Connect with us

በጁንታው የተዘረፉ መሬቶችን በመሸጥ ለሽብር ተግባር የገንዘብ ምንጭነት በሚያውሉ ላይ እርምጃ ይወሰዳል

ኢዜአ

ዜና

በጁንታው የተዘረፉ መሬቶችን በመሸጥ ለሽብር ተግባር የገንዘብ ምንጭነት በሚያውሉ ላይ እርምጃ ይወሰዳል

በጁንታው የተዘረፉ መሬቶችን በመሸጥ ለሽብር ተግባር የገንዘብ ምንጭነት በሚያውሉ ላይ እርምጃ ይወሰዳል- የጋምቤላ ክልል መንግስት

በጋምቤላ ክልል በጁንታው ቡድን የተዘረፉ መሬቶችን በመሸጥ ለሽብር ወንጀል የገንዘብ ምንጭነት ለማዋል በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በወቅቱ እንደገለጹት አሸባሪው የህወሐት ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት በህዝብ ላይ ከፈጸመው ግፍና በደል በተጨማሪ በርካታ የከተማና የገጠር መሬቶችን ዘርፏል።
“ቡድኑ የዘረፋቸውን መሬቶች በአካባቢው በሚገኙ ርዝራዦች አማካኝነት በመሸጥ ሀብት የማሸሽና ለሽብር ወንጀል የገንዘብ ምንጭነት ለማዋል ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ተደርሶበታል” ብለዋል።
ቡድኑ ካሁን በፊት በዜጎች ላይ ሲያደርስ የቆየው ግፍና በደል ሳያንሰው ሀገርን ለማፍረስ እያደረገ ላለው ሴራ ከክልሉ የተዘረፈው ሃብት ለቡድኑ የወንጅል ማስፈጸሚያ የገንዘብ ምንጭ እንደማይሆን አስገንዝበዋል።
እንደ ርእሰ መስተዳደሩ ገለጻ በአካባቢው የሚገኙ የቡድኑ ርዝራዦች ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል።
በክልሉ በገጠርም ሆነ በከተማ የተዘረፉ መሬቶችና ንብረቶችን ሲሸጥም ሆነ ሲገዛ የተገኘ አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊ አመራሮች መካከል አቶ ኮንግ ጆክ በሰጡት አስተያየት “የጁንታው ቡድኖች በስመ ኢንቨስትመንት መሬት መዝረፋቸው ሳያንሳቸው ሀብቱን ሀገር ለማፍረስ ለሽብር ወንጀል ሊያውሉት አይገባም” ብለዋል።
በአሸባሪው ቡድን ርዝራዥዎች ላይ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አመልክተዋል።
ከአሁን በፊት በጋምቤላ ከተማ የጁንታው ቡድን ሆቴሎች ለሽብር ቡድኑ የገንዘብ ምንጭ ሆነዋል በሚል ተዘግተው ባልታወቀ ምክንያት እንደገና እንዲከፈቱ መደረጉ ተገቢ ያለመሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌለው አመራር አቶ ኡቲያን ኡቻን ናችው።
አቶ ኡቲያን አክለው ካሁን በፊት የተዘረፉ የከተማና የገጠር መሬቶችን በመሸጥ ሃብት ለማሸሽ በሚሞክሩ አካላት ላይ ምን እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየት አቅርበዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ለተነሳው ጥያቄ አዘል አስተያየት በሰጡት ምላሽ “የክልሉ መንግስት በማያውቀው ሁኔታ ተከፍተው የነበሩ ሆቴሎች እንደገና እንዲዘጉ ተደርጓል” ብለዋል።
ከአሁን በፊት የተሸጡ መሬቶችና ንብረቶች ካሉም በሻጭም ሆነ በገዥው አካል ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል። (ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top