Connect with us

ዛሬ የንብ ቀን ነው፤ ከማር በላይ የተፈጥሮን ጤና ያጣፈጠችው ወሳኝ ፍጥረት!

ዛሬ የንብ ቀን ነው፤ ከማር በላይ የተፈጥሮን ጤና ያጣፈጠችው ወሳኝ ፍጥረት!
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ዛሬ የንብ ቀን ነው፤ ከማር በላይ የተፈጥሮን ጤና ያጣፈጠችው ወሳኝ ፍጥረት!

ዛሬ የንብ ቀን ነው፤

ከማር በላይ የተፈጥሮን ጤና ያጣፈጠችው ወሳኝ ፍጥረት!

(ሄኖክ ስዩም ~በድሬ ቲዩብ)

እንኳን ንብ ሌላውም ቀን አለው፡፡ ዛሬ የንብ ቀን ነው፡፡ ዓለም ይህቺን ታታሪ ፍጥረት ያከብራል፡፡ መኖሪያዋ ደህና ይሆን ዘንድ ያሳስበኛል ይላል፡፡ ማሯን እንጂ ደህንነቷን የማያስብ ቢሊዮን ፍጥረት ጥቅሟን አስልቶ አያውቅም፡፡

ዓለም ዛሬን የንብ ቀን ያለበት አንብሶ ጃንሳ የተወለደበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ሰውዬው እ.ኤ.አ በ1734 በስሎቫንያ ተወለደ፡፡ ዓለም የተወለደበትን ቀን አያውቅም ግን በዛሬው ቀን ክርስትና መነሳቱ ታወቀ፡፡ ትምህርት አልተማረም የተባለው ሰው ስመ ጥር ንብ አናቢ በመሆን ዝናው ናየ፡፡ 

የቤተ መንግሥት የንብ አለቃ እስከመሆን ደረሰ፡፡ ስለ ንቦች ሁለት መጻሕፍትን ጽፏል፡፡ እናም ለንብ ታሪክ አስተዋጽኦው ዓለም የንብ ቀንን ከእሱ ጋር አገናኝቶ ሰየመ፡፡ ለክብሩ በራዶልቪካ ውስጥ የሚገኘው የንብ ማነብ ሙዚየም በስሙ ተሰየመ፡፡

የንብ ቀን በዓለም ደረጃ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡ የንቦች ፋይዳ ማራቸው ብቻ አይደለም፡፡ የምትጣፍጥ ዓለም እንድትኖረንም አድርገዋል፡፡ ዛሬ ዓለም ሃያ ሺህ ገደማ የንብር ዝርያዎች እንደሚገኙባት ሳይንስ ይነግረናል፡፡

ንብ በብዙ ህዝቦች ባህል የታታሪነቷ ስም ጎልቶ ለትጋት ምሳሌ በመሆን የምትጠቀስ ፍጥረት ናት፡፡ ማሯ መድሃኒት መሆኑ ደግሞ የፈውስ ምክንያት ተደርጋም ትቆጠራለች፡፡ አንዳንዴም የንብ መርዝ መወጋት በሰውነት ያለን ደዌ ነቅሎ እንደመጣል እስኪቆጠር ጥቅሟ ገኖ ተነግሯል፡፡ከንብ ዝርያዎች ማር በመስጠት የሚታወቁት ቤተሰቦች አስር ዓይነት ናቸው፡፡ ባምብል ንብ የሚሏቸው ደግሞ ለአበባ ሥርጭት ምትክ የለሽ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ 

ንቦች ከአበባ ጋር ዝምድና ፍለጋ ሲባትሉ ተፈጥሮን አስታርቀው፣ እጽዋት አራብተው የሚኖሩ ህያው የምድራችን ባለውለታዎች ናቸው፡፡ ከዓለም ሰብሎች ሰባ በመቶው የንብ አመል እያራበው የሚኖር ነው፡፡

ንብን ከማር ጥቅሟ ጋር ያጠናው የዘመናችን ሳይንስ ቢሊዮን ዶላሮችን የምትለግስ ፍጥረት እንደሆነች ግምቷን አስልቷል፡፡

ዓለም የንብ ቀን ማክበርን የፈለገው የንብ ህልውና አሳሳቢ ደረጃ እየደረሰ ያለበት የተፈጥሮ መዛባት መኖሩ ነው፡፡ መኖሪያቸውን ማውደምና ተፈጥሮን ማራቆት የንብ ሀገር ጤናማ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡

ደግሞ በጸረ ተባይ ኬሚካሎች የተጠመቁ አበቦች ሌላው የንብ ስጋት ናቸው፡፡ የንብ ዝርያዎች ቁጥር በጣም መቀነሱ ዓለም ንብ በሌለባት መሬት ልንኖር ይሆን ብሎ እንዲሰጋ ምክንያት ሆነዋል፡፡

አሜሪካ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ንቦች በላይ በየዓመቱ ይሞቱብኛል ብላ ይፋ አድርጋለች፡፡ ይህ ቁጥር ካልተጠናው የመላው ዓለም የንቦች ሞት ጋር ተዳምሮ ቁጥራቸው ስጋት ውስጥ እየገባ ለመምጣቱ ምክንያት ሆኗል፡፡

አረንጓዴ አካባቢን አለመፍጠር፣ ተፈጥሮን ማቃወስና የንቦችን ምቹ ስፍራ ማሳጣት ለንብ ህልውና አደጋ ሆኗል፡፡ እናም እንደ ዓለም ሁሉ ትኩረት ምድራችንን ጤናማ ላደረገችው ፍጥረት፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top