Connect with us

“የአማራ ክልልን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል” አቶ አገኘሁ ተሻገር 

"የአማራ ክልልን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል" አቶ አገኘሁ ተሻገር
አሚኮ

ዜና

“የአማራ ክልልን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል” አቶ አገኘሁ ተሻገር 

“የአማራ ክልልን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል” አቶ አገኘሁ ተሻገር 

 የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም የአማራ ሕዝብ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን መሥራቱንም ገልጸዋል። 

የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል የወሰነው ውሳኔ በክልሉ መንግሥት እንደሚደገፍም አስታውቀዋል። 

የአማራ ሕዝብና መንግሥት ለመከላከያ  ደጀን መሆኑን አሳይቷል ፤ እያሳየም ይገኛል። ይህን አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት። 

ክልሉን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገን እየሠራን ነውም ብለዋል። 

የሕግ ማስከበር ዘመቻው ለአሸባሪው ትህነግ ዋጋውን የሠጠና የደመሰሰ ነውም ብለዋል። አሸባሪው ትህነግ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ አያደርስምም ነው ያሉት። የአሸባሪው ትህነግ ዓላማ የተዳከመ የመከላከያ ሠራዊት እንዲፈጠር ማድረግ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ለወራት የዘለቀው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል የተጠናቀቀ ነውም ብለዋል። መንግሥት በአሸናፊነት ላይ ኾኖ ያወጀው የተኩስ አቁም መሆኑን አስታውቀዋል። 

ርእሰ መሥተዳድሩ የአሸባሪው ትህነግ ቡድን የቻለውን በደል ኹሉ በአማራ ሕዝብ ላይ ፈፅሟል ነው ያሉት። ደብቆት የነበረውን የአማራ ሕዝብ ጠላትነት አሁን በይፋ ሲያወጣው መገረም እንደማይገባም ተናግረዋል። 

የአማራ ሕዝብና የጸጥታ ኃይሉ የአሸባሪውን ትህነግ ተስፋፊነት መግታቱን አስታውቀዋል። 

አሸባሪው ትህነግ ሂሳብ የሚያወራርድበት እና ቆሞ የሚጠብቅ ሕዝብ የለም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ እኛ በማንም ሕዝብ ላይ ሂሳብ አናወራርድም፤ እናወራርዳለን ብለን አልተነሳምን፣ የሚመጣ ካለ ግን ዝግጁ ነን ብለዋል። 

ከአሸባሪው ትህነግ የሚመጣውን ጥቃት ለመመከት ብቃትም ችሎታውም አለን ነው ያሉት። 

የአማራ ሕዝብ በሥነ ልቦና ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ ወጣቱ፣ ሚሊሻውና ልዩ ኃይሉ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል። 

ክልሉ አሁን ላይ መደበኛ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። 

(አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top