Connect with us

እውቀታቸው  በነፃ ለሚለግሱት ሰው ከተማ አስተዳደሩ ማስተማርያ ቦታ ይስጣቸው !!!

እውቀታቸው በነፃ ለሚለግሱት ሰው ከተማ አስተዳደሩ ማስተማርያ ቦታ ይስጣቸው !!!
ዘ-ኮረም ክብረት

ዜና

እውቀታቸው  በነፃ ለሚለግሱት ሰው ከተማ አስተዳደሩ ማስተማርያ ቦታ ይስጣቸው !!!

እውቀታቸው  በነፃ ለሚለግሱት ሰው ከተማ አስተዳደሩ ማስተማርያ ቦታ ይስጣቸው !!!

ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎቹን በሚሊኒየም አዳራሽ  ባስመረቀበት ወቅት  ‹‹መማር ያስከብራል›› የሚለውን ዜማ በከፍተኛ ድምጽ በሽዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአንድነት ቆመው እያጨበጨቡ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት   አቶ ተስፋዬ አበበ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የክብር ዶክትሬት መገለጫ ገዋን  እያለበሷቸው ነበር፡፡

ከ500 በላይ ግጥምና ዜማዎችን ሠርተው ለተለያዩ አርቲስቶች የሰጡ ሲሆን ‹‹ መማር ያስከብራል›› የሚለውን ዜማ  አንደኛው ስራቸው እርሳቸውን ለማጀብ ተማሪዎች      አጋጣሚውን  ተጠቅመውበታል፡፡ 

ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ከፍተኛ አሻራቸውን ካስቀመጡ ብርቅዬ የኪነጥበብ ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡እኝህ አንጋፋ አርቲስት የኪነጥበብ ፍቅር ላለው ጥበብ ለተጠማ ሰው ያለምንም የትምህርት ክፍያ በነጻ ላለፉት 53 አመታት ያለማቋረጥ  የኪነጥበብ ትምህርት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እየሰሩ ያሉ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡

ክቡር ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) ካስተማሯቸው  አንቱታ ካተረፉ አንጋፋ አርቲስቶች መካከል ወጋየው ንጋቱ ፣ ፍቃዱ ተ/ማርያም ፣ ፋንቱ ማንዶዬ፣ አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ሽመልስ አበራ፣ አስቴር አወቀ፣ይገረም ደጀኔ ፣ታሪኩ ብርሀኑ፣ትግስት ግርማ፣ መሰረት መብራቴ፣መሳይ ተፈራ፣ዘቢባ ግርማ፣እና ሌሎችን በርካታ  የኪነጥበብ ባለሙያዎች  ይገኙበታል፡፡

እኝህ የኪነጥበብ አባት በያኔው ጊዜ ከላይ የገለጽኳቸው አንጋፋ ባለሙያዎች  አስተምረው ለቁምነገር እንዲደርሱ ያደረጉት በደሳሳ ቤት ውስጥ ነው፡፡ አሁን ግን የተቀበሏቸው ተማሪዎች አስተምረው ለማስጨረስ እንዲሁም ሌሎች ተተኪ የኪነጥበብ ሰዎች ለማፍራት   ከአቅም በላይ በሆነ የማስተማርያ የቦታ ችግር ገጥሟቸዋል፡፡

ለማስተማር የተቀበሏቸው ወጣቶችም ቢሆን በቦታ እጥረት ምክንያት  ተማሪዎቻቸው  ለመበተን እየተገደዱ  መሆናቸውን በኪነጥበቡ ዘርፍ ያሉ የቀድሞ ተማሪዎቻቸው እና አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስተማርያ የሚሆን ቦታ እሰጣለሁ ብሎ ቃል የተገባላቸው መሆኑን የሚያወሱት የፋዘር ተማሪዎች  የከተማ አስተዳደሩ የገባውን ቃል ሊፈጽም ባለመቻሉ የማስተማርያ ቦታ በማጣት ምክንያት ትምህርት ቤቱ ስራውን ለማቆም እየተገደደ መሆኑን በማህበራዊ ድረገጽ የሚወጡ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገባውን ቃል  ሊፈጽም ይገባል የሚሉ የመልካም ስራ ጥሪ ሁሉም ማስተጋባት አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡

እኔ በፋዘር ባልማርም ፋዘር ያስተማሯቸው ሰዎች ለሀገራቸው ትልቅ አሻራ እያበረከቱ  መሆናቸው በአይኔ ተመልክቻለሁ፡፡  አቅሙ ያላችሁ በአቅማችሁ በማስተባበር ለኪነጥበብ ትምህርት ቤት የበኩላችሁን ተወጡ፡፡ እሳቸው አገር ናቸው፡፡

ክቡር ዶክተር አርቲስት ተስፋዬ  በ1947 ዓ.ም. የ17 ዓመት ወጣት ሳሉ በቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአሁኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተምረዋል፡፡ በቴአትር ቤቱ በተዋናይነት ከሠሩ በኋላ ወደ ፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃና ቴአትር ቡድን ተዛውረው ለዓመታት ሠርተዋል፡፡

አርቲስቱ ከ500 በላይ ግጥምና ዜማዎችን ሠርተው ለተለያዩ አርቲስቶች ሰጥተዋል፡፡ ከነዚህም ‹‹ኢትዮጵያ ሀገራችን›› በሒሩት በቀለ የተዜመ፣ ‹‹ጣሪያና ግርግዳ›› በብዙነሽ በቀለ የተዜመ፣ ‹‹ያም ሲያማህ ያም ሲያማህ›› በጥላሁን ገሠሠ የተዜመ፣ ‹‹እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ›› በዘሪቱ ጌታሁን የተዜመ፣ ‹‹ያ ልጅነት በጊዜአቱ›› እንዲሁም ‹‹መማር ያስከብራል›› ይገኙበታል፡፡

ላለፉት ዓመታት በርካታ አርቲስቶችን ያፈራው ‹‹የቴአትር ዕድገት ክበብ›› የአሁኑ ‹‹የተስፋዬ አበበ የኪነ ጥበብ ማዕከል›› በቦታ ጥበት ችግር ውስጥ ወድቋል፡፡ መልካም ለሚሰሩ ሰዎች ሁሉም እገዛውን ያድርግ፡፡

( ዘ-ኮረም ክብረት ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ/ም)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top