Connect with us

 የአረብ ሊግ ሴራ ለግብፅ የሚያስገኘው ፋይዳ የለም፣ አይኖርም !!

የአረብ ሊግ ሴራ ለግብፅ የሚያስገኘው ፋይዳ የለም፣ አይኖርም !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

 የአረብ ሊግ ሴራ ለግብፅ የሚያስገኘው ፋይዳ የለም፣ አይኖርም !!

 የአረብ ሊግ ሴራ ለግብፅ የሚያስገኘው ፋይዳ የለም፣ አይኖርም !!

(ንጉሥ ወዳጅነው – ድሬቲዩብ )   

 ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሲጀምር በናይል ተፋሰስ አገሮች ስምምነት መነሻ ነው ፡፡ ግን የስምምነት ማእቀፉን ሁሉም እንዳላፀደቁት ይታወቅ ነበር ፡፡ ያም ሆኖ ጉዳዩ የምእራባዊያን ወይም የአረብ ሊግ ስላልሆነ አገራችን ከየትኛዎቹም የግብፅ መንግስታት መሪዎች፤ የዉሃ ሚኒስትሮች ፣የዉጭ ጉዳይ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በርካታ ምክክሮችን ስታደርግ ቆይታለች ፡፡

 በዚህም ሞቅ ቀዝቀዙ ፣ መደማመጥና ስብሰባ ረግጦ መውጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለፉት 10 ዓመታት ገደማ ለ31 ጊዜ የሶስቱ ሀገሮች ( ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብፅ) ሙያተኛና ፖለቲከኞች የተሳተፉባቸዉ የድርድር መድረኮች ተካሄደዋል ፡፡ እንደ አፍሪካ ህብረት፣የአሜሪካ መንግስትና መሰል አካላት የተገኙባቸው ውይይቶችም ከ5 ጊዜ በላይ ተካሄደዋል ፡፡ 

በናይል ተፋሰስ የውሃ አጠቃቀም ስምምነት ላይም ሆነ ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት ከጀመረች ወዲህ ፣ በሚካሄዱ ምክክሮች ላይ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብጽ ብቻ ሳይሆኑ አረብሊግን የመሰሉ ሶስተኛ አካላት እጃቸውን ለማስገባት መሞከራቸውም አልቀረም ፡፡ ለነገሩ በሊጉ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ግብፃዊያንም በመካካለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ ናይል አጀንዳ እንዲሆን ሲጥሩ ኖረዋል ፡፡

ለአብነት ያህል  ግብፃዊያን ከእስራኤል ጋር የሠላም ስምምነት በፈረሙበት ወቅት ፣የሳዳት አስተዳደር የዓባይ ጉዳይ እንደ አንድ መሰረታዊ የጋራ አጀንዳ አንስቶት እንደነበር አይዘነጋም ፡፡ የግብጽ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በፍልስጤሞች ነጻነት ሳይሆን በአባይ ውኃ በመሆኑ በዚሁ ጉዳይ ላይ ማተኮሩ  ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን በመወትዎትም የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ተጠቅመውበት ነበር ፡፡ 

 ሰሞኑን እየተከታተልን እንዳለነውም የአረብ ሊግ ሰዎች የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንዳታካሂድ ክልከላ እንዲያደርግ ጫና ለማሳደር እየተሯሯጡ ነው ፡፡ የአረብ ሊግ ግብፅና ሱዳን ቅሬታቸው ሰሚ እንዲያገኝ ጫና ለመፍጠር አራት የአረብ ሃገራትን በአባልነት ያቀፈ ኮሚቴ አቋቋሞ የፀጥታው ምክር ቤትን ሲወተወተ ቆይቷል ። 

ለቀጣዩ ስብሰባም የድምፅ ሂሳብ እየሰሩ ነው ።ግብፅና ሱዳን አምና ተመሳሳይ ክስ ለመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አቅርበው ፣ጉዳዩን አህጉራዊው ተቋም የአፍሪካ ህብረት ተመልክቶ መቋጫ ይስጠው የሚል ውሳኔ ተላልፎ ነበር ። በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለው ድርድር ሳይጠናቀቅ ግን ይኸው በአመቱ ሀገራቱ ፣ በአረብሊግ ጋሻ ጃግሪነት ፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ያልተቋረጠ ሩጫ ላይ ናቸው ። 

በመንግስቱ ድርጅት የአረብ ሊግ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር መጅድ አብዱልፈታ ሰሞኑን ከግብፁ ሳድ አልበዳድ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ የቋጠሩት ተንኮል አንዱ የሩጫው ማሳያ ነው ። እንዲህ ነው ያሉት ” አምና የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለውይይት በቀረበበት ጊዜ በፀጥታው ምክር ቤት አባል የነበሩት ጀርመን እና ቤልጂየም ጊዜያቸውን አጠናቀው  በአርላንድና በኖርዌ ተተክተዋል። እነኚህ ሁለት ሃገራት ህዳሴ ግድብ በግብፅ እና ሱዳን ላይ የደቀነውን አደጋ ከጀርመን እና ቤልጂየም በላይ የተገነዘቡ ናቸው። ስለዚህም የእኛን ስጋት ታሳቢ ያደረገ እገዛ ይኖራቸዋል ” ።

 አምባሳደር መጅድ አብዱልፈታ በዚህ ሳያበቁ ተከታዩንም አክለዋል ” በተጨማሪም ኬንያ ደቡብ አፍሪካን ተክታ ዘንድሮ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ናት ። ደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቆርቋሪነት ስታሳይ የነበረች ሃገር ናት፤ አምና የአፍሪካ ህብረት ኘሬዝዳንት በሆነችበት አመትም ለኢትዮጵያ ስትወግን እንደነበር አይተናል። ኬንያ ግን ይህ ነው የሚባል ወገንተኝነት የላትም። ሌላኛዋ አባል ኒጀር የህዳሴ ግብድ የሚያሳስባት ሃገር ናት ። “

 እንዲህ ያለ ከመርህ የወጣና በስሌት የሚካሄድ የሴራ ፖለቲካ የተለመደ ቢመስልም አረብ ሊግ በዚህ ደረጃ ወርዶ ፣ ፍርደ ገምድል አካሄድ ሲከተል ማዬት የሚያስፈር ነው ፡፡  ይህ ግብፅ እና ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሃገራት ድምፅን ለማግኘት መርህን ሳይሆን ወዳጅነት ተሳቢ ያደረገ ሴራ ግን አገራችን የያዘችውን እውነትና ፍትህ ሊረታ አይችልም ፡፡ ፈጣሪና ሚዛናዊ ምልከታ ያላቸው አገሮችም ከእኛጋር እንደሚሆኑ ጥርጥር ለውም ፡፡ ሴራዉ የከሸፈ ነውና !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top