Connect with us

የተንኮታኮተው ህወሀትና አብሮት ያረጀው የሃይማኖት ቁማር!!

Social media

ነፃ ሃሳብ

የተንኮታኮተው ህወሀትና አብሮት ያረጀው የሃይማኖት ቁማር!!

የተንኮታኮተው ህወሀትና አብሮት ያረጀው የሃይማኖት ቁማር!!
( ገለታ ገ/ወልድ -ድሬቲዩብ)
ህወሀት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በቀረፀው ህገመንግስት የሃይማኖት እኩልነት፣ ነፃነትና ከመንግስት የተነጠለ መሆንን በነቢብ ያካተተ ቡድን መሆኑ ይታወቃል ፡፡
በገቢር ግን ፀረ የሃይማኖት እኩልነት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣በመንግስት የስልጣን ዘመኑ በእምነት ተቋማት ውስጥ እጁን እየከተተ ሲያተራምስ ነበር የቆየው ፡፡
ሌላው ቀርቶ አዛውንቱን ኦርቶዶክስ ለሁለት ክፍሎ ከማባላት ባሻገር ፣ በታላቁ እስልምልና ውስጥ ሁለት ቡድን ፈጥሮ ወህብያና አሀብሽ እያለ ሲያባላ መክረሙ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ፡፡ በየሃይማኖቶቹ ውስጥ ያለውን መከፋፋል ያስቀረው የለውጥ ሃይል መሆኑም ይታወቃል ፡፡
አሁንም በግብረሽበራና የጥፋት እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ ከዚሁ ነጣጣይ አስተሳሳብ እንዳልወጣ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል ፡፡
በአንድ በኩል የአብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግስት አገሪቱን ወደእስልምና እየወሰዳት ነው (በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዳራ ፣በጋራ አፍጥር ስርአት፣ በቤተመንግስት የሶርያ ስደተኞች ማፍጥር ስርአት …) ብሎ ህዝብ ያደናግራል ፡፡
በሌላ በኩል ለአናሳ ማንነትና እምነት ጠበቃ ነኝ ሲል መቆየቱን ረስቶት ፣ካብኔውን ፕሮቴስታንት ሞልቶታል ሲል በዲጂታል ቡድኑ በኩል ሊከፋፍል ዳክሯል ፡፡ ሲያሻው ደግሞ የኦሮቶዶክስ ሃይማኖትን የአንድ ብሄር መገለጫ እያስመሰለ፣ ከአገር አንድነት ምሶሶነት ለማውረድ የማይሸርበው ተንኮልም የለም ፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ደግሞ ለዚያው ለቆየበት የመከፋፋል ስትራቴጂ ሲል ብቻ ነው ፡፡
በመሰረቱ በአገራችን ሦስቱ የአለም ታላላቅ ሃይማኖቶች የአይሁድ ፣ የክርስትና፣ የእስልምና እምነቶች ለረጅም ዘመናት አብረው ነው የኖሩት ፡፡ መስጊድ ሲሰራ ክርስቲያኑ፣ ቤ/ክ ሲሰራ ሙስሊሙ ገንዘብና ጉልበት እያዋጣ የመኖሩ ብሂል የቅርብ ጊዜ አይደለም ፡፡
አንዱ አማኝ የሌለውን እምነት በአል አብሮ፣እሴቱንም በመጠበቅ እየበላና እየጠጣ መኖሩ ተደጋግሞ የተነገረ ነው፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሁለት ሶስት እምነት ተከታዮች በፍቅር የሚኖሩባት አገርስ የእኛው ታሪካዊ ምድር አይደለችምን !?
ኢትዮጵያዊያን በአለም ፣በመከራ፣በሠርግ ፣በቀብር ፣ በእድር፣ በጡት አባት ከመተሳሰር ባሻገር፣ እየተጋቡና እየተዋለዱ ተግባብተውና ተስማምተው በፍቅር የኖሩበት ምድር ነች ያላችን ፡፡ጁንታው ግን ህን ነባራዊ ሀቅ ነው ደጋግሞ የሚክደው፡፡
እንኳን የብሄር ፣የታሪክና ባህል ብዝሀነት ይቅርና የእምነት ስብጥራችንም የተሰናሰለ ሆኖ የቆየ ነዉ፡፡ ህውሀትና በአምሳሉ የቀረፃቸው ፅንፈኛ ሃይሎች ግን ትናንትም ሆነ ዛሬ ይህን ህብረት ማፍረስና የራሳቸውን ስንኩል ብሄል በህዝብ ላይ መጫን ነው የሚሹት ፡፡
አልተሳካላቸውም እንጂ ደጋግመው በአመማኞች መካካል ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበር የሚስተው የለም ፡፡
ህዝቡ ነቃባቸው እንጂ አክራሪዎችና የፖለቲካ ቁማድተኞችን ከፊት እያሰለፉ፣ ሲያሻቸዉ በብሄር ፤ አለፍም ሲል በቅዱሳን ሃይማቶቻችንን ደም ለማፋሰስ ብዙ ሴራ ሸርበዋል ፡፡ በተለይ የአገር ታሪክ አምሳያዋ ኦርቶዶክስን ለማዳከም ይማስናሉ፤ በመቻቻል ማሳችን ላይ እንክርዳድ እየዘሩበትም ይገኛሉ ፡፡
ሰላማዊውን እስልምና እንደጠላት ሃይማኖት ቆጥረው ለመንቀሳቀሳቸው ሰሞኑን በአፋር ወገኖቻችን ላይ ባደረሱት ጥቃት አሳይተዋል ፡፡ ሊሳካላቸው ግን አይችልም !!
ይህ የአሸባሪዎችና የፖለቲካ ቁማርተኞች እንክርዳድ ከዋናው ፍሬያማ የመቻቻል ውጤታችን ጋር መሳ-ለመሳ ሆኖ መጋፋት ከጀመረ ውሎ ቢያድርም፤ አሁንም ህዝቡ ሴራውን ነቅቶ መታገል አለበት ፡፡በመሞት ላይ ያለው ጁንታም ሆነ ተባባሪዎቹ ፅንፈኞች የተጀመረውን ለውጥና የአገር ሰላም ለማደፍረስ ብሎም፣ተራ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በህዝብ ደም ለመነገድ እንደማይመለሱ መንቃት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በብሄርም ሆነ በእምንት ሊለያዩ የሚሞክሩትን በመመከት ፣ አንድነታችንና ሰላማችንን ጠብቆ ሴረኞችን ማጋለጥ ያስፈልጋል !!
የህወሀትና ጥቂት ተባባሪዎቹ ግብና አላማ በቀዳሚነት አገሪቱን ሰላምና አንድነት የለሽ ፣እርስበርስ የምትባላና የተዳከመች ማድረግ ነው፡፡ ከዚያም በደቀቁ ጎረቤት አገሮች እንደምንመለከተዉ በጥቂት አጉራ ዘለሎች ፍጭት ፣ አገር ማተራመስና ፍርፋሪ ለሚያገኙበት የዉጭ ጠላት የወደቀች አገርን ማስረከብ ነዉ፡፡
ይህ ደግሞ መላው አገር ወዳድ ዜጎች እያሉ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ፡፡ጀግናው የመከላከያ ሃይላችንም ደምና አጥንቱን እየገበረም ቢሆን የሚፋለመው ይህን ሴራ ለመመከት ነው፡፡ እኛም እንደህዝብ ሁለንተናዊ አጋርነታችንን አጠናክር መገኘት ግድ ይለናል ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top