Connect with us

ህዉሀት ቅዠቱ አንድነታችንን ለመበተን ነው- ሊሳካለት ግን አይችልም

Social media

ነፃ ሃሳብ

ህዉሀት ቅዠቱ አንድነታችንን ለመበተን ነው- ሊሳካለት ግን አይችልም

ህዉሀት ቅዠቱ አንድነታችንን ለመበተን ነው- ሊሳካለት ግን አይችልም
(ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ )

ኢትዮጵያ ሕብረ ብሄራዊት አገር ናት ፡፡ መልከ ብዙ ፤ ቀለመ ዠንጉርጉር ፡፡የባህል ፣ የእምነት ፣ የቋንቋ፣ የመልክአ ምድር ብዝሀነትን የተላበሰች ምድር ፡፡ የሰው ልጅ በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘባትና የኖረባት ነች ፡፡
ኢትዮጵያ ከፊት ዘመን ጀምሮ በድህነት፣ በጉስቁልና በእርስ በእርስ ጦርነት ዉስጥ ዘመናትን ብታልፍም ፤ ህዝቦቿ የሚተባባሩበትና አንድ የሚሆኑበት አገራዊ እሴትም ነበራቸዉ/አላቸዉ ፡፡
በተለይ ከውጭ ወራሪዎች ጋር በየዘመኑ ጦርነት እየገጠመች በመጡበት እየመለሰች ነጻነትዋን አስከብራ እንድትኖር ያደረጎት በየዘመኑ የነበሩ ጀግኖች ልጆቾ ነበሩ፡፡
ዘር ፣ቀለምና ሃይማኖት ሳይለያያቸዉ ለዘመናት ሲፋለሙ የነበሩ አያት ቅድመ አያቶቻችን ፤ሌሎች በባርነት ቀንበር ሲማቅቁ እኛ በነፃነትና በኩራት የምንኖርባት ፣የሉአላዊነት ምሳሌና አርአያ ሁና የኖረች አገር ባለቤት አድርገዉን ነበር ያለፉት ፡፡
የአሁኑ ትውልድ አገሩን ከየትኛውም ጥቃት ለመጠበቅ የሚከፍለው መስዋእትነት የሚታዬውም እንደዚሁ ነው ፡፡
ህወሀት መራሹ መንግስት ወደስልጣን ከመጣ ያለፉት 30 አመታት ወዲህ ግን ይህን የጋራ መስተጋብር የሚበጥስና አብሮነትን የሚንድ በርካታ ተግባራት ተፈፅመዋል ፡፡
ስርአታዊና ህገመንግስታዊ መሰረት በማስያዝ ፣የተጨቆኑ ማንነቶችን እውቅና ለመስጠት በሚል ሽፋን ኢትዮጵያዊነት እንዲፈርስ ቀላል የማይባል ዘመቻ ተከናውኗል ፡፡ለአገር ክብርና ለህዝቦች አንድነት የተጋሉ ብዙዎቸች ተገድለዋ ፣ተሰደው አገር አልባ ሆነዋል ፡፡ …
በአገርና ህዝብ ላይ ይሄ ሁሉ መአት ቢወርድ፣ ያ ሁሉ የታሪክ መዛባት ቢጀምርና የሴራ ፖለቲካ አገሩን ቢፈትነውም ፣ የተሳሰረው አገራዊ ህብረታችንን መበጣጣስ የቻለ አልነበረም ፡፡ ሁሉ ነገር በቋፍ በሆነበት ጊዜ በአገራችን አዲስ የለውጥ ጅምርና የመደመር ቀንዲል መለኮሱ ደግሞ አዲስ ተስፋ አጭሮ ነበር ፡፡
በሂደቱ ግን ባለፉት ሶስት አመታት ፣ በተለይም ከስምንት ወራት ወዲህ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይን ሲያስተዳዳር በነበረው ያው ጠንከኛ ቡድን ለኳሽነት ጦርነት መቀስቀሱና ደም ለማቃበት መሞከሩ ዳግም ፈተናውን አክብዶታል ፡፡ይህ አደገኛ ሃይል ራሱን ወደጁንታነት ቀይሮ ስረአተ መንግስቱን ለማፍረስ ቢሞክርም ፣ ራሱንም ሆነ የወጣበትን ማህበረሰብ ለከፋ ችግር ማጋለጡም አልቀረም ፡፡
