ባለፁኑ አቋሙ የምስራቅ ቀንዲል – ሙስጠፌ !
(ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ )
የምስራቁ የብልፅግና ሰው ሙስጠፌ መሀመድ ለአገራችን መዳኛ ሆነው ከመጡ የለውጥ ሃይሎች አንዱና ቀዳሚ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዘንዳንት ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ተቸንክሮ የቆየውን የከራር ብሄርተኝነት አስተሳሳብ የሰበሩ ጠንካራ የለውጥ ሰው ናቸው ፡፡
የህወሀት ግትርና ፅንፈኛ አካሄድም አጥፊና አገር በተኛ መሆኑን ቀድመው ተረድተው በጥብቅ የታገሉ፡፡
ለዚህ ቀዳሚው ማሳያ የህወሀት ጁንታ በአገር ላይ የደቀነውን አደጋ ፈጥነው የተረዱና ያወገዙ መሆናቸው ብቻ አይደለም ፡፡ ሰሞኑን ደጋግመው እንዳረጋጋጠቱም ይህ የጥፋት ሃይል አገር ለማፍረስ የመጣና ለማንም የማይመለስ መሆኑን በግልፅ ተገንዝበን በህብረት ከመታገል ውጭ አማራጭ የለንም ማለታቸው ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ በእርግጥም የኢትዮጵያን ጠላቶችም ሆነ ራሱ ጁንታዉን ክው ያደረገው ይሄው ህብረት ተጠናክሮ መውጣቱ ነው !!
ቀደም ባለው ጊዜም በአንድ የአገራችን ጋዜጣ ላይ “ እየተበተነ ያለን ህዝብ ወደ አብሮነትና አንድነት እንዲመጣ ተባብሮ መስራት ፣ አሃዳዊ ካስባለ አሃዳዊ ነኝ “ ያሉበት አገላለፅ ፣በተለይ መነጠል እንደሚሻ ሲተረክለት ከኖረው የሶማሌ ህዝብ አንፃር ሲታይ ፅንፈኞችን አንገት ያስደፋና ትልቅ አገራዊ ብርታትን የፈጠረ ነበር ፡፡ በርካታ አገር ወዳድ ዜጎችም ከምስራቁ ጀግና ጎን እንዲቆሙ አድርጎል !!
ጀግናው ሙስጠፌ ትናንትም ዛሬም የችግራችንን ሰንኮፍ በጥልቀት አውቀውታል ፡፡ “ የሚጠላትን አገር ለሶስት አስርት አመታት የገዛ “ ያሉት ህወሀት ፣ ህዝቦችን እርስበርስ እያፋጠጠ የስልጣን ዘመኑን ሲያራዝም የነበረ ነው ፡፡ ጎሳኝነትና መነጣጣልን እያቀነቀነ በአገር ላይ መተባበርና መደጋጋፍን ሳይሆን መስገብገብና መባላትን ፣እንዲሁም ራስ ወዳድነትን ነበር ያንሰራፋው ፡፡
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የቀጠለዉ ብሄር ተኮር ግጭት (አንዳንዴም የማንነት ዉዝግብ)፤ መፈናቀልና ተዘዋዉሮ የመስራትና የመንቀሳቀስ መብት መገደብ ሁሉ መነሻዉ የተዳከመዉ አገራዊ እንድነትና እየበረታ፣ጠባብነቱ እየጠባባሰ በመቆየቱ እንደነበር በሁሉም ታምኖበታል ፡፡ የዚያ ሁሉ ዲያብሎሳዊ አስተሳሳብ አባት ደግሞ ህወሀት መሆኑን ብቻ ሳይሆን ፣ዛሬም ነጣጥሎ ለመምታት እንዲመቸው” ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ “ ማለቱ በፍፁም ተቀባይነት እንደሌለውና መላ የአገራችን ህዝብ ሊታገለው እንደሚገባ ቀድመው ያረጋገጡት ሙስጠፊ ናቸው ፡፡ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸውና !!
