Connect with us

ህወሀትማ  ከባዱን ኪሳራ ተጎንጭቷል፣ የትግራይ ህዝብንም ለመከራ ዳርጎታል !!

ህወሀትማ ከባዱን ኪሳራ ተጎንጭቷል፣ የትግራይ ህዝብንም ለመከራ ዳርጎታል !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ህወሀትማ  ከባዱን ኪሳራ ተጎንጭቷል፣ የትግራይ ህዝብንም ለመከራ ዳርጎታል !!

ህወሀትማ  ከባዱን ኪሳራ ተጎንጭቷል፣ የትግራይ ህዝብንም ለመከራ ዳርጎታል !!

( ገለታ ገ/ወልድ – ድሬ ቲዩብ )   

ህውሀት መራሹ የአመፅና የሴራ ፖለቲካ አቡኪ ቡድን ፣ በጁንታ መልክ በሴራ ተደራጅቶ ሰራዊቱን በመበታተን አገር ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ አልተሳካላትም  ፡፡ ስብስቡ ለዘመናት የህዝብ ሀብት እየዘረፈና ንፁሃንን እየፈጀ ያሳበጠው እብሪትና ድንቁርና በከፋ ሽንፈትና ውርደት ተኮማትሯል ሊባል ይችላል ፡፡ ግን አስተሳሳቡ ሙሉ በሙሉ ያልተሸነፈ ብቻ ሳይሆን ፣ በሽፍታ መልክ መዋጋቱ እንዳልቆመ እየታዬ ነው ፡፡

   እኔ ግን ህወሀትና ደጋፊዎቹ የደረሰባቸው ኪሳራ ከባድና በቀላሉ ሊወራረድ የማይችል ነው ስል ለመሞገት ያህል አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳት እወዳለሁ፡፡

1ኛ – ህወሀት በቀላሉ እንደዋለሁ ብሎ የአገሪቱን ብሄራዊ ጦር መውጋቱና መሳሪያውን መዝረፉ ፣ይበልጥ ከምልአተ ህዝቡ ጋር አጋጭቶታል ፡፡ በተለይ ደግሞ ከአማራና ከኤርትራ ህዝብ ደም አቃብቶታል ፡፡ ጁንታዉ  “ጠላቴ” የሚለው የአገሪቱን አመራር ቢሆንም፣ ህዝቡም እንደህዝብ  ያወገዘው ፣ አጥፊ ብሎ የፈረጀው ጉድ ሆኗል ፡፡

2ኛ- ህወሀት በጦርነቱ በደንብ ለመሸነፉ፣ ታጣቂው  በመማረኩ፣ በመበተኑና ተጠራርጎ ጫካ በመግባቱ ብቻ አልነበረም ፡፡ የሴራ ፖለቲካ  ቁንጮ የነበሩት እነአቦይ ስብሀት በሚያሳፍር ሁኔታ ከየዋሻ ውስጥ እየወጡ በፈፀሙት ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል ፡፡ እነስዩም ፣አባይ ፣አስመላሽ፣ዘርአይን …የመሰሉ ነበር ፖለቲከኞች ፣በመቶዎች የሚቆጠሩ መካካለኛና ከፍተኛ የጦር መኮንኖቻቸውን አስገድለዋል ፡፡ በየበረሃው ከስራ ተናጥቦ የሚንከራተተውና የተሰደደው ተጋሩም የህወሀት ኪሳራ ማሳያ ነው !!

3ኛ – ጁንታው የትግራይን ህዝብ ክፉኛ የበደለው በክልሉ ይነሳ የነበረውን የወሰንና የማንነት ጥያቄ በህግ ከመመለስ ይልቅ በጦርነት ለማስከበር በመፈለጉ ነው ፡፡ በዚህም ዛሬ ራያ፣ ወልቃይት፣ ባድመና ዛላምበሳ አካባቢ ለዘመናት የቆዩ ተጋሩዎች ተፈናቅለዋል ፤ ለፍተውም፣ ሰርቀውም ያፈሩትን ሐብት አጥተዋል ፡፡ ትግራይም እንደክልል አወዛጋቢዎቹን አካባቢዎች ተነጥቃለች ፡፡ ቢያንስ ደግሞ የፍጥጫና የውዝግብ ቀጠና ፈጥሯል ፡፡