ይህ መሆኑ አንሶ አሁንም ጁንታዉ አካባቢው እንዳይረጋጋ፣ ቀውሱ እንዳይቆም ህዝቡም መከራ በዛብኝ ብሎ በአገረ መንግስቱ ላይ ይበልጥ እንዲማረር እየሰራ ነው ፡፡
ከዚያም አልፎ በውሸት ፕሮፖጋንዳና በውዥንብር አለምን በማሳሳት የውጭ ሃይሎች በአገር ላይ ጫና እንዲያደርሱ በተቀናጀ መንገድ እየኮተነ ይገኛል ፡፡ በዚሁ የበአዳን ግፊትና ሴራ አገርን የማንበርከክ ምኞቱ ቢሳካም በጋራ እንበደል እንደሁ እንጂ፣ መፍትሄ ማግኘት የሚቻል አይደለም ፡፡
በመሰረቱ እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድ መገንዘብ ያለብን ቁምነገር ማንም ይሁን ማን ህግን ጥሶ ፣ በእብሪት ስርአትን ገርስሶ እንዲኖር አለመፍቀድን ነው ፡፡አንድነታችንም ሆነ ሰላማችን ሊጠበቅ የሚችለውም በመነጋጋርና በመደማማጥ ብሎም በህግና ስረአት መብታችንንና ግዴታችንን ማስከበር ስንችል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ለየትኛውም ጫና ሳንበረከክ የጉዞችንን እንቅፋት ለመጥረግ መረባረብ አለብን ፡፡
የግድም ነው!!
አንድነታችንንና አገራዊ ህልውናችንን እየፈተነ ያለው ህወሀትም እንደዋነና እንቅፋት መቆጠር አለበት፡፡
በቀዳሚነት ግን ራሱ የትግራይ ህዝብ እውነቱን ተረድቶ ፣ ከፅንፈኛው ኃይል መነጠልና ከምልአተ ህዝቡ ጋር በመወገን በአንድነትና በነፃነት የሚኖርበትን እድል መፍጠር ነው ያለበት ፡፡
ለሁላችንም ተከባብሮና ተደማምጦ በእኩልነት ከመኖር የዘለለ እድል ሊኖረን እንደማይችልም መገንዘብ ያስፈልጋል ፡፡ ከዚያ ውጭ አሁን ህገወጥ ቡድኑ የአገርን ህልውና በማጥቃቱ የሚወሰድበትን እርምጃ ህዝቡን ለመጥቃት ነው የሚለው ውዥንብር ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም ፡፡
ንፁሃንን ይዞ ለመሞት የሚያደረገው ሴራ አካል መሆኑንም ተረድቶ ሚናን መለየት ለሁሉም ይበጃል !!
በአጠቃላይ ፅንፈኛው የህወሀት ቡድን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝብን ከህዝብ እየነጠለ፣በዘረፋና በውንብድና ለመኖር የሚመኝ መሆኑ ተደጋግሞ ተጋልጧል ፡፡
ከአመፅና ጉልበት እንዲቆጠብ ሲለመን አሻፈረኝ በማለቱ ነው ይሄ ሁሉ መአትም የወረደበት ፡፡ ስለሆነም አብሮነታችንን ሳያፈርስ፣ የጋራ ህልውናችንን ሳያውክ ቅዠቱን በጋራ ትግላችን ለማክሸፍ መረባረብ ግድ ይለናል ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top