Connect with us

የካይሮ  ማስቀየሻ 

የካይሮ ማስቀየሻ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የካይሮ  ማስቀየሻ 

የካይሮ  ማስቀየሻ 

      ( እስክንድር  ከበደ)

ግብጽ  ግድቡ ሁለተኛ ሙሌት እንደማይጎዳት ግን ለሱዳን ያሳስበኛል ማለቷን ሰምተናል፡፡ ይህ በጣም  ተአምረኛ ለውጥ  እውነት  ይሆን ʔ የግብጽን የዲፕሎማሲ ጨዋታ በቅርበት ለተከታተለ የሚያስገርም አይደለም፡፡ በፊትም የያዘችውን አቋም በሌላ መልኩ የማራመድ ብልሃት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሱዳን አዳዲስ አጀንዳዎችን በማምጣት ከቀድሞ አቋሞቿ የተለየች መሆኗን እያየን ነው፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ውዝግብ እንድትገባ ፤ከድርድሩ በፊትና በድርድሩ ላይ የምታመጣቸውን ሀሳቦች  ከጀርባ  ለግብጽ አቀብላ  ከፊት ለፊት አጀንዳውን  እንምትደግፍ  ታስመስላለች፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው አዳዲስ የድርድር አካሄዶችን የምታመነጨው ካይሮ ነበረች፡፡  አሁን ግን በጓሮ በር የዶለቱትን ካርቱም ወደ አደባባይ እንደራሷ  የሀሳብ አመንጪነት ይዛ ትቀርባለች፡፡

አልጀዚራም ሆኑ  ሌሎች  አለም አቀፍ ሚዲያዎች  የካርቱም ባለስልጣናትን ስለህዳሴ ግድብ ሲጠይቁ ” ሱዳን ግድቡን በተመለከተ የነበራትን አቋም ምን አስለወጣትʔ” የሚሉ ጥያቄዎች ይበዛቸዋል፡፡ ኢትዮጵያም ሱዳን ባመጣችው አዲስ የባህሪ ለውጥ  ተስፋ ሳትቆርጥ ፤የካርቱም ጠበኛ አካሄድ መነሻውን ለሶስተኛ ወገን ይስጣሉ፡፡  የሱዳን መንግስትን በሁለት ከፍለው  የሱዳን ልዑላዊ ምክር ቤትን የሚመሩት  የወታደሮቹ ክንፍ ና የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ሲቪል ካቢኔን በመነጣጠል  የማየት አዝማሚያም አለ፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  የልኡካን ቡድናቸውን በመሩት አምባሳደር ሙሀሙድ ዲሪር አማካኝነት  ሱዳን  ሰላም እንድታገኝ ማድረጋቸው  ፤ ከሱዳን ህዝብ ፍቅርና ክብር ቢያገኙም ከወታደራዊ ኃይሉ ተመሳሳይ   ነገር መጠበቅ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም  የህዝባዊ አመጽ ተከትሎ  የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ኡመርን ከስልጣን  ያስወገደው ወታደራዊ ክንፉ  ለሁለት አመታት  የሽግግር  መንግስቱን በመምራት በምርጫ ለሲቪል መንግስት እንደሚያስረክብ መግለጹ ይታወሳል፡፡ 

ህዝባዊ አመጽ የመሩት ሲቪሎች ድርጊቱን በመቃወማቸው  ድርድር ተደርጎ  የሱዳን የስልጣን አንጓዎች ለሁለት እንዲከፈሉ ሆነ፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ትልቅ ሚና ነበራት፡፡ ይህም ማለት የግብጹ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ የመፈንቅለ መንግስት አካሄድ የተከተለው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል  ወደፊትም ቢሆን ልክ አንድ  አል ሲሲ እራሱን ወደ ሲቪል ቀይሮ የሀገሪቱ መሪ እንዳይሆን ገደብ ተቀምጦበታል፡፡

የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና  አዲሱ ካቢኔ  ስልጣኑን በተረከበ  ሰሞን ከሞላ ጎደል የቀድሞ መንግስትን  ብሎም  የሀገሪቱን ጥቅም  ያስቀደመ አካሄድ በጥንቃቄ መከተል ጀመረ፡፡ ሱዳን በአሜሪካው ድርድር  ወቅትም ኢትዮጵያ ባልተገኘችበት የመጨረሻ ስብሰባ ከግብጽ ጋር አንድና ያው የሆነ አቋም አልያዘችም፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ መንግስት  በአረብ ሊግ ስብሰባ ከግብጽ ጎን  ሲቆሙ ፤ሱዳን አቋም መግለጫውን በድምጸ ተአቅቦ ማለፏ የግብጽ ጥርስ እንዲነከስበት ሆነ፡፡ በዛው ሰሞን ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ካርቱም ውስጥ ለጥቂት ከግድያ ሙከራ ተረፉ፡፡ የካይሮ  የደህንነትና ስላላ ኃላፊው  ካይሮ በመሄድ ድርጊቱን እንደሚያወግዙ  አስመስለው ተመለሱ፡፡ ግብጽ ከወታደራዊ ክንፉ ጋር ያላትን ግንኙነት በእጅጉ አጠናከረች፡፡  የወታደሩና የደህንነት መዋቅሩ በእጁ የሌለው የሽግግር መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምርጫ በፊት ሊወገድ እንደሚችል ምልክቶችን እንዲያይ በማድግ የካይሮ ጆሮ ጠቢዎች አይሰናችውምና ሁሉ ነገር እየተቀየረ መጣ፡፡

የሱዳን ለስላሳ ባህሪና የጉርብትና መልክ እየተቀየረ መምጣቱ አልቀረም፡፡ በህዳሴ ግድብም ሆነ በድንበር ውዝግቡ ሱዳን  ይዛ የምትቀርበውን  እንግዳ ነገሮች  ኢትዮጵያ ደግሞ ፈጥና ለማመን እየተቸገረች ነው፡፡ ካርቱም በሶስተኛ ወገን ግፊት እያደረገችው መሆኗን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ  በአረበኛ የተጻፈ ደብዳቤ ካርቱም  ቢልኩም ፤ ሱዳን  በህዳሴውም ሆነ በድንበር ዙሪያ  የያዘቻቸው አቋሞች ከራሷ የሚመነጩ እንደሆነ ደጋግማ ታስረዳለች፡፡

አሁን ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ውዝግብ ላይ ናቸው፡፡ ግብጽና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ  ልምምዶች በሱዳን ያውም ለኢትዮጵያ በቀረበ አካባቢ ይደጋግሙታል፡፡ ይህንን ልምምድ  ግብጽ ከምትዋሰናቸው ሀገራት ወይም ሌሎች የድንበሮቿ አካባቢዎች ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ነው፡፡ ለወታደራዊ እርምጃቸውና እንቅስቃሴያቸው  በነጻነት ለማካሄድ በመጀመሪያ ዳርፉር የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ሱዳን ጠየቀች፡፡ 

ጦሩ እንዲወጣ ስምምነት ሆነ፡፡ ዋናው አላማ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ኃይል ከሱዳን ግዛት ማስወጣት ነው፡፡ ከኮንጎ ኪንሻሳው ድርድር በኋላ ደግሞ በአቢዬ ግዛት የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ይውጣል ስትል ሱዳን መጠየቋ ተሰማ፡፡

የሱዳንና ግብጽ ተቀያያሪ  መግለጫዎችና አዳዲስ ሀሳቦች በሕዳሴው ግድብ ላይ  ”እውነታውን ተቀበሉ” ብሎ እንደ ድል  ማየት እንዳያሳስተን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለፓርላማው ”የሁለተኛው ሙሌት አያሳስበንም” አሉ ” የሚያሳስበው ለሱዳን ነው፡፡” ማለታቸው ምንም የጎላ የአቋም ለውጥ አይደለም፡፡ 

የግብጽን  አካሄድን ላጤነ ሁለት ነገር ይገምታል፡፡ አንዱ ሱዳን የምታቀርበው አጀንዳ የራሷ መሆኑን ለኢትዮጵያና ለሌላው ለማሳመን ፤ የወዳጅ ሀገር መነካት እንደራሷ መነካት አድርጋ ማስቀየስ ይመስላል፡፡ የሱዳን መንግስትና ህዝብ ደግሞ አሁን እያራመደ ካለው አቋም  የበለጠ እንዲገፋበት በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር  ከሙሌቱ በፊት አስገዳጅ  የሚሉትን ስምምነት እንድትፈርም  ማግባባት ፤ ይህም ለሌላ ” ሁሉም አማራጮች ” መጠቀም ማማተር እንደሆነ በጥንቃቄ  መመልከቱ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የቤት ስራ ይሆናል፡፡ 

የግብጽ ማስቀየሻዎች ረቂቅ በመሆናቸው ምንጊዜም በጥንቃቄ መመልከቱ አይከፋም፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top