Connect with us

አደብ ያላስገዛው መንግስትና አለቅጥ ኃያል ያደረገው የፌስ ቡክ ሠራዊት ያገነነው ኦነግ ሸኔ!…

አደብ ያላስገዛው መንግስትና አለቅጥ ኃያል ያደረገው የፌስ ቡክ ሠራዊት ያገነነው ኦነግ ሸኔ!...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አደብ ያላስገዛው መንግስትና አለቅጥ ኃያል ያደረገው የፌስ ቡክ ሠራዊት ያገነነው ኦነግ ሸኔ!…

 

አደብ ያላስገዛው መንግስትና አለቅጥ ኃያል ያደረገው የፌስ ቡክ ሠራዊት ያገነነው ኦነግ ሸኔ!…

ከተማ መስራት ቢያቅትን እንዴት ከተማን ከቃጠሎ መጠበቅ ይከብዳል?

(ስናፍቅሽ አዲስ – ድሬቲዩብ)

ኦነግ ሸኔ አቅሙ ምንድን ነው? የህግ የበላይነት አለመከበር፤ በዳቦ ስም መንቆለማመጥ፣ ያለ ልክም መናቅ ያለ ልክም መከበር ይመስለኛል፡፡ መንግስት ሰው ሰው አርዶ የውንብድናውን ስም ግጭት ይለዋል፡፡ ግጭት በሁለት ወገኖች መካከል ያለ ጠብ እንጂ አንዱ አሳዳጅ አንዱ ተሳዳጅ የሚሆንበት ጥፋት አይደለም፡፡

ኦነግ ሸኔ በመንግስት በኩል አለ ልክ ተንቋል፡፡ ያ ንቀት አራት ኪሎን ሊገዘግዝ ሰሜን ሸዋ ደርሷል፡፡ አበለጽጋለሁ ያለው መንግስት እንዲህ ተንከርፎ እንኳን ለሀገር ለራሱም ሳይሆን ትቢያ እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ አለ ልክ መናቁን መልሶ ይመልከተው፡፡

መንግስት ሀገሩን ሰላም ካላደረገ ተዘፍዝፎ መኖር ምን ይጠቅመዋል? ከተማ መስራት አለመቻል ስንፍና ይባል ወይም አቅመ ቢስነት መሳሪያ ይዞ መሳሪያ በያዘ አካል ከተማ ሲቃጠል አለመታደግ ግን ስሙ ምንድን ነው?

ግብጽ ከሚሴ ላይ ጦር ካምፕ መስርታለች፡፡ ወለጋ ላይ ውጊያ ጀምራለች፡፡ መተከልና ጭልጋ የቻለችውን እያደረገች ነው፤ ታዲያ ኢታማዦር ሹሙ ለሀገር ወደ ኋላ አንልም የሚሉት የት ስትደርስ ሊወጓት ነው?

ኦነግ ሸኔ ብዙ ቦታ የሚሰጠው ልዩ ሰራዊት አይደለም፡፡ የጥፋት ቡድኑ መንግስታዊ ሹሞች ቢደግፉትም፣ ግብጽ አስታጥቃ ቀለብ ብትሰፍርለትም፣ የወደቀችው ህወሃት ከተደበቀችበት ጎሬ ሆና አይዞህ ብትለውም ኢትዮጵያን የማመስ አቅም የሰጠው ግን የህግ የበላይነት አለመከበርና የመንግስታችን ሆዴ ካልጎደለ ባይነት ነው፡፡

አማራ አሁን አንድም ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመደገፉ የሚሰቃይ ህዝብ ነው፡፡ አንድም የኦነግ ሸኔ ሃይል አማራን ካመስከው ግድቡ እልባት ያገኛልና መሬት ውረር ተብሎ በትርክቱ ላይ የግብጽ ስውር እጅ ያረፈበት ነው፡፡ ይሄንን ደምሮ ሀገር ማዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚመሩት መንግስት ድርሻ ነበር፡፡ በሺህ የሚቆጠር ጠባቂ አለኝ ብሎ ከተማ ሲቃጠል ህንጻ እየመረቁ ውሎ ማደር የሮማን ቃጠሎ በሙዚቃ እንዳጀበው ንጉሥ መሆን ነው፡፡

ሌላው የኦነግ ሸኔ ጉልበት የአማራ ፌስቡክ ሰራዊት ነው፡፡ ይኑረውም ፎቶ ሾፕም ይሁን፤ ሀገር ውስጥም ይነሳ የተጠለሉበት በረሃ ብቻ እነሱ ለስነ ልቦና የሚለቁትን ፎቶ እየተቀባበሉ ገበሬው ራሱን እንዳይከላከል ከአንተ የባሰ ሃያል መሳሪያ የያዘ ጉልበተኛ መጣ እያሉ ፕሮፖጋንዳውን ማሳለጥ ያስተዛዝባል፡፡

እነሱ ለማስደንገጥ የሚለጥፉትን ፎቶ ያልደረሰበት እያደረሰ ወገኑን የሚያሸብረው የአማራው አክቲቪስት ነው፡፡ ግዝፈታቸውን ያብራራል የሀገር መከላከያ ሠራዊት የስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ የክልሉ ልዩ ሃይል አሁን ህዝቡን መታደግ አልችልም ብሎ እንዲብረከረክ ይቀሰቅሳል፡፡ ኦነግ ሸኔ በዚህ መካከል በመንግስት ችላ ባይነት ያሻውን ያደርጋል፡፡ 

የመንጋውን ሃያልነት በሰበኩት የአማራ ልጆች ሳቢያ የአማራ ገበሬ ራሱን መከላከል የማይቻል ይመስለዋል፡፡ መከላከያ ወገን ልታደግ ብልም አልቃለሁ እንጂ ምን አመጣለሁ እንዲል ይገደዳል፡፡

አሁንም ኦነግ ሸኔ ሃያል አይደለም፡፡ አርባ አመት ተዋግቶ የቀበሌ መንግስት መሆን ያቃተው የጥፋት ቡድን ነው፡፡ ታዝሎ ገብቶ በስውር የፖለቲካ ደባ ጀርባ በመሆን መንግስት ለመጣል የሚዋትት ከርታታ ነው፡፡ ጦርነትን አያውቃትም፤ ቤት አቃጥሎ ከተማ አንድዶ የሚሞቅ እንጂ ከተማ ይዞ ሀገር የሚመራ አይደለም፡፡ 

ህጻናትና ሴት የሚገድል እንጂ ከወንድ የሚዋደቅ አይደለም፡፡ ያገነነው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የከበበ እና ጠቅላዩም መጣል የሚሻ ስውር የኦሮሞ ብልጽግና ደባ ነው፡፡ ያገነነው የግብጽ ቀለብና ትጥቅ ነው፡፡ ከዚያ ሲያልፍ ዝናውን ያናኘው የፌስ ቡክ ሰራዊት ነው፡፡ መንግስት ሆይ ለራስህ ስትል ልክ አስገባው፡፡ 

ፎቶ፡- ኢንተርኔት

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top