Connect with us

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ዘመቻው ህልውናችን ነው ብለዋል፤ ጎንደር “ምነው አሜሪካ?” ብላለች፤

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ዘመቻው ህልውናችን ነው ብለዋል፤ ጎንደር "ምነው አሜሪካ?" ብላለች፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ዘመቻው ህልውናችን ነው ብለዋል፤ ጎንደር “ምነው አሜሪካ?” ብላለች፤

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ዘመቻው ህልውናችን ነው ብለዋል፤ ጎንደር “ምነው አሜሪካ?” ብላለች፤

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

እነሱ እኛን ለማፍረስ ሲኦል መግባት ካለባቸው እንደሚገቡ ነግረውናል፡፡ እኛ ገነት የሆነች ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት አይደለንም፡፡ ቆሞ የሚፈርስ ኢትዮጵያዊ በታሪክ እንደሌለ ዓለም ያውቃል፡፡

የትህነግ ጦርነት አሁን ዓላማው ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ባይነት እንጂ ሌላ አጀንዳ የለውም፡፡ የእርዳታ እህል ለሚያስፈልገው ህዝብ አፈሳና ጦርነት መፍትሔ አልነበረም፡፡ የእነ ጌታቸው ረዳ ዓላማ ስውር በቀል በአሸአ ላይ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አድዋ ሽሬ አክሱም እያሉ ትህነግ የገነቡት ስውር ሥርወ መንግስትን ነቅሎ ለመጣል ትህነግን ከኢትዮጵያ አዋግቶ ትግራይን በእናት ሀገሯ ላይ ጠላት አድርጎ ሁሉንም የማክሰሩ ሙከራ ቀጥሏል፡፡ እንኳን ከጣሊያን ባንዳ ከጣሊያንም መዳፍ አምልጠን ከነ ክብራችን አለን፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ዘመቻው ህልውናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኦሮሚያ ከተሞች ትህነግ ላይ የሚደረግን ዘመቻ ደግፈው ከዳር ዳር ቀውጢ ሆነዋል፡፡ አማራ በተለያየ አቅጣጫ ለመከላከያ ድጋፉን እየሰጠ ነው፡፡

ጎንደር በጠዋቱ ደማቅ ሰልፍ አድርጋለች፡፡ “አሜሪካንን ለምን?” ያለችው ጎንደር የህልውና ትግሉ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡ የጎንደር ሙስሊም ወጣቶች ዓለም በሚገባው ቋንቋ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሲዖል ገብቼ አፈርሳለሁ ያላቸውን ሃይል የሚዋጉበት ምክንያት የህልውና መሆኑ የሚገባው ስውር አጀንዳ የሌለው ነው፡፡ መቶ ሚሊዮን ህዝብን አጠፋለሁ ያለ ወንበዴ ቡድን ማንም ቢረዳው የትም እንደማይደርስ የምናይበት ቀን ሩቅ አይሆንም፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል መስሎትም ሆነ ተታሎ መከራውን የሚመለከት ከሰላም ህይወቱ የተነጠለ የጦርነት መንፈስና ተልእኮ ያልተለየው የትግራይ ህዝብ ያሳዝናል፡፡

ይህ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር የሚያደርጉት የድጋፍ ሰልፍ ጉዳዮን ከዶክተር አብይና ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ብቻ አያይዞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምቹ ነገር እንደሌለ መልእክት እያስተላለፈ ያለ ሰልፍ ነው፡፡

ድፍን ኢትዮጵያ ኪሱን ነፍሱን እና ሁለ ነገሩን ለህልውናው እንደሚሰጥ እያየን ነው፡፡ በርካታ መቶ ሺህዎች ወደ ጦር ሜዳ ለመግባት ውትድርና ተመዝግበዋል፡፡ ትህነግ አሁን የምትገጥመው ከደርግ ጋር አይደለም፡፡ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ታፍሶ ሳይሆን ተደባድቦ እንዴት እኔ አልዘምትም ብሎ ከዘመተ ሀገር ወዳድ ጋር ነው፡፡

የትህነግ ውንድብና ውጤቱን ታሪክ ቆጥሮ ይመዝነዋል፡፡ እውነት አለኝ ብለው ሀገር ዘርፈውና ሀገር ሸጠው በደሃ ነፍስ ግጥሚያ ያማራቸው ወንበዴዎች የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገ ታሪክ ሲሆኑ ከአሳፋሪውና ከሚሞተው ታሪክ ጋር አብረው የሚሞቱ ናቸው፡፡ በቁሙ ሲኦል የገባ አሸባሪ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚገባበት ሲኦል የለም፡፡

ትህነግ የአማራ ኢሊት ላይ አወራርደዋለሁ የምትለው ሂሳብ ውጤቱ አማራን አንድ አድርጎ ለህልውና አስነሳ እንጂ ሌላ አልፈየደም፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነገ ከነገ ወዲያ ቀሪ ሂሳብ አለባችሁ ልንባል ነው ብሎ በጋራ ቆመ እንጂ ከጥላቻ ንግግሩ አንዳች ትርፍ አልተገኘም፡፡

አሁን የገጠምነው ሲኦል ወርጄ ኢትዮጵያን አጠፋለሁ ካለ ሃይል ጋር ነው፡፡ ገነት ከሆነችው ኢትዮጵያ ሳንወጣ በገባበት ሲኦል እንደምናስቀረው አልጠራጠርም፡፡ ጦርነት ክፉ ነው፤ ትህነግን ማጥፋት ግን ጽድቁ ይበልጣል፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top