Connect with us

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአማራ ህዝቦች ምስጋና አቀረቡ

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአማራና ድርጊቱን ለተቃወሙ ህዝቦች ምስጋና አቀረቡ
Photo: Social media

ዜና

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአማራ ህዝቦች ምስጋና አቀረቡ

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአማራና ድርጊቱን ለተቃወሙ ህዝቦች ምስጋና አቀረቡ

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአማራና ድርጊቱን ለተቃወመው ህዝብ በምስጋናቸው

በዞናችን በተደራጀውና በታጠቀው ቡድን ከመንግስት የፀጥታ መዋቅር ውጪ በማይፈቀዱ ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ታግዞ አጣዬን፣ካራቆሪንና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በመውረር አውድሟል።

በተጨማሪም እንደ አማራ ህዝብ ተከታታይነትባለው መልኩ በኦሮሚያ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በታጠቁና በተደራጁት ቡድኖቾ ዘርን መሠረት ያደረገ አሰቃቂ ግድያና የንብረት ውድመትና መፈናቀል ተፈፅሟል።

በዞናችን  አስተዳደር ደብረብርሃን ከተማ ከ13-14/2013 ዓ.ም ለተከታታይ 2ለት ቀናቶች በተደረገው ሠላማዊ ምስጉን ሠልፍ ላይ የነበረውን አርቆ አስተዋይነት ተሞክሮ ለመላው ህዝባችሁ አስመስክራችኋል እኛም  ከህዝባችን ጎን ቆመን ስናጠፋ የሚሰጠንን ተግሳፅ አፈናጥረን ሳይሆን ድክመታችንን ወደ ውስጥ አይተን ከሚያኖረን ከሚያድነን አርቆ አስተዋይ ህዝባችን ጎን መቆም መዳኛችን መሆኑን ለአፍታም አንዘነጋው።

ጠላቶቻችን ባለመደራጀታችን በአራቱም ማዕዘን ያለን ኢትዮጵያኖች እርስ በእርሳችን ተዋደን ፣ ተከባብረንና እንደሠርገኛ ጤፍ መለየት በማይቻልበት ተቀላቅለን ከሠላም ወዳዱ የኦሮሞ ህዝብና ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ከሙስሊም ክርስቲያኑ በጋራ መኖራችን ሠላም ያልሰጣቸው እርኩሶች  ያደረባቸው እርኩስ መንፈስ ነው እና ቀልደውብን ያጠፉናል ።

ከህዝባችን ጎን ስንሆን ግን ገዳያችንና ወራሪያችን ያነገበው አላማ መጥፎ መንፈስ ነው እና በማይወደው ስለመጣን ኮስምኖ ይወድቃል ምርጫችን ዛሬም ነገም  እንደ አማራ ተደራጅተን ከህዝባችን ጎን በመሆን ኢትዮጵያን ከጠላት መታደግ ነው።

ህዝቡ የአባቶቹን ከፍታ አርቆ አስተዋይነት ላቅ ባለ ጀግንነትና ቁርጠኝነት የተደረገው ግፍና በደል ትኩስ በመሆኑ  ቁጭት እልህና መፈታተን  ስለሚኖር ይህንን ተጠቅመው ሰልፉን ጠላቶቻችን ሊያለያዮንና ሊያቆራርጠን በሚችል መልኩ ለመረበሽና ደም ለማፋሰስ ከውስጣችንም ከውጪም በመቀናጀት የታሰበውን ሴራ በፍፁም ጨዋነትና ትዕግስት የዞናችን አርቆ አስተዋይ ህዝብና ወጣቶች የዘርአያቆብ፣ የእምዬ ምኒልክ ልጆች እንደሚባለው ሁሉ ሸዋ በጥበቡ  የቋመጡለትን እረብሻ እንደጉም አትንነው  በአስገራሚ ስክነት መልእት በማስተላለፍ ሠልፉ በሠላም ተጠናቋል።

እንደ አማራ አሁን የገጠመንን የህልውና ፈተና ለማለፍ ኃላፊነቱን ለማንም ባለመስጠት ሁሉም አካል ከዚህ ቀደም እንዳስተላለፍንው አጥፊወቻችን ከጥፋት ድርጊታቸው እንዲታቀቡና አደብ እንዲገዙ ከስራዎች ሁሉ ቀዳሚ በሆነው ስራ በመደራጀት እራሳችንን በራሳችን ተፈጥሯዊ የማዳንና የመከላከል መብት ተጠቅመን አካባቢያችንንና ኢትዮጵያን ከዚህ አሸባሪና አውዳሚ ቡድን መጠበቅ አለብን።

በመጨረሻም ሠልፉ እንዳይረበሽ በሰልፉ ለተሳተፉ ሁሉ፣ በተለይም ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሰልፉ አስተባባሪዎችና ሃገር ተረካቢ ወጣቶች እንዲሁም ለፀጥታ መዋቅሩ ክብር ያለኝ መሆኑንና ምስጋናዬንም በዚሁ አጋጣሚ በእጅጉ አቀርባለሁ ብለዋል፤ አቶ ታደሠ ገብረፃዲቅ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top