Connect with us

“እረኛዬ” ድራማ በልባችን እንዲቀር በጆሮአችን እንድናየው ያደረገን የማጀቢያ ሙዚቃ ፈጣሪው ታደለ ፈለቀ፤

"እረኛዬ" ድራማ በልባችን እንዲቀር በጆሮአችን እንድናየው ያደረገን የማጀቢያ ሙዚቃ ፈጣሪው ታደለ ፈለቀ፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“እረኛዬ” ድራማ በልባችን እንዲቀር በጆሮአችን እንድናየው ያደረገን የማጀቢያ ሙዚቃ ፈጣሪው ታደለ ፈለቀ፤

“እረኛዬ” ድራማ በልባችን እንዲቀር በጆሮአችን እንድናየው ያደረገን የማጀቢያ ሙዚቃ ፈጣሪው ታደለ ፈለቀ፤

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬቲዩብ)

እረኛዬ በፍቅር የጣለን በተዋጣ ጥበብ የተሳካ ሥራ ስለሆነ ነው፡፡ ገጸ ባህርያቱን የሚመስሉ ተዋናዮች ድንቅ ብቃታቸው አሳይተውበታል፡፡ የሲኒማ ባለሙያዎች አቅም ፍንትው ብሎ የታየበት ድራማ ነው፡፡

እረኛዬን ሳስብ ሁሌም ወደ ልቤ የሚመጣው ያ ድምጽ ነው፡፡ 

ያ ልዩ ማጀቢያ ሙዚቃ፡፡ ሙዚቃው ሥፍራውን፣ ታሪኩን፣ ገጸ ባህርያቱንና መቼነቱን መልሰን እንድናስታውስ፣ ከገባንበት ምሳጤ እንዳንወጣ የሚያደርግ ነው፡፡

ታደለ ፈለቀ ከዚህ ቀደም በወደድኳቸው የቴሌቨዥን ድራማዎች ያወቅሁት የሙዚቃ አቀናባሪ ነው፡፡ ድራማውን በጆሮ እንዲታይ የማድረግ አቅም እንዳለው አስመስክሯል፡፡ እረኛዬ ያንን ከሚመሰክሩ ስራዎቹ አንዱ ነው፡፡

የእረኛዬን መወደድ ተከትሎ ልባችንን የሰረቀው ስፍራ የቱ ነው? ብለን ብንፈልግ በየሙያውና በየዘርፉ የተዋጣው ክህሎት እንደሆነ እንረዳዋለን፡፡ ካሜራ ባለሙያዎቹን እናደንቃለን፡፡ ድርሰቱን ወዝ የሰጡ የአደባባይ ጀርባ ጥበበኞችን እናመሰግናለን፡፡ ከዚያ ድርሻ አንዱ የሙዚቃ አቀናባሪው የታደለ ፈለቀ ማጀቢያ ሙዚቃ ነው፡፡

ማጀቢያ ሙዚቃው የሆነውን እንዳንረሳ ያደርገናል፤ ድምጾቹ ከመንደሯ ጋር አንዳች ቁርኝት እንዲኖረን አድርገዋል፡፡ ስጋት ደስታ ሰቀቀን ናፍቆትን አጅበዋል፡፡ በዚያ ሁሉ ህይወት ውስጥ ሀገረሰባዊ ለዛ ያለው ሙዚቃን ከድራማው ጀርባ እናደምጥ ነበር፡፡

ከዚህ ቀደም እንደ ሞጋቾች ያሉ ድራማዎች ላይ ብቃቱን ያሳየን ታደለ ስፍራን ስሜትንና ጉዳይን አዛምዶ ማጋመድ የሚችል ሰው መሆኑን አስመስክሯል፡፡

ዛሬ ማንም ሰው ገና ያንን መስክ ላይ የሚጋልብ ምስል ያጀበ ሙዚቃ በጆሮው ብቻ ቢሰማ የተመለከተውን መልሶ በምናቡ የሚያስታውስበትን ጉልበት የያዘ ሙዚቃ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ እረኛዬ ክፍል አንድ እና ሁለት ላይ የተመለከትናቸው ሀዘንና ደስታ የተፈራረቁበት መሳጭ ድምጽ ታላቅ ድርሰት እንደሆነ መረዳት አይከብድም፡፡

ያ ሙዚቃና ያ ማጀቢያ ወደ ሆነ ስፍራ ተመልካችን ይዞ ሄዶ የድራማው መቼት መንደር ነዋሪ የሚያደርግ ጥበብ አለው፡፡ ደግሜ እላለሁ፤ እረኛዬን በጆሮአችን እንድንሰማ ያደረገን ጥበበኛው ከያኒ ታደለ ፈለቀ እጅህ ይባረክ ብለነዋል፡፡  

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top