Connect with us

በአጣዬና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገ ነው

በአጣዬና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገ ነው
አሚኮ

ዜና

በአጣዬና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገ ነው

በአጣዬና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገ ነው

በሰሜን ሸዋ ዞን የኦነግ ሸኔ አጥፊ ቡድን በፈፀመው ጥቃት ንጹሃን ተገድለዋል፡፡ አካል ጎድሏል፡፡ ሀብትና ንብረት ወድሟል፡፡ ከጥቃቱ የተረፉት ዜጎች ደግሞ የሞቀ ቤታቸውን ጥለው ለችግር እንዲዳረጉ ሆነዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መካከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት  ኃላፊ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ለአሚኮ እንዳሉት በዞኑ በርካታ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡ በደረሰው ጉዳት በጊዜያዊ መጠለያ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን ለማገዝ ወጣቶች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ማኅበራትና ሌሎች አካላት ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

ከቀያቸው ተፈናቅለው በመሀል ሜዳ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደብረ ሲና እና በበርግቢ ለሚገኙ ወገኖች የዕለት ደራሽ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ለተፈናቀሉት ወገኖች የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሌሎች አካላትም ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት በዘጠኝ ተሽከርካሪዎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ መላኩን ነው  የተናገሩት፡፡ ከፍተኛ ውድመት ባልደረሰባቸውና አሁን ላይ መረጋጋት ባለባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው  እየተመለሱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢው  የጸጥታ ችግር ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ  ድጋፍ እያደረጉ ያሉ የኀብረተሰብ ክፍሎችን ኀላፊው አመስግነዋል፤ በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም  ጠይቀዋል፡፡ 

የክልሉ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣና የተፈናቀሉት ዜጎችም በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያሳየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ወርቃለማሁ ጠይቀዋል፡፡

(ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ ~አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top