Connect with us

የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ 

የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ገለጸ፡፡
አሚኮ

ዜና

የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ 

የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ገለጸ፡፡ 

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በንጹሐን ላይ ሞት፣ በንብረት ላይ ውድመት እና በክልሉ ሰላም ላይ ስጋት አጥልቶ ሰንብቷል፡፡ ከጥቃት ያመለጡትም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሸሽተዋል፡፡ 

ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ በየአካባቢው የጸጥታ መዋቅር ተሰማርቷል ያሉን የክልሉ ሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በሰሜን ሽዋ ዞን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር ከክልሉ እና ከፌደራሉ የጸጥታ ኀይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡ 

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ተጨማሪ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ወደ ቦታው አቅንቷል ያሉት አቶ ሲሳይ ትናንት ግጭቶች ቢኖሩም የጸጥታ ኀይሉ ችግሩን እየተቆጣጠረው ነው ብለዋል፡፡ 

የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ እና በከተማዋ አካባቢ የመሸጉ ሥርዓት አልበኞችን ከሕዝቡ ጋር እየለዩ መሆኑን አቶ ሲሳይ ዛሬ ለአሚኮ በሰጡት መረጃ ገልጸዋል፡፡ 

በክልሉ የገጠመው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር በሽብር ቡድኖች ክልሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዳይቀጥል ታስቦበት የሚሠራ በመሆኑ ሕዝቡ ይህንን በመረዳት ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመቆም የአካባቢውን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(አሚኮ) 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top