Connect with us

የመንጋ ፍርድ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም!

ከምንም ምድራዊ ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ሃገራችንን ማዳን፣ ኢትዮጵያችንን መጠበቅ ነው!
የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት

ዜና

የመንጋ ፍርድ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም!

የመንጋ ፍርድ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም!

(ከኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት የተሰጠ መግለጫ)

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ በአምቡላንስ ውስጥ ተጭነው የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ይጓዙ በነበሩ ዜጎች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በምንም መሥፈርት ተቀባይነት የሌለው እና የሚወገዝ ኢሰብዓዊ ደርጊት ነው፡፡

በአምቡላንስ ውስጥ የሚጓዝን ታካሚ በመንገድ ላይ አስቁሞ ጥቃት ማድረስ አሳፋሪ ድርጊት እና ወንጀል በመሆኑ በድርጊቱ የተሳተፉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውለው ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተፈጸሙ አጅግ አስነዋሪ እና ኢሰብአዊ የጭካኔ ግድያዎች በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ተቀረፅው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወሩ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

እነዚህን ዘግናኝ ግድያዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማስተጋባት የዜጎችን አብሮ የመኖር እሴት ከመጉዳቱም በላይ በቀልን የሚዘራ መሆኑን ተረድተን ጥላቻንና ጥፋትን ከማባባስ ይልቅ ተመሳሳይ መረጃዎችን ለፍትህ አካላት በማድረስ ወንጀለኞች በሕግ እንዲዳኙ ማድረግ ይገባል ብለን እናምናለን።

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top