Connect with us

ልክ ነው፤ ኢትዮጵያን መከራ ሳይሆን አረንጓዴ እናልብሳት!

ልክ ነው፤ ኢትዮጵያን መከራ ሳይሆን አረንጓዴ እናልብሳት!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ልክ ነው፤ ኢትዮጵያን መከራ ሳይሆን አረንጓዴ እናልብሳት!

ልክ ነው፤ ኢትዮጵያን መከራ ሳይሆን አረንጓዴ እናልብሳት!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እጅግ ሊመሰገኑበት ከሚገባው ተግባራቸው አንዱ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመፍጠር ጥረታቸው ነው፡፡ ቁጥሩ ትዝብት ውስጥ እየከተተን ነው አይደለም ብንነታረክም፤ ለአንድ መሪ አንድ ዛፍ በቅሎ የማየት ምኞቱ ብቻውን ትውልድ ተሻጋሪነቱን ያሳየናል፡፡

አረንጓዴ አብዮቱ ከትናንት በስቲያ ተበስሯል፡፡ ብዙ ሚሊዮን ችግኞችን በዘንድሮው ክረምትም እንተክላለን፡፡ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትልበስ መሪ ቃሉ ነው፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ከዳር ዳር የለበሰችውን መከራ አሽቀንጥራ ጥላ አረንጓዴ ለብሳ ችግርና ረሃብ የተወገደባት ሀገር መኖር እንሻለን፡፡

ኢትዮጵያን የሚወድ አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻውን ይቀላቀል፡፡ ይህ የችግኝ ተከላ ዘመቻ የዘንድሮው አብዮት ከቁጥር እና ከፌዝ ዘመቻ ባሻገር እንደ ጠቅላዮ ምኞት እኛም መረር ብለን ችግኝ ተክለን ሀገር የምናስጌጥበትም የምናድንበትም እንዲሆን መስራት አለብን፡፡

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግኝ የሚተክል መንግስት ላይ መሳለቅ አንዱ የትግል ስልት ነው፡፡ እንዲህ ያለ የትግል ስልት ለረሃብተኛ ህዝብ ረሃብ ማሸነፍ የሚፈልግ ነጋዴ ፖለቲከኛ እንድናመርት አደረገን እንጂ አልጠቀመንም፡፡

በትግራይ አብርሃ አጽበሃ የምትባል ቀበሌ ከተፈጥሮ ጋር ታግላ አረንጓዴ ለብሳ እንዴት ለድል እንደበቃች ዓለም ከሰጠው ምክርነት ጭምር አይተናል፡፡ እናም ከጠቅላዮ ጎን ከምንቆምባቸው ተግባራት አንዱ ይሄ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ምድር ለማድረግ የሚባትሉበት ህልማቸው ነው፡፡ ስኬቱ ግን የሃገር እና የመቶ ሚሊዮን ህዝብ ስለሆነ ከዳር ዳር ሆ ማለት ይጠበቅብናል፡፡

መንግስት ሰው እየነቀሉ ችግኝ ተከላ ላይ የሚመጻደቁትም እንዲሁ አደብ ያስገዛልን፡፡ የተከልነው ለሰው ነው፡፡ ሰው የሚነቅል ሰው ዛፍ አያሳስበውምና አረንጓዴ የምናለብሳትን ኢትዮጵያ መከራ ሊያለብሳት ያደባውን ሥርዓት ማስያዝም ያስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያ በተራ ፖለቲካ የተፈጥሮ ጥበቃ ህልሟ በተደጋጋሚ መክኗል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ገበሬው አፈርና ውሃ ጥበቃ ላይ ብልጥ እንዲሆን አስበውና ሰርተው ነበር፡፡ ካድሬው ግን በቁጥርና በሪፖርት ተረት መና አስቀርቶ አመድ አፋሽ አደረጋቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ቢሆኑ ተመሳሳይ ምኞት አንግበው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ትሁን ብለዋል፡፡ ግን ካድሬው ድራማውን ከቀጠለና መትከሉን ትቶ መቁጠሩን ስራ ካደረገው አሁንም ምኞታችን ይመክናል፡፡

ምኞት ማምከን ስራው የሆነ ካድሬ ለብቻው የሚኖርባት ሀገር ስለሌለች ይሄንን የችግኝ ተከላ ዘመቻ በጋራ በእውነትና በህብረት ልናሳካው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እንድትለብስ ሁሉም ዜጋ፣ ሁሉም ፓርቲ፣ ሁሉም አንቂ አብሮ ቆሞ ውጤታማ ማድረግ አለበት፡፡

የራሳችንን ሀገር አረንጓዴ ማልበስ ጥቅሙ የማንም አይደለም፡፡ ይሄንን አሳክቶ ምርጫ ድል ለማድረግ ያደባም ካለ ያድርግለት፤ ብቻ እኛ አረንጓዴ እንልበስ፡፡ የተራቆተው ተፈጥሮ መልሶ እንዲያምርበት ውሃ እንዳንቸገር ከሰው ሰራሽ ዝናብ እንድንወጣ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብሳት፡፡

ለምለሟ ኢትዮጵያ የነበረችው ድሮ አሁን ያለችው ሙዚቃችን ላይ ነው፡፡ ያቺን ኢትዮጵያ ማየት የማይፈልግ የለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ለምለም ሀገር የማየት ምኞት አለ፤ ያ ምኞት ደግሞ የሚሳካው ሀገራችንን አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻውን ስንቀላቀል ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top