Connect with us

“በአደባባይ ንግግርና ድስኩር የበለፀገ ሀገርና የተፈታ ችግር የለም!!…”

"በአደባባይ ንግግርና ድስኩር የበለፀገ ሀገርና የተፈታ ችግር የለም!!..."
የገቢዎች ሚኒስትር

ዜና

“በአደባባይ ንግግርና ድስኩር የበለፀገ ሀገርና የተፈታ ችግር የለም!!…”

“በአደባባይ ንግግርና ድስኩር የበለፀገ ሀገርና የተፈታ ችግር የለም!!…”

(የአቶ ላቀ አያሌው ~ የገቢዎች ሚኒስትር መልዕክት)

የዋልያዎችን የድል ብስራት አጣጥመን ሳንጨርስ በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞንና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን አካባቢ ዘርን መሰረት ያደረገ (አማራና አገው) በተለያዩ ጊዚያት በንፁሀን ወገኖቻችን እንዲሁም የእነዚህን ህይወት ለመታደግ ወይም ህግን ለማስከበር በተሰማራው የፀጥታ መዋቅር ላይ ጭምር ግድያ ሲፈፀም ቆይቷል ።

ዛሬም ሌላ ልብን የሚያደማና በእጅጉ የሚያሳዝን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል። ድርጊቱም በምንም ሚዛንና መስፈርት ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪና በታሪክ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው:: ከአሁን በፊት በወያኔና ተላላኪዎች ሲፈፀም እንደነበር ግልፅ ነው:: ነገር ግን ዛሬ ላይ የሚልኩትና ስምሪት ሰጭውን አካል የደመሰሰ መንግስት እንዴት ተለላኪው አለቃ ሁኖ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ  ከአቅሙ በላይ ሊሆን ቻለ ?? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት አለው ብዬ አምናለሁ ።

እኔን ጨምሮ ለወንጀለኞች የተለያዬ የዳቦ ስም እያወጣንና በመግለጫ ጋጋታ እያጀብን ዜጎቻችን በየቀኑ ህይዎታቸው እየተቀጠፈ እኛም ተላምደነው በመቀጠላችን እንጅ ከኢትዮጵያዊያን አቅም በላይ ሆኖ አይደለም የሚል አስተሳሰብ አለኝ። ወንጀለኞችም የሰው ህይወትን እንደ ቅጠል መቁረጣቸውን ተያይዘውታል ።

ይህ ድርጊት በአስቸኳይ ይቆም ዘንድ  ወንጀለኞቹና ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ተቋማትና ሀላፊዎች ወደ ፍርድ አደባባይ መቅረብ አለባቸው ። ሁላችንም የተሰጠንን የህዝብ ሀላፊነት ካልተወጣን በህግ መጠየቅ አለብን ። ይህ ካልሆነ የጅምላ ፍረጃ፣ የጅምላ ውንጀላና ክስ በሌላ በኩልም የጅምላ ከንቱ ውዳሴና ገፅታ ግንባታ እንዲሁም በተግባር የተሠራ ሥራን ከመቁጠር ይልቅ የተነገረን አጉል የተስፋ ቃል መቁጠር በሀገራችን በእጅጉ ጎልቶ እየታየ መጥቷል። 

ጅምላ ፍረጃና ጅምላ ውዳሴ ምንም አበርክቶ የሌለው የሌቦችና የሰነፎች እንዲሁም የስልጣን ጥመኞችና የስልጣን ፈላጊዎች መደበቂያ ኮንክሪት ምሽግ መገንባት ነው። 

ማን ምን ተናገረ ሳይሆን ማን ምን የሚዳሰስና የሚቆጠር (ለኢትዮጵያዊያን) ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ሠራ ብለን መጠየቅ ካልጀመርንና ሥራን አወድሰን ስንፍናን ካልተቸን እንዲሁ በአደባባይ ንግግርና ድስኩር የበለፀገ ሀገርና የተፈታ ችግር የለም ። 

ህዝባችንም ማስተዋል ያለበት በተሰጠን የሥራ ኃላፊነትና ስልጣን ልክ በተጨባጭ የሚታይና የሚዳሰስ ምን ሥራ ተሰራ ? ምን ጎደለ ? ተገቢው ሥራ ያልተሰራውና የህዝቦች ችግር የሆነው በማን ተቋምና በምን ምክንያት ነው ? ብሎ እየለየ ጥያቄውን ቀጥታ ለባለቤቱ ከእነ ሙሉ ኃላፊነቱ ካላቀረበ ጅምላ ውንጀላና ጅምላ ውዳሴ ህዝብን የሚያከብርና  ተጠያቂነትን የሚፈራ እንዲሁም አገልጋይ የሆነ መሪ አይፈጠርም፤ ሀገርም ሰላም አታገኝም፤ እየሆነ ያለውም ይህ ነው ። 

ስለዚህ ሁላችንም የዜጎችን ህይወት የእኔ ህይወትና የእኔ ቤተሰብ ናቸው ብለን አስበን ሃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ።

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሁላችንም የስራችንን ማግኘታችን አይቀርም ።ስለዚህ ሰው የሆነ ሁሉ በሰው ህይወት ላይ መጨከን የለበትም ::

ለተጎጂ ቤተሰቦች  እና ለመላው ህዝባችን መፅናናትን እመኛለሁ !

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top