Connect with us

ባለስልጣኑ በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ያስጀምራል

ባለስልጣኑ በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ያስጀምራል
የአ/አ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

ዜና

ባለስልጣኑ በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ያስጀምራል

ባለስልጣኑ በ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ያስጀምራል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ጎሮ ድረስ ያለውን አዲስ የመንገድ ፕሮጀክት በ1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የግንባታ ስራውን በዛሬው ዕለት በይፋ ያስጀምራል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 4.9 ኪ.ሜ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን የእግረኛ እና የሳይክል መንገድን ጨምሮ ከ30 እስከ 60 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡ የግንባታ ስራውን አሰር ኮንስትራክሽን የሚያከናውነው ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ዩኒኮን የተባለ አማካሪ ድርጅት የሚከታተለው ይሆናል፡፡

ይህን የመንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ የወሰን ማስከበር ስራውን ጨምሮ የ24 ወራት የጊዜ ገደብ የተያዘለት ቢሆንም ግማሽ የሚሆነውን የመንገዱን ክፍል በ14 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ከመጨረሻ መዳረሻው ጎሮ ሰፈራ አደባባይ በተጨማሪ ከቦሌ ሆምስ ተነስቶ በጉምሩክ በኩል አድርጎ ገርጂ ሮባ ዳቦ ጋር ያለውን ነባር መንገድ የሚያስተሳስርም ይሆናል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ጎሮ ለመሄድ በገርጂ እና ኤምፔሪያል በኩል የሚደረገውን ረጅም ጉዞ ከማስቀረቱም በላይ በአካባቢው ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡(የአ/አ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top