Connect with us

ሸኘናት !!!

ሸኘናት !!!
Photo: Social media

ዜና

ሸኘናት !!!

ሸኘናት !!!

አዎ በክብር ሸኘናት!!!

ሚያዚያ 20/2013 ዘሚ በለጠፈችው መልዕክት ’’The battle goes on, I need your prayers!’’ ስትል የመጥፎ ዜናውን መጀመሪያ ነገረችን፡፡

በእውነት እንደምትድን ትልቅ ተስፋ ይዤ እኔም ስሜቴን ገልጬላት ነበር፡፡

‹‹Dearest Zemi, thinking of lots and hoping for a speedy recovery. Your presence is a lot for Joye, get well soon. ሥምሽ በራሱ የተቆላመጠ ዘምዬ  መታመምሽን የሠማሁት በድንጋጤ ነው፤ ድነሽ ‘አለሁ’ እንድትይን ፀሎቴ ነው፡፡››

አልሆነም ዛሬም በዘሚ ደነገጥኩ፡፡ ከዘሚ ጋር የምንተዋወቀው የኤፌም 97.1 እንግዳችን ሆና የውበትና ሞዲሊንግ ጥበብን በፋሽን ፕሮግራም እንድታስረዳ በምትመጣበት ወቅት ነው፡፡

ስለውበት ሙያዋ ብቻ አልነበረም የምታወራን፤ አሜሪካ የተማረችውን ትምህርት ወዲህ አምጥታ የመጀመሪያውን ኒያና የውበትና ሞዲሊንግ ማሰልጠኛን በመክፈት በልዩ ልዩ ችግር ውስጥ ላሉ ሴቶች ልጆች የነጻ ትምህርት ዕድል ስለመስጠቷም ነበር ፡፡ የልጇን የጆጆንም ታሪክና አንድ ማዕከል ለማቋቋም የወደፊት እቅዷን ትነግረን ነበር፡፡

ዛሬ ከሠዓት በኋላ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ኒያ ፋውንዴሽን ለዘሚዬ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላታል፡፡ ‹‹እናቴ፣ ጉልበቴ ፣ መደበቂያዬ ፣ ለራስሽ ሳትኖሪ ሞትሽ››! ከትኩስ እንባ ጋር እዚህም እዚያም የሚሰሙ ጩኸቶች ነበሩ፡፡

የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ፣ የሴቶች-ሕጻናትና ወጣቶች ሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ እና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትሯ  ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንባ እየተናነቃቸው የዘሚዬን ትጋትና ጥንካሬ መስክረውላታል፤

ዘሚ እራሷ ከምትመራው ድርጅት በተጨማሪ ለሌሎችም አለሁ ትላለችና በተለይ አሁን በቀይ መስቀል ቦርድ አባልነቷ ያላሠለሠው አስተዋጽዋ በማህበሩ ፕሬዝዳንት ተዘርዝሯል፡፡ አልጋ ከመያዟ አንድ ሳምንት በፊት የቀይ መስቀልን እርዳታ ይዛ መቀሌ ነበረች፡፡

ዘምዬ ግን በመድረኩ ያልተነገረላት አለ፡፡ የሚዲያ ተጠቃሚና ተቺ ነች፡፡ ከአንድም ሁለት መድረክ ላይ እንዳየኋት የሚዲያዎችን አሠራርና ይዘት በጥሩ አንደበቷ ስትተች ያዳመጧት ሁሉ እይታዋን እያደነቁ ነበር፡፡ ለምሳሌ የኤፍ ኤም 97.1 13ኛ ዓመት በዓል  ላይ የነበረውን ያስታውሱታል፡፡

እንግዲህ ዘምዬ የለችም፡፡ ከወለደቻቸው ከቢላልና ከጆጆ በተጨማሪ በየቤቱ በኦቲዝም የተዘጋባቸው ልጆች እናትም ነበረች፡፡ የነገዎችም ልጆች እናት ትሆን ዘንድ በሳሚት አካባቢ በተሰጣት ቦታ ሥራው የተጀመረውን የኦቲዝም ማዕከል ግንባታ ተባብረን ከዳር እናድረስው ሲሉ ሁሉም ተናጋሪዎች ጠይቀዋል፡፡ ግንባታውን የሚያከናውነው የኮንስትራክሽን ድርጅትም ያለምንም ጥቅም በሙያ ለማገልገል ቃል በመግባት እናንተም አሸዋ፣ ሲሚንቶ ፣ ጠጠር ብረት ገዝታችሁ እንድታቀርቡልን ሲሉ የድርጅቱ ባለቤት ጥሪ አድርገዋል፡፡

በገንዘብም ለመርዳት የባንክ የሂሳብ ቁጥር ተሰጥቷል

Nia Foundation (Joy Autism Center)

Commercial Bank of Ethiopia

1000066285808

ዘሚን በዚህ እንጥራት!!

(ሶሎሜ ደስታ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top