Connect with us

የአፋርና ሱማሌ አርብቶ አደሮች ግጭት፡፡

ለተጨማሪ ዜና እና መረጃዎች
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የአፋርና ሱማሌ አርብቶ አደሮች ግጭት፡፡

የአፋርና ሱማሌ አርብቶ አደሮች ግጭት፡፡

ዛሬም ያለ ምክንያት ሞት፤ ምክንያት ባላቸው የፖለቲካ ሴረኞች ደባ፡፡ 

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)

እዚህም እዚያ ሀገርና ህዝብን ማስጨነቁ ቦታም ብሔርም ሳይመርጥ ቀጥሏል፡፡ የትህነግ ፈንጂ ወቅትና ቀን እየጠበቀ ሲፈነዳ እያየን ነው፡፡ በአፋርና እና በሱማሌ ክልል ድንበሮች ረዥም አመት የዘለቀ ግጭት ነበር፡፡ መፍትሔ የለሹ በብሔረሰቦች ስም የሚነግደው ህገ መንግስትና የብሔር መንግስት ብዙ ደም ባፋሰሰበት ያለፉት አመታት ተራ የአጎራባች አካባቢ ነዋሪዎች ግጭት መንግስታዊ እጅ ጭምር እየገባበት እዚህ ደርሷል፡፡

ሰሞኑን በአፋርም በሱማሌም ክልሎች በኩል የበለጠ የተጎዳሁት እኔ ነኝ በሚልና አንዳቸው የሌላቸውን ልዩ ሃይል በሚከስ መልኩ መግለጫዎች ተከታትለው ነበር፡፡ የክልል መሪዎቹ ችግሩን ለማብረድ በጋራ መክረው እርቅ ማውረዳቸውንም እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያው መንደር ሲንሸራሸር ሰማን፡፡

ደስታው ውሎ ሳያድር ደግሞ በአፋር በኩል ሌላ ብዙ ሞት ብዙ ወገን እንደወደቀ ዜና ሰማን፡፡ የአርብቶ አደሩ ግጭት በራሱ የተነሳ ከሆነ በራሱ የሚበርድበት ብዙ ባህላዊ ስርዓት አለው፡፡ ችግሩ አርብቶ አደሩን በማጋጨት ፖለቲካ ለማትረፍ የታቀደ ሴራ ካለ ግን የወገን ነፍስ ይወድቃል እንጂ መፍትሔ አይመጣም፡፡

የትህነግን የኦነግንና የኡጋዴንን አማጺያን የሚረዱ አደረጃጀቶች በትናንትናው የኪንሺያሳ ስምምነት መፋረስ ጮቤ ረግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሃይል ከአብዬ ግዛት ይውጣልኝ የሚለውን የሱዳን ጥያቄ ከሀገር ውስጥ አያሌ ግጭቶቻችን ጋር አጣጥመው መልሰው ነግረውናል፡፡

ከየትኛው በርሃ እንደሆነ የማይታወቀው የአማጺያኑን ዝግጅት የሚሳይ ምስልና ድምጽ ሲለቁልን እንዲህ ያሉ የሀገር ውስጥ ሽኩቻዎችን አጣጥመው እያካፈሉን ነው፡፡ 

ድምሩ ከባድ እንደሆነ ለመረዳት ሊቅ መሆን አይጠይቅም፡፡ አፋር እንደ አማራ ሞትን እንዲቀምስ የተደረገበትና በወንድማማቾቹ በአፋርና በሱማሌ ህዝቦች መካከል ግጭቱ እልባት እንዳያገኝ እየተሰራ ያለው ደባ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ምስራቅ አፍሪቃን የሚጎዳ ከባድ ችግር ነው፡፡

አርብቶ አደሮቹ የአፋርና ሱማሌ ህዝቦች በባህል በአኗኗር በታሪክ እና በእምነት ብዙ አንድነትና የወል እሴት ያላቸው ናቸው፡፡ በፖለቲካ ቁማር ከውስጣቸው የሚነሱም ሆነ ከርቀት እጃቸውን የሚያስገቡ ሃይሎች ለመገዳደል ምክንያት የሚሹ ጎረቤቶች አድርገዋቸዋል፡፡

ከአዲስ አበባ አዋሽ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድ ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር የሚገጥመው በዚሁ የአፋርና ኢሳ ግጭቶች ሳቢያ ነው፡፡ ብዙ ማኅበራዊ ቀውስ አለመረጋጋትና ሞት እንደ ቀላል በየጊዜ ሲመዘገብበት ኖሯል፡፡ መፍትሔው ግን አሁንም አልመጣም፡፡

የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ያለበት መጀመሪያ የሁለቱም ህዝቦች የባህል አባቶችና የእምነት መሪዎች ምን እናድርግ ብለው እንዲመክሩና ከውጪም ከውስጥም እነሱን መጠቀሚያ አድርጎ በማገዳደል ኢትዮጵያን ማክሰር የሚፈልጉ ሃይሎችን ደባ እንዲረዱ ማድረግ ነው፡፡ ሁለቱም ህዝቦች በውይይት የሚያምን የሰለጠነ ባህል አላቸው፡፡ ለባህልና ለጎሳ መሪዎች ውሳኔ የሚገዙ መሆናቸው ደግሞ ችግሩን ከልብ ካለቀሱ እንባ እንዳይገድ ያድርገዋል፡፡

ይህ ካልሆነ አብዬ ያጉረመረመው፣ ትህነግን በርቺ የሚለው፣ የኦሮሞ ነጻ አውጪን ግፋ ብሎ የሚያስታጥቀው፣ አማራን የሚያሳርደው የግብጽ ስውር እጅ አዋሽን ተከትሎ ወደ መሃል ሀገር እንደሚገባ አያጠራጥርም፡፡ አሁን ጠላቶቻችን በውስጥ ፍላጎቶቻችን እየተጋሉን ነው፡፡ ከጣሉን ማንም አይተርፍም የምንወድቀው እንደ ህዝብ ነው፡፡ እንደ ሀገር ለመትረፍ እንደ ሀገር እንስከን፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top