Connect with us

የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው

የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ዜና

የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው

የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው

ትናንት በአሶሳ ከተማ ባለቤቱ ያለታወቀ አንድ ተሣቢ መኪና የጦር መሣሪያ ተይዟል በሚል የተናፈሰው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተሠጠው ሙሉ መግለጫ ይህ ነው።

ሚያዚያ 14 ቀን 2013 ዓ/ም በአሶሳ ከተማ ባለቤቱ ያልታወቀ አንድ ተሳቢ መኪና ሙሉ ጦር መሳሪያ እንደጫነ ተይዟል በማለት ያልተረጋገጠና ከእውነት የራቀ የውሸት መረጃ ከአንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ተመልክተናል።

እነዚህ ማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ማንነታቸውን ደብቀው ድብቅ አጀንዳ በሚያራምዱ ግለሰቦች መረጃውን በማሰራጨት ህብረተሰቡን በማደናገርና በከተማው ያልተፈለገ ግርግር ለመፍጠር የታሰበ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል።

ሆኖም ወደ ከተማው ገባ የተባለውን ተሽከርካሪ ፈትሾ ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኖ የአሶሳ ከተማ አስ/ር ፖሊስ አባላት የንብረቱ ባለቤቶች ባሉበት ፍተሻ ሲያደርግ በመኪናው ውስጥ የነበረው በህጋዊ መንገድና ህጋዊ ሰውነት በፌደራል ተሰጥቶት የገባ የወርቅ ማሽን ሲሆን የማሽኑን ህጋዊነት የሚያሳይ ሰነድ ይዘው መገኘታቸው ተረጋግጧል።

ስለሆነም ህብረተሰቡ ምንጩ የማይታወቅና ያልተረጋገጠ መረጃ ይዘው ለማወናበድና የከተማውን ነዋሪ ወደ አልተፈለገ ሽብር ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን በመለየት እራሱን እንዲጠብቅ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ አጋጣሚ መልዕክቱን ያስተላልፋል።(የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top