Connect with us

144 የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው

144 የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው
ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

ዜና

144 የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው

144 የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ነው

የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሥራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን መመሪያ ተቀብለው ተግባራዊ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሰራተኛ አገናን ኤጀንሲዎች ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ውጤት እና የተሰጡ የውሳኔ ሀሳቦችን በተመለከተ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አሠሪ ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በጋራ ለጋዜጠኖች ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመግለጫው እንደተናገሩት በምልከታው ሁሉም ኤጀንሲዎች ሊባል በሚችል ደረጃ በተለይ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና አዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ ተከትሎና አክብሮ በመሥራት ረገድ ክፍተት ያለባቸው መሆኑና በተለይ 20/80ን ተግባራዊ አለማድረጋቸው መረጋገጡን አንስተው የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጄንሲዎች የሥራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣው መመሪያን ተፈፃሚ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሯ በጥናቱ በተሸፈኑ ሁሉም ኤጀንሲዎች በጥበቃም ሆነ በሌሎች የሙያ መስኮች የተቀጠሩ ሠራተኞች የደሞዝ አከፋፈል ሁኔታ፣ የሥራ ሰዓት፣ የዓመት ዕረፍት፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በሕጉ መሰረት እየተከፈለ አለመሆኑ በጥናት መረጋገጡ ጠቁመዋል፡፡ 

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህጎችን በመጣስም ሆነ በወንጀል ድርጊት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ 144 ኤጀንሲዎች ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠውን ፈቃድ በመመለስ ከዘርፉ መውጣት ይኖርባቸዋል የሚል የውሳኔ ሃሳብ መተላለፉን ዶ/ር ኤርጎጌ አንስተው በጥናቱ የተላለፉ ውሳኔዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ  ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልፀዋል፡፡

በመንግስታዊ ተቋማት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ለኤጀንሲዎች ፍቃድ በመስጠትና አፈፃፀማቸውን በመከታተልና በመደገፍ ረገድ ክፍተት ያለበት በመሆኑ በቀጠይ ትኩረት ተሠጥቶ እንደሚሰራበት ዶ/ር ኤርጎጌ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሠሪ ፌዴሬሽኖችን ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታደለ ይመር በበኩላቸው የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሥራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታ ለመወሰ የወጣውን መመሪያ ትክክለኛና ሊያሰራ የሚችል በመሆኑ ኤጀንሲዎች ህግና ደንብን አክብረው እንዲሰሩና  ለተፈፃሚነቱ  ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

መመሪያና ህግ ተግባራዊ የማይደረግ ከሆነ ህግና ሥርዓት አይኖርም ያሉት የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሮዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በመመሪያው መሰረት የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ህግን አክብረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

ጥናቱ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉና ፍቃድ አውጥተው በሚንቀሳቀሱ 314 ኤጀንሲዎች ላይ መደረጉ ተገልጿል፡፡(የሠራተኛና ማህበራዊ ጉ/ሚ)

ፎቶ:- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

 

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top