Connect with us

ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ
አዲስ ቲቪ

ዜና

ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

ሕዝበ ሙስሊሙ መጪውን የረመዳን ጾም በፍቅር፣ በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራትን በማከናወን እንዲያሳልፍ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ፡፡

ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በቀጣዩ ሣምንት የሚጀመረውን 1442ኛውን የረመዳን ጾም መግቢያን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በሚጾምበት ጊዜ ለሰዎች እያዘነና እየተረዳዳ ሊያሳልፍ ይገባል” ብለዋል፡፡

በጾም ወቅት በጎ ተግባራትን ማከናወን ጾሙ ትክክለኛና በፈጣሪ ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኝም ገልጸዋል።

“በረመዳን ጾም ወቅት የተለያዩ ችግሮች በመፍጠር ሙስሊሙ ከጾሙ እንዲስተጓጎል ማድረግ አይገባም” ያሉት ቀዳሚ ሙፍቲው፤ ሁሉም በየራሱ መስጂድ መስገድና የጾሙን ወቅት ማሳለፍ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።

ከወንጀልና ከተለያዩ በደሎች በመቆጠብ ወደ አምላክ መቅረብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ጾም ለኮቪድ-19 ተጋላጭ እንዳይሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በቤትም ሆነ በመስጊድ በሚሰባሰቡበት ወቅት ለኮቪድ-19 የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን መከተል እንደሚያስፈልግም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የዜጎችን ሞትና መፈናቀል ያወገዙት ቀዳሚ ሙፍቲው፤ የመንግስት አካላት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

“የሃይማኖት አባቶች ሕዝቡን ማስተማር ይገባቸዋል” ያሉት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ፤ ለአንድነትና ለሠላም ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(አዲስ ቲቪ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top