Connect with us

የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ስለትግራይ!!

የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ስለትግራይ!!
ናትናኤል መኮንን

ነፃ ሃሳብ

የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ስለትግራይ!!

የጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ስለትግራይ!!

“የታክቲክ ለውጥ አድርገናል!”

ትላንት ማምሻውን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በምርጫው ወቅት ሚዲያዎች በነበራቸው አስተዋጽኦ ዙርያ ምስጋና ባቀረቡበት ንግግራቸው ስለ ትግራይ ተኩስ አቁም ዙርያ ሰፊ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ጠ/ሚ ዐብይ ሲናገሩ እስካሁን ለእርዳታ ብቻ ከ100 ቢሉየን ብር በላይ ወጭ ሁኗል። ይህም ለክልሉ ፌደራል መንግስት ሊሰጠው  ከሚችለው አመታዊ በጀት 10 እጥፍ በላይ ነው። በተረጅዎች አማካኝነት ርዳታው ለጁንታው እንዲደርሰው ይደረግ ነበር ሁለት ልጅ ያለው 5 ና 7 እያለ በተረጂዎቹ አማካኝነት ጁንታው እርዳታውን ያገኝ ነበር ይህም ሁሉ ዋጋ ተከፍሎ ከውስጥም ከውጭም ያሉ አካላት ማናቸውም እየተደረገ ላለው ድጋፍ እውቅና መስጠት የፈለገ የለም::

መንግስት ይህንን ሁሉ ተቋቁሞ እየሰራ የነበረ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ከውስጥ የሚደርሱበት ጫናዎች እና በመንግስት ላይ ከውጭ እየደረሱ ያሉ ጫናዎች የሚከፈለው ዋጋ ለማን ነው የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርገዋል። ምንም አቅም የሌለው ቀሪ የጁንታው አካል አዲሱ ታክቲክ እኛን አመድ እንዳደረጉን በተራዘመ ጦርነት ሀገሪቱም አብራ እንድትዳከም እና እንድትወድቅ ማድረግ ነው የሚል ነው። 

እኛም ይህን በመረዳት እየሞተ ካለ ቡድን ጋር አብሮ ላለመሞት የታክቲክ ለውጥ ማድረግ ያስፈልግ ነበር።  ሳምንት ተወያይተን የወሰነውም መከላከያው ደጀን ወደሚያገኝበት አካባቢ እንዲመጣ ህዝቡም ከስህትቱ የሚማርበት የጥሞና ጊዜ መስጠት ለአለም አቀፍ ማህበረሰቡም እውነታውን የሚረዳበት ሁኔታን መፍጠር አለብን በሚል ነው የተወሰነው።

ጦሩ ትግራይን ለቅቆ እንዲወጣ ከወሰኑ በኋላ ትናንት እስከ እኩለ ሌሊት ከብዙ የአለም መሪዎች የስልክ ጥሪ እንደደረሳቸው በተለይም ጦሩን ሲከስሱ እና ሲወቅሱ የነበሩ ሀገራት በጦሩ መውጣት መበሳጨታቸውን ተናግረዋል፡፡

ለሚዲያ ፍጆታ የማይውለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ብዙ አስገራሚ አሳዛኝ እና ለህዝቦች አብሮነት ሲባል በትዕግስት የታለፉ አናዳጅ  አዳዲስ መረጃዎች የተሰሙበት ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ገለጻ ውስጥ ግን ሁሉም ያደነቀው እና የኮራበት ነገር የመከላከያ ሰራዊቱ ጀግንነት ፣ ትዕግስት እና ያለፈባቸውን ፈታኝ ሁኔታዎችን ነው::

አንዳንዶች ተሸንፈው ነው ይላሉ፤ 80 በመቶ ወታደራዊ ትጥቅ ከመንግስታዊ ስልጣን ጋር የያዙ አካላትን በሶስት ሳምንት አሽንፈን አሁን ማንም በሌለበት እንዴት ተሸንፈን እንወጣለን? ሰው ይህን ማገናዘብ ይኖርበታል ብለዋል። በክልሉ ብሎም በመቀሌ የነበሩ ዋና ዋና የምንፈልጋቸውን ነገሮች አውጥተናል። አሁን መቀሌ ምንም አይነት የስበት ማዕከል አይደለችም። ምንም ለወታደራዊ ስትራቴጂነት የቀራት ነገር የለም ብለዋል። 

እስከ ቅርብ ሰዓት ድረስ ማንም የህውሓት አመራር ወደ ከተማዋ እንዳልገባም አረጋግጠናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በቅሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፖርክ በተዘጋጀውና ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና ከ600 በላይ ታዳሚዎች በተገኙበት ስነስርዓት ላይ::

©ናትናኤል መኮንን

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top