Connect with us

በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ

መንግስት በትግራይ ክልል የወሰነው የተናጠል የተኩስ አቁም በክልሉ ተጨማሪ ጥፋት እንዳይከሰት በማሰብ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
Photo: Social media

ዜና

በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ

መንግስት በትግራይ ክልል የወሰነው የተናጠል የተኩስ አቁም በክልሉ ተጨማሪ ጥፋት እንዳይከሰት በማሰብ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአለም አቀፍ ዲፕሎማት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት በትግራይ ክልል ያሳለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ተከትሎ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለተለያዩ አገራት አምባሳደሮች በአሁኑ ሰዓት ገለፃ በማድረግ ላይ ናቸዉ ።

መንግስት የወሰነው የተናጠል ተኩስ አቁም በክልሉ ተጨማሪ ጥፋት እንዳይከሰት በማሰብ እንደሆነ አቶ ደመቀ ተናግርዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ በርካታ ሀብቶች የወደሙ በመሆኑ ከዚህ በላይ በሰው ህይዎትና በአገሪቱ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጥፋትና ብክነት ለማስቀረት እንደሆነም አንስተዋል። 

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንን በተገቢው መንገድ መረዳት ይገባዋል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ከዓለም አቀፉ ማህረሰብ የሚያስፈልገን ትብብር ብቻ ሊሆን ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

መንግስት በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ከአጋር አካለት ጋር እንደሚሰራም ተነስቷል።

በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መንግስት መልሶ የገነባ ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ ግን በህወሓት ኃይል ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ መንግስት ከዚህ በላይ ሀብት ማባከን ስለሌለበት ለክልሉ ዜጎች የጥሞና ጊዜ ተሰቷል ነዉ ያሉት።

በአሁኑ ሰዓት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ከአምባሳሮቹ ጋር እየመከሩ ይገኛሉ።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top