Connect with us

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ የአጣዬና አካባቢዋን ጥቃት አወገዘ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ የአጣዬና አካባቢዋን ጥቃት አወገዘ
አሚኮ

ዜና

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ የአጣዬና አካባቢዋን ጥቃት አወገዘ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ የአጣዬና አካባቢዋን ጥቃት አወገዘ

ጽንፈኛ እና አሸባሪ ኀይሎች ባሰማሯቸው አሸባሪዎች በሰሜን ሸዋ በተለይም በአጣዬ፣ በካራቆሬ፣ በሸዋሮቢት፣ማጀቴ፣አላላ፣አንጾኪያ እና አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ተግባር የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በጽኑ አወገዘ።

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ እንዳለው በዘር ማጥፋት ተግባሩ በሕይወት እና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት እጅጉን አዝኗል፡፡ የአማራ ክልልም ሆነ የፌዴራል መንግሥት በዚህ ተግባር በቀጥታ ተሳታፊ በሆኑ ታጣቂዎች እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በመሸጉት የሽብርና የማንነት ተኮር ጥቃት አቀናባሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ መማክርቱ አሳስቧል።

የዜጎች ደኅንነት የማስጠበቅ የቅድሚያ ግዴታ የመንግሥት መሆኑን በማስገንዘብ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት ይህን ግዴታቸው በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብሏል።

እየተፈጸሙ ያሉ ተከታታይና የተቀናጁ ጥቃቶች አማራን የማጥፋት፣ አማራን የማዋከብና ሠላሙን የመንሳት፣ የክልሉን መንግሥትም በተለያዩ አቅጣጫዎች የመወጠርና የማፍረስ፡ የክልሉን ልዩ ኃይል የማዳከም ሴራዎች አካል መሆናቸውን መማክርቱ አመላክቷል።

የፌደራል መንግሥት እና የሁሉም ክልል መንግሥታት እንዲሁም የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በአማራ ላይ ተከታታይ እና ያልተቋረጠ የዘር ማጥፋት ተግባሮች እየተፈጸመ መሆኑን እየተመለከቱ ጥቃቶችን በትክክለኛ ስማቸው ከመጥራት ጀምሮ በግልጽ አለማውገዛቸው መማክርቱን እና የአማራ ሕዝብን በእጅጉ ያሳዘናቸው መሆኑን ገልጿል።

ሕዝቡ በየጊዜው በተጠናና በተቀናጀ ሁኔታ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በንቃት በመከታተል በተደራጀ ሁኔታ ራሱን እንዲከላከልና ከጸጥታ አካላት ጎን እንዲቆም እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በሚችለው ሁሉ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርቧል።

በተደጋጋሚ የሚፈፀሙትን የዘር ማጥፋትና የሽብር ተግባራት በዘላቂነት ለማስቆም የክልሉን ሕገመንግሥት ማሻሻል ጨምሮ ተገቢ የሆኑ ሥርዓታዊ እና መዋቅራዊ ማስተካከያዎችን ማድረግ እንደሚገባ መማክርቱ አሳስቧል።

(አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top