Connect with us

የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ፋውንዴሽን ለሆስፒታል መገንቢያ በኦሮምያ መሬት ተረከበ

የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ፋውንዴሽን ለሆስፒታል መገንቢያ በኦሮምያ መሬት ተረከበ
Photo: Social media

ዜና

የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ፋውንዴሽን ለሆስፒታል መገንቢያ በኦሮምያ መሬት ተረከበ

የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ፋውንዴሽን ለሆስፒታል መገንቢያ በኦሮምያ መሬት ተረከበ

ከ6 ዓመት በፊት በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እና ጓደኞቹ የተመሰረተው ኀብረት ለበጎ ፋውንዴሽን በዋንኛነት በኩላሊት ሕመም ለሚሰቃዩ ወገኖች መርጃ የሚሆን ሪፈራል ሆስፒታል ለመገንባት 60 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በትላንትና  ዕለት ተረከበ። 

በሥነሥርዓቱ ላይ የሆስፒታሉ የመሰረት ድንጋይ በለገጣፎ ለገዳዲ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና በአቶ ሰለሞን ቦጋለ ተቀምጧል።

በኩላሊት ሕመም ታመው ሲሰቃዩ የነበሩ በርካታ ወገኖቻችንን ወደ ውጭ በመላክ እያሳከመ የቆየው ሰለሞን ቦጋለ እና ጓደኞቹ ሕብረት ለበጎ የኢትዮጵያውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት በኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ወገኖቻችን በቀላል ወጪ በሀገራቸው እንዲታከሙ ለማስቻል ግዙፍ ሆስፒታል ለመገንባት አስቦ የቦታ ጥያቄ አቅርቦ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል።

ፋውንዴሽኑ ባለፉት 6 ዓመታት 24 ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሕክምና እንዲያገኙ ማድረጉ ተነግሯል።

በሥነሥርዓቱ ላይ የለገጣፎ ለገዳዲ ከንቲባ፣ የኦሮምያ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top