Connect with us

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች እየመከሩ ነው

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች እየመከሩ ነው
ኦቢኤን

ዜና

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች እየመከሩ ነው

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች እየመከሩ ነው

የኦሮሚያና የአማራ ክልል አመራሮች  የጋራ ልማትና ሰላም ላይ በአዲስ አበባ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡

በምክክር መድረኩ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል በትብብር መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

በሁለቱም ክልሎች በሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት ማስቆም፣ የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መውሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ፍትህ እንዲያኙ እና ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቤት ንብረታቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም እንዲሁም በሁለቱም ክልሎች ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አኳያ በትብብር ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ክልሎች አመራሮች በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣ አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የውይይቱ አንኳር ጉዳዮች ናቸው ተብሏል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር፣ እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top