Connect with us

ሁለት ልክ ያልሆኑ ንግግሮች፤

ሁለት ልክ ያልሆኑ ንግግሮች፤
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሁለት ልክ ያልሆኑ ንግግሮች፤

ሁለት ልክ ያልሆኑ ንግግሮች፤

ያለ ክልሉ የሚኖር አማራ የለም፤ ከሚኖርበትም እናውጣው የሚባል አማራ መኖር የለበትም፡፡ የጋራ አገር የምትኖረን በየቀበሌያችን ተሰብስበን አይደለም፡፡

(ስናፍቅሽ አዲስ~ድሬቲዩብ)

በወለጋ የሆነው እጅግ አሳዛኝ እና ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለ የአውሬ ድርጊት ነው፡፡ በድርጊቱ ማዘን አለማዘን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ይገናኛል፡፡ በተደጋጋሚ በአማራ ብሔር ላይ የሚደርሰው የማንነት ጥቃት የሰካራሙ ህገ መንግስትና ትህነግ ያኖረው ክፉ መርዝ በመሆኑ ላይ አለመግባባት በራሱ ገዳይነት ነው፡፡

አሁን መንግስት ሀገር እየመራሁ ነው ካለ ገዳዮቹን ከኢትዮጵያ ምድርም ከአብሮነት እሴት ስነልቦናችንም ለዘለዓለም ሊያስወግዳቸው ይገባል፡፡ ይሄንን አለማድረግ ቀን ይፈጃል፤ ነገም የንጹሃንን ነፍስ ይጠይቃል እንጂ ዓለም ዝም አይለውም፡፡ አደብ ይይዛል፡፡

ተደጋጋሚ የሆነው ቃልና ልክ ያልሆነው ያለ ክልሉ የሚኖር አማራ የሚለው ነው፡፡ ይሄንን መርዝ ቃል ባለማወቅ ጭምር የአማራ ፖለቲከኞች፣ የብሔረሰቡ ተቆርቋሪ ነን ባዮች፣ ጋዜጠኞችና መንግስት ሲሉት እንሰማለን፡፡ አንድ ነገር መታወቅ ያለበት የጋራ ሀገር እስካለን ድረስ ወለጋም የአማራ ክልል ነው፤ ባህር ዳርም የኦሮሞ ክልል ነው፡፡

ያለ ክልሉ የሚኖርና ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የሚሉት ሰንኮፍ ቃላት መጤ ባይ ለሆኑት የብሔር አክራሪ ሰካራሞች ጉልበት ከመሆን ውጪ የእውነት ትርጉም የለውም፡፡ ሰው ሀገሩ ክልሉ ነው፡፡ እንዴት በአንድ ባንዲራ በአንድ መንግስት እየኖርን አንዱን የሀገር ክፍል ከነሙሉ ክብሩ እንዴት ለአንድ ብሔር ይሰጣል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ህገ መንግስቱን ህገ አራዊት ነው የሚሉት ወደው አይደለም፡፡ በአራዊት ህግስ እንዲህ ከኔ ውጪ ልኑር ባይ አውሬ መኖሩን እርገጠኛ አይደለሁም፡፡ ለምን ይሄ ሁሉ ሆነ ብለን ስንጠይቅ መልሳችን የጥፋተኞቹን ሀሳብ የሚያከብር እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡

በሌላ በኩል እንዲህ ሞት ሲበዛ ወንጀለኛው ቅጥ ሲያጣና አራጁ ሲበረታ ተጋግዞ ህግ ማስፈን እንጂ በቃ ኑ ውጡ ማለትም ልክ አይደለም፡፡ 

ሰው ከሀገሩ የት ነው የሚወጣው፡፡ ጥቂት ወንጀለኞች ዛሬ አማራን ወለጋ ላይ አንመልከት ብለው አያበቁም፤ ነገ ቋንቋ ተናጋሪያቸውን መልሰው ካልዋጥንህ በማለት ደግሞ አካባቢያዊነትን ያቀነቅናሉ፡፡ እንዴት ለሽፍታ ሀገር ለቃችሁስ ውጡ ይባላል?

አማራ ወለጋ የገባው ሀገሬ ነው ብሎ ነው፡፡ በሀገሩ ካልኖረ ሀገሩ የት ነው? ሀገርህን ጥለህ ወጥተህ በየመንደሩ ተሰብሰብ መባባል ከጀመርን ከየሰፈራችን የማንወጣባት ትልቅ ሀገር ለእኛ ጥቅሟ ምንድን ነው? ወለጋ አትኖርም የተባለ አማራ ኢትዮጵያስ ምኑ ናት? ገዳይ በበረታ ቁጥር ወገኔን አወጣለሁ የሚለው የማይቆም ወንጀል ቢቀጥል ምን መልስ አለው፡፡

አንድ ሀገር አለን ካልንና ከተስማማን አንድ እና እኩል የትም የመኖር መብት ሊኖረን ይገባል፡፡ በየሰፈራችን እየኖርን ትልቅ ሀገር አለን ማለት ቀልድ ነው፡፡ ውጣልኝ የሚለውን ልውጣልህ ብለን ከመለስንለት ከእሱ ጋር አንድ ሀገር መኖር ጠቀሜታውስ ምን ድን ነው?

ሁለቱን ቃላት እንጣላቸው ያለ ክልሉ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ 

ኢትዮጵያዊ ሀገሩ በሙሉ ክልሉ ናት፡፡ ሞተንም ተገድለንም ማረጋገጥ ያለብን የቱም ኢትዮጵያዊ የትም እንዲኖር እንጂ በየሰፈራችን ለመኖርና ከየሰፈራችን ላለመውጣት የጋራ ሀገር ምንም አያደርግልንም፡፡

በሌላ በኩል ተደጋግሞ የሚነሳ የህግ የበላይነት አለመከበር ለወንጀለኛው ጥቅም በሚያደላ የራስ ውሳኔ መደምደም የለበትም፡፡ በምንም መልኩ ህግ ተክብሮ ዓለም ጭምር ጣልቃ ገብቶ ወንጀለኛ አደብ ይገዛል እንጂ ሀገር ሳይፈርስ ሰው ከሀገሩ የትም መውጣት የለበትም፡፡ 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top