Connect with us

ከግማሽ በላይ የ12 ክፍል ተፈታኞች ከ350 በላይ ውጤት አመጡ

ከግማሽ በላይ የ12 ክፍል ተፈታኞች ከ350 በላይ ውጤት አመጡ
ትምህርት ሚ/ር

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ከግማሽ በላይ የ12 ክፍል ተፈታኞች ከ350 በላይ ውጤት አመጡ

ከግማሽ በላይ የ12 ክፍል ተፈታኞች ከ350 በላይ ውጤት አመጡ

– ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ ማየት ይችላሉ፣

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ  ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

የሀገር አቀፍ  ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦተሪ(ዶ/ር) የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና  በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ  ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ  55.7 ፐርሰንቱ  ከ 350 በላይ አምጥተዋል።

በመግለጫው የፈተና ውጤት ከባለፈው አመት  ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን  በዚህም ከ 600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች  702  መሆናቸው ተገልጿል።

የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም  669 ሆኖ መመዝገቡን  ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

ተማሪዎችም በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ  ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።(ትምህርት ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top