Connect with us

ጎበዝ ግጭትን ጠልቶ የሰላም ምክክር ነቅፎ ይሆናል እንዴ?

ጎበዝ ግጭትን ጠልቶ የሰላም ምክክር ነቅፎ ይሆናል እንዴ? የአማራና የኦሮሚያ ክልል መሪዎች እንኳን ተገናኝተው መከሩ፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ጎበዝ ግጭትን ጠልቶ የሰላም ምክክር ነቅፎ ይሆናል እንዴ?

ጎበዝ ግጭትን ጠልቶ የሰላም ምክክር ነቅፎ ይሆናል እንዴ?

የአማራና የኦሮሚያ ክልል መሪዎች እንኳን ተገናኝተው መከሩ፤

(እሱባለው ካሳ -ድሬቲዩብ)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅ እግር ወደሌለው ምዕራፍ ገብቷል፡፡ ማንም እጁ ላይ ባለው ሞባይል ብሔሬን ካላሰለፍኩ ብሎ በተሰለፈበት በዚህ ክፉ ጊዜ ፖለቲከኛ እንደመሆን አበሳ የለም፡፡ አሁን ፖለቲከኞች ህዝቡ ምን ይፈልጋል የሚለውን ለማጤን እድል ተነፍገዋል፡፡ ሁሉም የሚያስወቅስ በመሆኑ ተረጋግቶ ሀገር መምራት አበሳ እየሆነ መጣ፡፡

በወለጋው የማንነት ጥቃትና የወገኖቻችን ግድያ የአማራ ክልል መሪዎች ሲብጠለጠሉ ሰምተናል፡፡ በዚህ የዴራሊዝም ሥርዓት የፌዴራል መንግስት እንኳን ዘው ብዬ ከአንዱ አንዱ ጋ አልገባም በሚልበት በዚህ የፖለቲካ እሳቤ ድፍን ኢትዮጵያ ኮሽ ባለ ቁጥር አቶ አገኘሁ ተሻገርና ፓርቲያቸውን እንዲሁም የክልሉን መንግስት ማብጠልጠልና የራስን ፖለቲካ ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት እንዴት ያለ የትግል ስልት እንደሆነ ግራ ገብቶናል፡፡

በዚህ ሳያበቃ ገና ስልጣን ያልያዘ ጭቆና ገፍቶት ለወገኔ መድረስ አለብኝ ብሎ አበሳውን የሚያየውን አብንን ጭምር መግለጫ ብቻ እያሉ ማሳቀቁም ሌላ ስውር ዓላማ ያለው የጠላት ተልእኮ እንደሆነ ማጤኑ ደግ ነው፡፡

አብን ማድረግ የሚችለው ግድያውን ማውገዝ ነው፡፡ ከዚህ የተሻለ አማራጭ አለኝ እና ለአማራ እቆረቆራለሁ የሚል አካል ሃላፊነቱን ወስዶ የድርሻውን ይወጣ በተረፈ ለህዝብ የሚታገሉ አመራሮችንና ፓርቲዎችን ለህዝብ በመቆርቆር ስም መንቆሩ ያስተዛዝባል፡፡

የአማራ ብልጽግና አሁን ክልሉን በሰላም እየመራ ነው፡፡ አቶ አገኘሁ እና ጓዶቻቸው የተሾሙት ክልሉን ሊመሩ ነው፡፡ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እንደ ሰላም አስከባሪ መሳሪያ ታጥቀው ከጠረፍ ጠረፍ እንዲታኮሱ መጠበቅም የቅንነት ሀሳብ አይመስልም፡፡

አማራ ብልጽግና ከብልጽግና ይውጣ የሚለው ጩኽት ስካር ነው፡፡ እነ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደ እነ ዶክተር ደብረ ጽዮን የት እንዳለ የማይታወቅ የፌስ ቡክ ታጋይ ጻፈ ብለው እንዲህ ያለውን እብደት አይሞክሩትም ብልጽግና አማራ ፖለቲካ አብሮ የሰራው ፓርቲ እንጂ እቁብ አይደለም፡፡

የአቶ አገኘሁና የአቶ ሽመልስ ምክክርና ውይይት ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለውጥ ባያመጣ እንኳን ዳርና ዳር ቆሞ ከመነታረክ መቀራረብ የሰለጠነ መንገድ ነው፡፡ መቀራረብ ችግር ባያስወግድ እንኳን ትንሽም ቢሆን ይቀንሳል፡፡ ትንሽ ችግር መቀነስ ማለት ትርጉሙ የአንድ ሰው ሞት እንኳን ማዳን ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ሰውስ ለምን ይሞታል? አቶ ሽመልስና አቶ አገኘሁ ቁጭ ብለው ቢነጋገሩ ምን መሬት እንዳይደረመስ ነው የአንድ ሰው ሞት ሊያስቀር ቢችል እንኳን ጥቅም ያለውን ውይይት ቢዘህ ደረጃ የምንጫጫበት?

የፖለቲካችን መፍትሔ ሁለት አይነት ነው አንዱ ጨርሶ እሳቱ የማይበላው እሳቱን አንድደን መፍትሔውን እናምጣ የሚለው ጠብ ቆስቋሽ ነው፡፡ ሌላው ሞት ባላስቀር ሞት ልቀንስ ብሎ ከበጣም መጥፎ በጣም መጥፎውን እንኳን እየመረጠ ወገን ለመታደግ ይጥራል፡፡

አብንም ሆነ አማራ ብልጽግና የሚወቀሱበት አንዳች ምክንያት የለም፡፡ አብን አሁን የሚጠበቅበት መንግስት ለመሆን ራሱን አዘጋጅቶ ምርጫን ጥሩ ተወዳዳሪ መሆን ነው፡፡ በዚያ ስራ ተጠምዷል፡፡ አብን ታጥቆ ወገኑን ለመታደግ የተደራጀ ፓርቲ አይደለም፡፡ አብን በሀሳብ በህግና በዲሞክሲ ሞግቶ ቀን ቢፈጅም አማራን እታደጋለሁ ያለ ነው፡፡

አማራ ብልጽግናም እየሆነ ያለውን ነገር እንደ ክልል መሪ አውቃለሁ የጋራ ትግል ይፈልጋል እንታገል ሀገር የሚያፈርሱ ወገኖች እየፈተኑን ነው ብሎ ነግሮናል፡፡ ከቻልን እንደግፋለን፤ ካልሆነ የመጣ ይምጣ ሀገር አፍርስ ካልነው ከትህነግ እና ከግብጽ በምን ተለየን ለማንስ ነው ይሄ ሁሉ ምክርና ሀሳብ? ጎበዝ መደማመጥ ካልቻለን እንዴት ከሞት ማምለጥ እንችላለን?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top