Connect with us

” የአማራ ክልል መንግሥት፤ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይተባበራል እንጅ እንቅፋት አይሆንም”

" የአማራ ክልል መንግሥት፤ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይተባበራል እንጅ እንቅፋት የመሆን ፍላጎት የለውም"
አሚኮ

ዜና

” የአማራ ክልል መንግሥት፤ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይተባበራል እንጅ እንቅፋት አይሆንም”

” የአማራ ክልል መንግሥት፤ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይተባበራል እንጅ እንቅፋት የመሆን ፍላጎት የለውም”

~ የአማራ ክልል መንግሥት

አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎችና የማኅበረሰብ አንቂዎች የአማራ ክልል መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ  እንዳይገባ እያደረገ ነው በሚል የሚያሰራጩት ዘገባ ፍፁም የክልሉን መንግሥትም ኾነ ሕዝብ የማይወክልና የመንግሥትን ባህሪይ የማይገልፅ ነው ሲል የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በጋራና በምክክር እየሠራ ያለው ነገር ቢኖር አማራ ክልልን አልፎ የሚሄድ የትኛውም የእርዳታም ይሁን የንግድ ሸቀጥ በፍተሻ ኬላዎች እየተፈተሸ  ሕጋዊና የተፈቀደ የሰብዓዊ እርዳታ ቁስ መሆኑን በማረጋገጥ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ሰብዓዊ እርዳታው እንዳይደርስ የማስተጓጎል ፍላጎት የለውም ብሏል።

ክልሉ በመግለጫው እንዳለው የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶችም ኾነ ሀገራት በሰብዓዊ እርዳታ ስም ያልተፈቀደላቸውንና ህገወጥ የሆኑ ቁሳቁሶች ለአብነትም የጦር መሳሪያ፣ አደንዛዥ እፆች፣ አውዳሚ ኬሚካሎች እና የመሳሰሉት ጠቃሚ ያልሆኑና ለማኅበረሰባችን የበለጠ ቀውስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶች ለአሸባሪው ለትህነግ ኃይል እንዳይደርስ ስጋት ስላለብንና የክልሉ መንግሥት ደግሞ የዜጎቹን ደኅንነት የመጠበቅ  ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በእርዳታ ስም የሚጓጓዘው አልሚ ምግብ፣ እህል ወይም ሌላ ቁስ በእርግጥም ትክክለኛ የሰብዓዊ እርዳታ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይፈልጋል።

ፎቶ :- ፌቡ

ከፍተሻ በመለስ ትክክለኛው የሰብዓዊ እርዳታ ከሆነ እንድያውም ደኅንነቱ ተጠብቆ እንዲደርስ በክልሉ ውስጥ እርዳታ ጭነው የሚመጡ አካላትንም ሆነ የሚጎጎዘውን እርዳታ ደኅንነቱ ተጠብቆ እንዲደርስ እያደረገ ነው የሚገኘው። ለወደፊቱም የሚያደርገው ይሄንኑ መሆኑ መታወቅ እንዳለበት ገልጿል።

በእርዳታ ስም ያልተፈቀደና በሀገሪቱ ሕግ መሰረት ለዜጎች ደኅንነት ስጋት የሆኑ የትኛውም አይነት ቁሶችን ወደ ኢትዮጵያም ኾነ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ በክልሉ አልፈውም ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች እንዳይገቡ መከላከል ያልተገደበ ሙሉ የክልሉ መንግሥት ኃላፊነት ስለሆነ የማንንም የውጭና የውስጥ ኃይል ፈቃድና ይሁንታ ሳያስፈልገን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር በጋራ ጥብቅ ፍተሻ ማድረጋችንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ከዚህ ውጭ የክልሉ መንግሥት ለምን ፍተሻ ያደርጋል በሚል በውጭ ሚዲያዎችና በማኅበረሰብ አንቂዎች በተዛባ መንገድ የአማራ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባና እርዳታ ለሚያስፈልገው የኅብረተሰብ ክፍል እንዳይደርስ እያደረገ ነው የሚለው ክስ ምን አልባትም “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው” በእርዳታ ስም ሕገወጥ የጦር መሣሪያና ሌሎች ያልተፈቀዱ ቁሶችን ለጠላት ኃይል ለአሸባሪው ትህነግ ለማድረስ ካልሆነ በቀር አይደለም ፤ አሁን ወትሮም ቢሆን የኬላ ፍተሻ የኖረና ለወደፊትም የሚኖር ነው ብሏል።

በተዛባው የውጭ ሚዲያና በአሸባሪው ሕወሓት ቅጥረኛ የማኅበራዊ ሚዲያ የሐሰት ክስ መንግሥት መደበኛ የደኅንነት ሥራውን የማያቆም እንደሆነ ደግመን ደጋግመን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን ነው ያለው።

በየትኛውም የዓለም ሀገር ቢሆን አይደለም ከውጭ የሚገባን ይቅርና አንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የሚደረግ እንቅስቃሴ በየኬላው ሳይፈተሽ የሚያልፍበት እድል የለም። ደግሞስ ትክክለኛ የሰብዓዊ እርዳታ ከሆነ ማድረስ የተፈለገው ተፈትሾ ማለፍ ለምን ተጠላ? ለምን ጩኸቱ በረከተ? የሚለውን ምላሽ መስጠት ተገቢነት ይኖረዋል ብሏል።

በአጠቃላይ የክልሉንና የሕዝቡን ለስጋት የሚጥል ነገር እንዳይኖር የጥበቃ የኬላ ፍተሻ ተጠናክሮ በዘመናዊ መሣሪያም ታግዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያለው።

ወደ ክልሉ የሚመጡና ክልሉን አልፈው ወደ ሌላ ክልል የሚያልፉ እርዳታም ይሁን ሌሎች ጤነኛና ሕጋዊ እንቅስቃሴዎችን እንተባበራለን፤ እንደግፋለን፣ ደኅንነታቸውንም እንጠብቃለን። በተቃራኒው ያልተፈቀዱ፣ ጎጅና ለአደጋ የሚያጋልጡ እንቅስቃሴዎችን ደግሞ በመከላከል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ከአደጋ መከላከል ግዴታ ስላለበት ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታውቋል። (አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top