Connect with us

የአፋር ክልል ምላሽ

የአፋር ክልል ምላሽ
አሐዱ ራድዮ 94.3

ዜና

የአፋር ክልል ምላሽ

የአፋር ክልል ምላሽ

የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን ለመሸሸግ የተደረገ ሴራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡

የአፋር ክልል መንግስት እያረገ ያለው የጦር ነጋሪት ጉሰማ የክልሉ መንግስት አሰላለፍ ከየትኛው ወገን እንደሆነ እንድንጠራጠርና እንድንጠይቅ የሚያስገድድ ነው ሲል የሱማሌ ክልል መገለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

አሐዱም በሁለቱ ክልሎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማጣራት ሞክሯል፡፡

የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአጎራባች ክልሎችና የግጭት አፈታት ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሰመሬ ከባለፈው አርብ ጀምሮ በዜጎች ላይ ግድያና ማፈናቀል የተፈፀመ ሲሆን ከ35 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሲቆስሉ በርካቶች ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡

የአፋር ብሄራዊ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ የሶማሌ ክልል በ2011 ዓ.ም አከባቢዎችን በኃይል ለመያዝ አስፈላጊውን ጥረት አደርጋለው ሲል መግለጫ ማውጣቱን አስታውሰው በሱማሌ ልዩ ኃይሎች የአፋር ህዝብ እየሞተና እየተፈናቀለ ነው ብለዋል፡፡

ጥፋተኝነትን ለመሸሽ መግለጫ ማውጣት ከተጠያቂነት አያስመልጥም በማለት ሂደቱ ተገቢነት እንደሌለው አቶ አህመድ ገልጸዋል፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፅኑ ፍላጎት አለኝ ሲል ለአሐዱ የገለጸ ሲሆን በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል መንግስት ችግሩን ፈትቶ የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚፈልግ ገልፃል።

(አሐዱ ራድዮ 94.3)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top