Connect with us

#የትዝብት_ጥግ!!

#የትዝብት_ጥግ!!
ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

ነፃ ሃሳብ

#የትዝብት_ጥግ!!

#የትዝብት_ጥግ!!

ሰሞኑን ወደፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሚያመላልስ የቤተሰብ ጉዳይ ነበረኝ። ቢሮው ለገሀር አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የፌደራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ነው። ጠ/ሚ ዐብይ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት የዋና ዋናዎቹ ኃላፊዎች ቢሮ ውብ ሆኖ ተገንብቷል።

ግን ምን ዋጋ አለው ውስጡ የተቀመጡ አንዳንድ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጭምር ውስጣቸው ስለመንፃቱ፣ ስለመታደሱ የዓይን እማኝ ለመኾን አልታደልኩም።

አብነት አንድ:-

ወደአንድ ከፍተኛ ኃላፊ ቢሮ ለአቤቱታ ለመግባት ጥያቄ ባቀረብኩበት ወቅት በአጭሩ “እሳቸውን ማናገር አትችልም፣ አትድከም ተባልኩኝ”

ምክንያት?…በኮቪድ ምክንያት ሰዎችን አያናግሩም። እናም የተሰጠኝ አማራጭ ” አቤቱታ የሚቀበል ክፍል አለ፤ እዚያ አቅርብና መልስ ታገኛለህ የሚል ነው።” ትንሽ ባንገራግርም ከፀሐፊዋ የተሰጠኝ መልስ “እኔ ምን ላድርግ ታዛዥ ነኝ” የሚል ነበር።

እዚህ ላይ አሳዛኙ ነገር ከፍተኛ ባለጉዳይ የሚመላለስበት ቢሮ በኮቪድ ምክንያት መዘጋቱ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ኃላፊዎቹ ስራ ባለመስራት ጭምር  ከኮቪድ ራሳቸውን በማሸሽ ዝቅተኛ ሠራተኞች ግን እነሱ ከሸሹት ኮቪድ ጋር እየታገሉ ስራቸውን እንዲያከናውኑ መግፋታቸው ነው። እንግዲህ ከተያዛችሁም እናንተ ብትያዙ ይሻላል የሚል  ይመስላል።

አብነት ሁለት:-

የኮርፖሬሽኑ የበላይ ኃላፊዎች ከኮቪድ ራሳችሁን መጠበቃቸው፣  ተገቢ ያሉትን ጥንቃቄ ማድረጋቸው አያስወቅሳቸውም። ግን ኮቪድን ምክንያት አድርጎ ከባለጉዳይ መሸሽ፣ በር መዝጋት በምንም መመዘኛ ተገቢ እርምጃ ሊሆን አይችልም። የፈራ ሹም መመለስ ያለበት ወደቤቱ ነው። ቢሮ መስሪያ እንጂ መጎለቻ ሊሆን አይችልም።

በተጨማሪ የኼድኩበት ጉዳይ ከቤት ማስመለስ ጋር የተያያዘ ነበርና በየቢሮው ያየኹዋቸው ኃላፊዎች የተሰላቹ፣ ፊታቸው ፈታ አድርገው እንኳን ባለጉዳይ ማናገር የማይችሉ በአጠቃላይ ከቢሮ ማስዋብ በዘለለ የአገልጋይነት መንፈስ አፈር የበላበት ሆኖ አግኝቼዋለኹ።

በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ የበላይ  አመራሮች ለምን ተተቸን ብለው ሳያኮርፉ በኮቪድ ፍራቻ ስራ ትተው ቢሮአቸውን ዘግተው የሚውሉ አመራሮች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ፣ የቢሮውን አገልግሎት አሰጣጥም እንዲያሻሽሉ ጥቆማዬን አቀርባለኹ። (እሱባለው ካሳ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top