Connect with us

የክልል የልዩ ሀይል አባላት ህወሓትን ለመደምሰስ መዝመታቸውን ቀጥለዋል

social media

ነፃ ሃሳብ

የክልል የልዩ ሀይል አባላት ህወሓትን ለመደምሰስ መዝመታቸውን ቀጥለዋል

የክልል የልዩ ሀይል አባላት ህወሓትን ለመደምሰስ መዝመታቸውን ቀጥለዋል

የድሬደዋ ፖሊስ፣ የሐረሪ፣ የሶማሌ፣የአፋር፣ የጋምቤላ ክልሎች ልዩ ሀይል አባላት የህወሓትን ጥቃት ለመመከት ወደግንባር ተንቀሳቅሰዋል።

ቀደም ሲልም የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የሲዳማ ክልሎች ልዩ ሀይሎች በተመሳሳይ ሁኔታ መዝመታቸው የሚታወስ ነው።
***
ትህነግን በትብብር መደምሰስ ለምን አስፈለገ

አሸባሪው ትህነግ የአማራ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን ቀንደኛ ጠላት ነው፡፡ ለዚህም ማሳያው ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተወጣጡ የልዩ ሃይል አባላት ትህነግን ለመፋለም ወደ ግንባር መዝመታቸው የትህነግን የጋራ ጠላትነት ዋነኛ ማረጋገጫ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ትህነግ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ጠላት ነው የሚባልባቸው ዋና ዋና ምክንያች የሚከተሉት ናቸው፡-

~ የመላው ኢትዮጵያውያን አርማ የሆነውን የአገር መከላከያ ሠራዊት (የሰሜን ዕዝ) በክህደት አጥቅቷል፤

~ ትህነግ ህገ መንግስቱን በተደጋጋሚ ጥሷል፡፡ ህገ መንግስቱን መጠበቅ፣ ማክበርና ማስከበር ደግሞ የመላው ኢትዮጵያውን የጋራ ሀላፊነት እንጂ የአንድ ክልል ብቻ አይደለም፡፡

~ ትህነግ በአሸባሪነት ተፈርጇል፡፡ ስለሆነም የመላው ኢትዮጵያውያን ጠላት እንጂ የአንድ አካባቢ ብቻ ጠላት አይደለም፡፡

~ አሸባሪው ትህነግ በተለያየ መልኩ በእጁ የገቡትን የአገር መከላከያ ሠራዊት አዋርዷል፤ ደብድቧል፡፡ ይህ ግፍ የተፈፀመባቸው ወታደሮች ደግሞ የመላው ኢትዮጰያውያን ልጆች ናቸው፡፡ በመሆኑም ትህነግ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ጠላት ነው፡፡

የትህነግን የጋራ ጠላትነት የበለጠ የሚያረጋግጠው በዚህ ሁለት ቀን ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተወጣጡ የልዩ ሃይል አባላት በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የትህነግን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ወደ ሰሜኑ የአገራችን ክፍል መዝመታቸው ነው፡፡
ይህ የሆነው የጋራ የሆነውን ጠላት አሸባሪው ትህነግን በጋራ ታግሎ መደምሰስ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ እንጂ የአማራ ክልልን ለማገዝ በሚል እሳቤ ብቻ የተከናወነ ተግባር አይደለም፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top