Connect with us

‹‹ስንቱን አይነት ዜና እየሰማን ምንም እንዳልነበረ ኑሯችንን የምንቀጥልበት ልብ ሊኖረን አይገባም!!›› ኘ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ

‹‹ስንቱን አይነት ዜና እየሰማን ምንም እንዳልነበረ ኑሯችንን የምንቀጥልበት ልብ ሊኖረን አይገባም!!›› ኘ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

‹‹ስንቱን አይነት ዜና እየሰማን ምንም እንዳልነበረ ኑሯችንን የምንቀጥልበት ልብ ሊኖረን አይገባም!!›› ኘ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ

‹‹ስንቱን አይነት ዜና እየሰማን ምንም እንዳልነበረ ኑሯችንን የምንቀጥልበት ልብ ሊኖረን አይገባም!!›› ኘ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ

‹‹ በምንም ሁኔታ ይሁን በየትኛውም አገር አቀፍ ሕግ የንፁሃን ደም በከንቱ ሊፈስ አይገባም፣ ከመብቶች ሁሉ ቀዳሚ የሆነው በበሕይወት የመኖር መብት በቅድሚያ መከበር ያለበት ነው። […]

ሞት፣ ሰቆቃ፣ መፈናቀልን እየተለማመድን ከመጣን አገራችንን ለከፍተኛ አደጋ እናጋልጣለን። ይልቁንም ወገኖቻችን የት ሔዱ፣ ምን እናድርግላቸው ማለት የሁሉም ቤተ እምነቶች አስተምሮ በመሆኑ ለፈጣሪ መገዛት ይገባል።

ስለዚህ ‹‹ለአገሬ ስል ዝም አልልም፣ ቁጭ አልልም በማለት እያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ራሳችን ፈትሸን አዳምጠን የእኔ ሚና ምንድ ነው ብሎ መጠየቅ አለብን። ምክንያቱም ጉዳዩ ለሰላም ዘብ የመቆም ጉዳይ በመሆኑ የራሳችን እንቅስቃሴና ፍላጎት የሌላውን መብትና ፍላጎት እንዳይነካ ለከት ማበጀት ይኖርብናል።

‹‹እጃቸዉን በሌላ ላይ ሲያነሱ እያየን ዝም አንልም ማለት አለብን፡፡ እዉነት ለመናገር ግፍ ሲፈጸም እያየን፣ እየሰማን የጭካኔና አረመኔነት ፉክክር ያለ ይመስል የሚከሰተዉን እያወቅን ዝም አንበል፤ እንረባረብ።

በአንድ ላይ ሆኖ መፀለይ ከፍተኛ የሆነ የአንድነት ኃይል መሆኑን እናሳያለን፤ ሰላምን ለማደፍረስ የሚፈልጉና የሚታገሉት እነዚህን የመሰሉ ጠንካራ የመገናኛ ድልድዮች ላይ ስለሚያነጣጥሩ ነቅተን በአንድነት መጠበቅ ይኖርብናል፤ እግዚአብሔር እንዲረዳን መረዳዳት ይገባናል።…”

***የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፤  የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፈዉ ሳምንት ባዘጋጀው አገር አቀፍ የፀሎትና ምህላ ፕሮግራም  ማስጀመሪያ ላይ ከተናገሩት፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top