Connect with us

አንጋፋው  የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ህንፃ ሊታደስ ነው

አንጋፋው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ህንፃ ሊታደስ ነው
Ethiopian News Agency

ዜና

አንጋፋው  የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ህንፃ ሊታደስ ነው

አንጋፋው  የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ህንፃ ሊታደስ ነው

ከ50 ዓመት በላይ እድሜ ያለው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንፃ በ45 ሚሊዮን ብር እድሳት ሊደረግለት መሆኑ ተገለፀ።

እድሳቱ በዛሬው እለት የተጀመረ ሲሆን ወጪው በጤና ሚኒስቴር እንደሚሸፈን ታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አመራሮች በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋት አዳዲስ ግንባታዎችን ማከናወንና ነባር የጤና ተቋማትን ለማደስ እየተሰራ ነው።

በዚህም ሪፈራል ማዕከል ሆኖ በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጠው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ነባር ህንጻ እድሳት እንደሚደረግለት ገልጸዋል።

በኮሌጁ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በመጠቆም።

በጉብኝታቸው የካንሰርና የልብ ህክምና ማዕከል፣ የአንገት በላይና የአይን ህክምና እንዲሁም የተለያዩ ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጡ ግንባታዎች አፈፃፀም 67 በመቶ መድረሱን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የማዕከላቱ ግንባታ ወጪ ሶስት ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ቢሆንም ወጪ ቆጣቢ አሰራር በመከተል የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎችን ጨምሮ ግንባታቸው ሁለት ቢሊዮን ግምት ያለው መሆኑን አስረድተዋል።

የማዕከላቱ ግንባታ ከአቅርቦትና ዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ የተጓተተ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግንባታቸው በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ በቀጣይ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ጠቁመዋል።

“ኮሌጁ ከኮቪድ-19 ህክምና ጎን ለጎን ሌሎች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው” ብለዋል።

የኮሌጁ ነባር ህንፃ የድንገተኛ አገልግሎቱን ለማስፋፋትና የቀዶ ህክምናና የውስጥ ደዌ ህክምናን ለማጠናከር ታስቦ በ45 ሚሊዮን ብር ሰፋ ያለ እድሳት የማድረግ ስራ መጀመሩን ጠቅሰዋል።

እድሳቱ ኮሌጁ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑን ገልፀው፤ “እድሳቱ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከኮሌጁ አመራሮች ጋር ይሰራል” ብለዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር ወንድማገኝ ገዛኸኝ ነባሩ ህንፃ ከ50 አመት በፊት የተገነባና ለበርካታ አመታት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

እድሳቱ የህክምና አገልግሎቱን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚረዳ በመጠቆም በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስረድተዋል።(ኢዜአ)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top