እውነት ለመናገር ህወሀት በህዝብ ቁጣና ለውጥ በሚሻው ሃይል ቅድሚያ ብልሹውን አካሄድ እንዲያስተካክልና አብሮ እንዲቀጥል ነበር የተፈለገው ፡፡ እርሱ ግን አሻፈረን ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ትግራይ ክልል በመግባት በህገወጥ ድርጊት ከመሰማራት ባሻገር “ያልመራኋት አገር ትፍረስ!“ ብሎ በግልፅም ሆነ በድብቅ ብዙ ችግር ፈጥሯል ፡፡
በመጨረሻም በክልሎ የነበረውን የሰሜን እዝ በማጥቃት በዘረፈው መሰሪያና በአዘጋጀው ሰራዊት አገረ መንግስቱን አፍርሶ መልሶ ቀጥቅጦ ለመግዛት ነበር የሞከረው ፡፡መቼም ባይሳካላትም !!
ህወሀት በአንፃራዊነት አናሳ ከሚባል ብሄር ወጥቶ፣ አብዛኛውን የአገሪቱ ህዝብ በፈለገው መንግስታዊ ጫና ሳያለውስእንዲገደል ፣ እንዲታሰር፣ እንዲሰደድና አገር አልባ እንዲሆን ነበር ያደረገው ፡፡ እንዲሁም የጥቅም ተጋሪዎቹ የሆኑ ኢሊቶችና ጥገኞችን በማበልፀግ ፣ በትጥቅ ትግሎም ሆነ በደጋፊነታቸው “ማህበራዊ መሰረቶቼ“ የሚላቸውና ዛሬም ድረስ ለጥፋት የሚጠቀምባቸውን ትግሪኛ ተናጋሪዎች የመበዝበዣ መሳሪያ አድርጎ አገር ማራኮቱም ሊዘነጋ አይችልም ፡፡
ታዲያ ያ የኢፍትሃዊነትና የብልሽት ጊዜ እንዲመጣ ማን ነው የሚፈቅደው !!? ሙስጠፌ ተናገረውት እንጂ በሁሉም ልብ ውስጥ ያለው እውነት ያው ነው፡፡
ህወሀት ባለፉት ሶስት አስርትም ለአገዛዙ እንዲያመቸው እንደ ሀገር ህብረ ብሄራዊ ማንነት እየተረሳ ፤ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት እየተዳከመ በብሄር መከፋፋልና መናቆር እንዲበረታ ሰርቷል ፡፡ ይህን የከፋት መንገድ ለመመለስ የወጠነውን ሴራ ፣ ቢያንስ አሁን ካልነቃንበት ደግሞ በለውጥ ሃይሉና በህዝቡ ጥረት ከውድቀት አፋፍ የተመለሰቸውን አገር ዳግም አደጋ ላይ እንደሚጥላት ጥርጥር የለውም ፡፡ ትግሉ ትናንት በአፋር እንደተደረገው መራርና የማያዳግም ሊሆን ይገባል !!
እናም ብቸው መደኛ የምስራቁ ቀንዲል ሙስጠፌና ጎደኞቹ ያነሱት የጋራን ጠላት በጋራ መመከትና የአገር ህልውናን መረጋጋጥ ብቻ ነው፡፡የሁሉም ቀዉሶችና ችግሮች ማጠንጠኛ ፣ ከታሪካችን የቁርሾና የጥላቻ ጥጥ እየተፈተለና እየተገመደ እዚህ ያደረሰን አለመግባባትና ጭቅጭቅ ጠንሳሽ ህወሀትን አስተሳሰብና ተግባር ማስወገድም ነው ፡፡ ከዚህ ከነተበ ኋላቀር እይታ ጋር ተንገታግቼ እሞታለሁ የሚልንም ቅድሚያ ማስገንዘብና አደጋዉን ማሳዬት እምቢ ካለም ቆርጦ መጣል ያስፈልጋል ፡፡