Connect with us
#ድሬደዋ
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

ዜና

#ድሬደዋ

#ድሬደዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማያከብሩ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡

የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በተመለከተ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በሀገራችን ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ወደ 32 ሺ 209 ለሚሆኑ ሰዎች በአስተዳደራችን ምርመራ መደረጉንና ከነዚህም ውስጥ 3718 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው አስፈላጊው ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ሰዓት ድረስ 45 ሰዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ግን በዚህ ሶስት ሳምንት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በዚሁ ሶስት ሳምንት 565 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህም ቫይረሱ የሚገኝባቸውን ሰዎች በፐርሰንት 45% የደረሰ ሲሆን ይህም ከመቶ ሰው 45ቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የሚያመላክት ነው፡፡ 

በዚሁ ሶስት ሳምንት ውስጥ 15 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው ማለፉንና ይህ ቁጥር የኮቪድ ናሙና ሰጥተው በኮቪድ ህክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ የሞቱትን እንጂ በተለያዩ ተቋማትና ህክምና ሳያገኙ በቤታቸው የሚሞቱትን ቁጥር እንደማይጨምር፤ በተለያዩ ምክኒያቶች ሰሞኑን ሰዎች እየሞቱ መሆኑንና ይህም ሳይመረመሩ በኮቪድ-19 ምክኒያት የሚሞቱ ወገኖቻችን መኖራቸውን ነው፡፡

በዚሁ ሶስት ሳምንት ውስጥ በኮቪድ-19 የመያዝ ቁጥር መጨመር፣ በኮቪድ-19 ህመም ምክኒያት ከፍተኛ የህመም ደረጃ ላይ የደረሱና ኦክስጂን የሚያስፈልጋቸው ህሙማን መጨመር እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሞት ቁጥርም የጨመረ በመሆኑ በሽታውን በመከላከል እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ማዳን እየቻልን ያጣናቸውን ወገኖቻችንን እየጨመሩ ነው፡፡ 

በመሆኑም የአስተዳደራችን ነዋሪእራሱንና ሌሎችን ከወረርሽኙ ለመከላከል ቅድሚያ በመስጠት የመከላከያ መንገዶቹን እጅን መታጠብ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግና ርቀትን መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዋ ሁሉም ነዋሪ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያስከትለው የጤና ችግርና ሞት እራሱንና ሌሎችን በመከላከል እንዲሁም ከህግ ተጠያቂነት እንዲድን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኤ.ፊ.ድ.ሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ሹርኬ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 30/2013 በተመለከተ የግንዛቤ መስጫ ትምህርቶችን ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ቦታዎች ላይ በተከታታይ ቀናት የመስጠቱ ሥራ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮን ጨምሮ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚከናወን ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት ወረርሽኙን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ ለማስፈፀም በተሰጠን ኃላፊነት መሰረት ህግን የማስከበር ሥራ ለመስራት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡ የስርጭት መጠኑንና የሞት መጠኑን ለመቀነስ በአግባቡ እራሱንና ሌሎችንም ከቫይረሱ መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መገራ በበኩላቸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከተማችን ድሬዳዋ ሞትን እያስከተለ አደገኛ አዝማሚያ ላይ ያለ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመዘናጋት ወጥቶ እራሱንና ሌሎችንም መከላከል እንደሚገባና በትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ፣ በመገበያያ ስፍራዎች፣ በሆቴሎች እና በመንግስት መስሪያቤቶች እንዲሁም ማህራዊ ጉዳዮች በሚከወኑባቸው ስፍራዎች ሁሉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በማድረግና ርቀትን በመጠበቅ እንዲሁም እጅን በመታጠብ ወረርሽኙን ለመግታት የራሱን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

 ኮሚሽነሩ ጨምረውም የግንዛቤ መስጫ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ ባሻገር በማን አለብኝነት የሚደረጉ የኮቪድ-19 መመሪያ ጥሰቶችን በሚፈፅሙ ላይ አስፈላጊውን በህጉ የተቀመጡ ቅጣችን ከሚመለከታቸው የህግ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን የምናስፈፅም ይሆናል ብለዋል፡፡ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ገደብን በተመለከተ በቀጣይ በምን አግባብ መቀመጥ አለበት የሚለውን በድሬዳዋ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወደፊት ተወስኖ የሚገለፅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

(ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top