Connect with us

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
Ethiopian press agency

ዜና

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከ137 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን  አስታወቀ፡፡ የተገኘው ገቢ ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር 27 ሚሊየን ብር  ብልጫ  አለው ብሏል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሐመድ የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ወር እና የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

እንደ አቶ አብዱሰላም መሐመድ ገለጻ፣በ2013 በጀት ዓመት በመጋቢት ወር ከመንግስት ታክስ እና ከመዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር 140 ሚሊየን 865ሺህ 471.36 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 137,402,956.20 መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የወሩን የእቅዱን 97.54በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የ2013 በጀት ዓመት የመጋቢት ዕቅድ አፈፃፀም ከ2012 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ24.89 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ መንግስት በኮሮና ወረርሽኝ ግብር ከፋዩ ላይ የደረሰውን የኢኮኖሚ ጫና እንዲታደግ 120,000,000 ብር በላይ ያደረገው ድጎማ ሳያካትት 1,267,936,139.77 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 1,075,575,415.17 መሰብሰቡን ገልፀዋል። ዕቅዱን 84.83በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 12.18በመቶ ወይም በብር 116,766,722.85 ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

አስተዳደሩ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ የሰጠው ጠንካራ ትኩረት ፤ ታማኝና ከፍተኛ ግብር ከፋዬች ግብራቸውን በማሳወቅ በጊዜ መክፈል በመቻላቸው እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተቀናጅተው በመስራታቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ መግለጻቸው ባለስልጣኑ አስታውቋል ፡፡(ኢኘድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top