Connect with us

ሥልጠና እየተካሄደ ነው

ሥልጠና እየተካሄደ ነው
ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል

ዜና

ሥልጠና እየተካሄደ ነው

ሥልጠና እየተካሄደ ነው

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ አስተባባሪ ግብረሀይል የምርጫ ክልል 28 የአስተባባሪዎች ሥልጠና መርሐግብር በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የኢየሩሳሌም ሕፃናት ማኀበረሰብ ልማት ድርጅት የሥልጠና ማዕከል በመካሄድ ላይ መሆኑ ተሰማ።

ሥልጠናው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ እና ሥርዓት፣ የምርጫ አስተባባሪዎች በሒደቱ  መከተል የሚገባቸው የሥነምግባር ሁኔታ እና የመሳሰሉት ላይ ያተኮረ ነው።

ዲያቆን ዳንኤል በዐዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ክልል 28 (የካ ወረዳ 9፣10፣11፣12 እና 13 እና ቦሌ ወረዳ 10 በድምሩ ከ108 በላይ ንዑስ ምርጫ ጣቢያዎችን በሚሸፍን ቦታ ለሕዝብ እንደራሴ ም/ቤት በግል እንደሚወዳደር ይታወቃል።

የዛሬው የቢሾፍቱ የሥልጠና መርሐግብር ተሳታፊዎች የኮሮና ወርሽኝ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ባሟላ መልኩ ማስክ፣ ሳኒታይዘር በማቅረብ የጤና ሚ/ር የኮቪድ መመሪያን በጠበቀ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ከአስተባባሪ ኮምቴው የተገኘ ዜና ጠቁሟል።

የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል የመጀመሪያው የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሐግብር መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ማካሄዱ የሚታወስ ነው።

 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top