Connect with us

“ከሐሰተኛ ብር ተጠንቀቁ” የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮምሽን መልዕክት

የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮምሽን

ዜና

“ከሐሰተኛ ብር ተጠንቀቁ” የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮምሽን መልዕክት

“ከሐሰተኛ ብር ተጠንቀቁ” የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮምሽን መልዕክት

የክልሉ ፖሊስ ለህዝቡ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ወቅታዊ የሆኑ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በህዝብ ግንኙነት የታጀበ የወንጀል መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በክልላችን ዋና ከተማ አሶሳ መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ሀሰተኛ የብር ኖት ከነማባዣ ማሽኑና ከተጠርጣሪው ጋር በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል፡፡

ይህም ስኬታማ ስራ የተከናወነው የአሶሳ ከተማ አስ/ር ፖሊስ መምሪያ ባለፉት ሁለት ወራት የሀሰተኛ የብር ኖት ምንጩን ለማግኘት እልህ አስጨራሽ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስተዋውቋል፡፡ 

ስለዚህ ተጣርጣሪውና ሀሰተኛ ብሩ በቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት የተለያዩ መጠን ያላቸው የሀሰተኛ ብር ኖቶች በተለያዩ የክልላችን ከተሞችና የግብይት ቦታዎች ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ሲውል የቆየ መሆኑን እያስታወስን የሀሰተኛ ብር ኖት ስርጭቱ በሁሉም አካባቢ ይኖራል ተብሎ ስለሚታሰብ ህብረተሰቡ በግብይት ወቅት በገበያ ማእከላት፣ እንዲሁም የወርቅ ቁፋሮና ሽያጭ በሚደረግባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እያሳሰብን።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ወንጀልን ለመከላከል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ስራውን እንዲያከናውንና ይህንንም ወቅታዊ የጥንቃቄ መልዕክት በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲደረግ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት መረጃ ስርጭት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር ኢሳ መርቀኒ  አሳስበዋል፡፡

መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ/ም

 አሶሳ

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top