Connect with us

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!”.. ሙሉ እንዲሆን…

"ኢትዮጵያ አሸንፋለች!".. ሙሉ እንዲሆን...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!”.. ሙሉ እንዲሆን…

“ኢትዮጵያ አሸንፋለች!”.. ሙሉ እንዲሆን…

(ነብዩ ባዬ)

በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓለቲካም ሆነ በተመራጭነት በተሳተፍኩበት ምርጫ የተወዳደርኩበት ብልፅግና ፓርቲ በብዙ አካባቢዎች ማሸነፉን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

በተለይ በተወዳደርኩበት በአዲስ አበባ ከግል ተወዳዳሪው ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በቀር ሙሉ በሙሉ ወንበሮቹ የብልፅግና ፓርቲ ሆነዋል።

ይህ አሁን ያለው የምርጫ ህግ በአንድም ድምፅ ቢሆን ሌሎቹን ለየብቻ ያሸነፈ ወንበር ያሸንፋል ለሚለው መርሁ ማሳያ እንጂ ሁሉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ድምፁን ሰጥቶናል ማለት አይደለም።

እኔ በተወዳደርኩበት በአራዳ ድምፅ ከሰጠው ከሰማንያ ሺህ ጥቂት ከፍ የሚል መራጭ ውስጥ የብልፅግና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተወዳዳሪዎች በአማካይ አርባ አርባ ሺህ አካባቢ፣ የሌሎች ስምንት ፓርቲዎች እጩዎችም በአማካይ ድምሩ ያንኑ የብልፅግናን ያህል ድምፅ ማግኘታቸውን በምርጫ ቦርድ የክልል ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ የተመለከትኩትን አስልቼ ተረድቻለሁ።

በአራዳ በግርድፍ ሂሳብ ከቀረቡለት ዘጠኝ ፓርቲዎች ግማሹ መራጭ ድምፁን ለብልፅግና ሲሰጥ የተቀረው ግማሽ ደግሞ ለስምንቱ እንደየምርጫው በተለያየ መጠን ሰጥቷል።

እርግጥ ነው ምርጫችን በኢትዮጲያዊ ጨዋነት፣ በፈጣሪ ቸርነት በሰላም ተጠናቋል።

እርግጥ ነው ከመስመር ወጥተው በብዙ ይሰራረቃሉ፣ በብዙ ይሰዳደባሉ፣በእፍርት ይሞላሉ፣ በብዙ ይጣላሉ፣ ይገዳደላሉ፣ ሀገራቸውን ያቃጥላሉ ብለው የገመቱንን ስላልሆንን ኢትዮጲያ አሸንፋለች።

የተመረጥነው ኢትዮጲያ አሸነፈች የምንለው እኛ ስለተመረጥን እንዳይመስለን እና ተመርጠን እንዳንሸነፍ መጠንቀቅ አለብን። ፈጣሪ ከዚህ ውድቀት ይጠብቀን። ኢትዮጲያ ማሸነፏ ሙሉ እንዲሆን ግን የተመረጥነው ሰዎች ሄደን የምንቀመጥበት ወንበር ድምፅ የሰጠውን ሰው ሁሉ የመወከል ግዴታ የሚጥልብን መሆኑን ማወቅ ይገባናል። 

ዝናብ፣ ፀሃይ… ብርድ፣ ሙቀት የተፈራረቀበት መራጭ ሁሉ ድምፁን ለብልፅግና ለመስጠት መስዋዕት የከፈለ እንዳልነበረ መረዳት የፍትሃዊነት መጀመሪያ ሊሆን ይገባል።

በምንገባበት ምክር ቤት አስቀድመን የዚያን ሁሉ አሸናፊውን ያልመረጠ መራጭ ድምፅ በምክር ቤቶች ድምፅ ያሳጣ የምርጫ ህግ እንዲቀየር መቆም አለብን። የመረጠንም ያልመረጠንም ተወካይ ሆነናልናም የሁሉም ተወካይ የመሆን ሃላፊነትን በፈጣሪ ፊት መሸከም አለብን።

ለሁሉም ሃላፊነት ፈጣሪ ይርዳን።

ለምርጫ የተወዳደርኩበት ፎቶ እንደፊርማ ተያይዟል።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top