Connect with us

ኢትዮጵያ ~ ለተባበሩት መንግስታት:- “ግብፅና ሱዳን ድርድሩን እያኮላሹ ነው”

ኢትዮጵያ ~ ለተባበሩት መንግስታት:- "ግብፅና ሱዳን ድርድሩን እያኮላሹ ነው"
የውጭ ጉ/ሚ ቃል አቀባይ ቢሮ

ዜና

ኢትዮጵያ ~ ለተባበሩት መንግስታት:- “ግብፅና ሱዳን ድርድሩን እያኮላሹ ነው”

ኢትዮጵያ ~ ለተባበሩት መንግስታት:- “ግብፅና ሱዳን ድርድሩን እያኮላሹ ነው”

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘውን የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተ ያላትን አቋም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት በጻፉት ደብዳቤ አስታወቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት አባል አገራት ሱዳን እና ግብጽ በውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ላይ በማተኮር ወደሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲመለሱ እንዲሁም አገራቱ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት የድርድር ሂደትን እንዲያከበሩ ሊያሳስቧቸው ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ለወቅቱ የተባበሩት የጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት ፕሬዚዳንት በፃፉት ደብዳቤ የአፍሪካ ሕብረት ሂደት የተባበሩት መንግስታት መርሆዎችን እንዲሁም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ የታቃኘ በመሆኑ በም/ቤቱ ድጋፍ የተቸረው መሆኑን አስታውሰዋል።

ሱዳንና ግብጽ በሁሉንም አገራት ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ላይ እንዲደረስ በቅን ልቦና እየተደራደሩ እንዳልሆነ በደብዳቤያቸው ጠቅሰዋል። አያይዘውም አገራቱ ድርድሩን “ማኮላሸት” ምርጫ ማድረጋቸውን እና ጉዳዩን “ዓለም አቀፋዊ ይዘት” በማላበስ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ለመክተት እየሞከሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት ለሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ያላትን እምነት እና ቁርጠኝነት አረጋግጠው፣ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም አሁን ደግሞ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚለው መርህ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ያላቸውን ምስጋና ገልፀዋል።

በመጪው ክረምት ከሚካሄደው የሁለተኛው ዙር የግድቡ ሙሌት አስቀድሞ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ ተነሳሽነቱን ወስዳ ላቀረበችው ጥሪ በግብፅና ሱዳን በኩል አዎንታዊ ምላሽ እንዳላገኘች በፃፉት ደብዳቤ አፅዕኖት ሰጥተው ገልፀዋል።

በሁሉን አቀፍ አስገዳጅ ስምምነት ስም ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን በማስጠበቅ እና ኢትዮጵያ በውሃው እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 በሶስቱ አገራት መሪዎች በካርቱም ለተፈረመው የመርሆች ስምምነት ያላትን ቁርጠኛ አቋም ገልጸው፣ ሁለቱ አገራት ግን ከስምምነቱ ባፈነገጠ መልኩ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ክቡር አቶ ደመቀ በጻፉት ደብዳቤ ጠቅሰዋል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ለመክተት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ እንዲሁም ድርድሩ ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች በአገራቱ መካከል ያለውን መተማመን እንደሚጎዳ በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።(የውጭ ጉ/ሚ ቃል አቀባይ ቢሮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top