4ኛ- አሳዛኝ ቢሆንም ጁንታው በለኮሰው ጦርነት የትግራይ ህዝብ የገጠመው መከራና አሳር ብቻ ሳይሆን መፋናቀል ፣ መዘረፍና የህሊና መረበሽ ከ40 ዓመት ወዲህ የመጀመሪያው ነው ፡፡ በማንም ይሁን በማን ብዙ ሴቶች ተደፍረዋል ፣ በጦርነቱ የሞቱና የቆሰሉ ብቻ ሳይሆን ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ትንሽ አይደሉም ፡፡ ብዙዎቹ ፋብሪካዎች በመውደማቸው ሰራተኞች ተበትነዋል ፡፡ በህወሀት ጫናም ሆነ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ነፍጥ አንግተው ከጁንታው ጋር የሚንከራተቱትም ከስራ ውጭ መሆናቸውን ልብ ይሏል ፡፡

5ኛ- ጁንታው እንደቡድን ለ30 ዓመታት ያካበተው ከፍተኛ ሀብት ( ኤፍርትን ልብ ይሏል) ከነትርፉም ሆነ እዳው አጥቷታል ፡፡በጊዜዊ ቦርድም ይባል በመንግስት ይተዳዳር በቢሊዮን የሚቆጠረው ከፍተኛ የህዝብ ሀብት ለአገር ጥቅም የሚውልበት እድል ተከፍቷል ፡፡ በግል ደረጃም በርካታ በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ህንፃዎች፣ መኖሪያ ቪላዎችና ኩባንያዎች በህግ ታግደዋል ፡፡ አሁንም በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የጁንታው ደጋፊዎች በአገር ውስጥ ያሻቸውን እየሰሩ ፣በእጅ አዙር ጁንታዉን እንደሚደገፉ ተረጋግጧል ፡፡ ካስፈለገም መንግስት እርምጃ ከመውሰድ ከልካይ አይኖረውም ፡፡

6ኛ- በሌሎች  የአገሪቱ አካባቢዎችና ከተሞች  ከሌላው ወገኑ ጋር በነፃነትና በመከባባር  ለዘመናት የኖረው ተጋሩ ያጋጠመው የመጠርጠርና መጋፋት ስሜትን የፈጠረውም ይሄው ቅብጥብጥ ቡድን ነው፡፡ንፁሀኑ በሰላም ሰርቶ መኖር ሲገባውና በውስጡም የማያርፉ አንዳንድ የጁንታው ደጋፊዎችም ስላለ በአይነ ቁራኛ የሚታዩ ሆነዋል ፡፡ 

እንደልብ ሰርቶ ለመኖር መገለል የገጠመውም ትንሽ አይደለም ፡፡ ለዚህ ማሳዬው አዲስ አባባን ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ ፎቆችና ቪላዎች ሰው አልባ ሆነው መታዬታቸው ነው፡፡

7ኛ- ጁንታው አሁን ላይ የትግራይ ክልልን ለቆ በወታደራው ብሄራዊ ጦርና በመንግስት የተኩስ አቁም እርምጃ ምክነያት፣ በየትኛውም ውጊያ እንደሚያጋጥመው የተማረኩ ወታደሮችን እያሳዬ ድል ማድረጉን እየተናገረ ነው ፡፡ አሁንም ግን ክልሉ በቂ መሰረተልማት ያልተለቀቀለት ፣ በፈራረሰ የአስተዳዳርና በወደመ ማህበራዊ ልማት ውስጥ ነው ፡፡ 

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ምንዱባን መላኩን ባይተውም ፣ መንግስት ድጋፉን ለመቀጠል ፣የቀደመው ትጋት የለውም ፤፤ እንዳውም ከዚህ በሆላ ክልሉን ህወሀት ነው የሚመለከተው ብሏል ፡፡ ይሄ ደግሞ በሌላው ተከሸ ታዝሎ ለኖረው ክልል ከፍተና ጫና ይፈጥራል ፡፡

8ኛ- በተቃራኒው የአገሪቱ መንግስት ጁንታው ውጊያ ከጀመረ በሆላ በወታደራዊው  መስክ ያደረገውን አድርጎ ይነስም ይብዛም በአገር ውስጥ ልማቶች አከናውኗል ፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን አስተክሏል ፣ ምርጫ በተሳካ መንገድ አጠናቋል ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ሁለተኛ ዙር ሙሊት ከመሙላት ባሻገር፣ በካይሮና ሱዳን የዲፕሎማሲ ውዝግብ አለም አቀፍ አሸናፊ ሆኗል ፡፡ …

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top