Connect with us

“ከሂጃቤ ላይ እጃችሁን አንሱ” በሚል በሱማሌያዊቷ ሞዴል የተጀመረው ዘመቻ ተቀባይነት እያገኘ ነው

"ከሂጃቤ ላይ እጃችሁን አንሱ" በሚል በሱማሌያዊቷ ሞዴል የተጀመረው ዘመቻ ተቀባይነት እያገኘ ነው
ኢትዮ ኤፍ ኤም

ነፃ ሃሳብ

“ከሂጃቤ ላይ እጃችሁን አንሱ” በሚል በሱማሌያዊቷ ሞዴል የተጀመረው ዘመቻ ተቀባይነት እያገኘ ነው

“ከሂጃቤ ላይ እጃችሁን አንሱ” በሚል በሱማሌያዊቷ ሞዴል የተጀመረው ዘመቻ ተቀባይነት እያገኘ ነው

አልጀዚራ እንደዘገበው ኑሮዋን በኖርዌይ ያደረገችው ትውልደ  ሶማሌያዊቷ ሞዴል ራውዳ መሀመድ በማህበራዊ ትስስር ገጽ የጀመረችው “ከሂጃቤ ላይ እጃችሁን አንሱ” ዘመቻ በሺዎች  በሚቆጠሩ ሰዎች ተቀባይነት አግኝቷል።

ባለፈው ወር የፈረንሳይ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዕድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆናቸው ታዳጊዎች በአደባባይ ሂጃብ እንዳያደርጉ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆ ነበር:: 

ይህን ተከትሎ ነበር  ሞዴሏ ዘመቻውን የጀመረችው፡፡

የፈረንሳይ መንግስትም በዚህ ውሳኔው ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ውግዘት ደርሶበታል፡፡

 ራውዳ በእጇ ላይ ጽፋ የጀመረችው ዘመቻም  በፈረንሳይኛ  ቋንቋ ተተርጉሞ  በማህበራዊ ትስስር ገጾች በበርካቶች ሀሳቡን በማስተጋባት እንዲቀላቀሉ ሆኗል፡፡

ዘመቻውን አሜሪካዊቷ የምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማርን ጨምሮ ሌሎች እውቅ ሰዎችም ተቀላቅለውታል፡፡

ሞዴሏ ለሙስሊም  ሴቶች  መብት እንደምትታገልም  ከአልጀዚራ ጋር በነበራት ቆይታም  ገልጻለች፡፡

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top